Get Mystery Box with random crypto!

አደራችሁን! አቅልላችሁ እንዳታዩት! ከስር የሶስቱ ክልሎች መዝሙር ላይ የተቀነጨቡ ስንኞች ተቀምጠ | Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®

አደራችሁን! አቅልላችሁ እንዳታዩት!

ከስር የሶስቱ ክልሎች መዝሙር ላይ የተቀነጨቡ ስንኞች ተቀምጠዋል። እያወራን ያለነው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በግለሰብ ስለተለቀቀ ጉዳይ አይደለም። አንድ ሰሞን መነጋገሪያ ስለሆነ ነጠላ ዜማ አይደለም። ትውልድ 30 አመት በላይ አይኑን ጨፍኖ በስሜት እየዘመረው ስለመጣበት ጉዳይ ነው ልዩነቱን ታገኙታላችሁ።

1)የኦሮሚያ ክልል መዝሙር

የመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽ
በብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘን
...........
ኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብን
ኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!

2)  የትግራይ  ክልል መዝሙር
.....
በጭራሽ አንሸነፍም!
......
በፀሀይ ሀሩር እና በቁር
ነፍሳችን ውሀ ይጥማት
አለት ይሁን ትራሳችን
ዋሻ ይሁን ቤታችን
ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም
.............
በጅቦች እንከበብ መሬት ይክበበን
የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር!
ስጋችን ላሞራ ደማችን እንደ ጎርፍ ይፍሰስ፤
አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን
............
የጦር መሳሪያ መርዝ ፋሽስታዊ ንዳድ
ሚሊየን ጠላቶቻችን ፊታችን ላይ ይጉረፉ
መስዋዕትነት መቁሰል እና ኪሳራም እንከፍላለን፤
የከፋ መከራም ቢመጣ ወደን እንከፍላለን

3) የአማራ ክልል መዝሙር
የአማራነት ክብር ደማቅ አርማ ይዘን ፥
ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን
በፍቅር በአንድነት አብረን እንዘልቃለን ።

በነገራችን ላይ አማራ ክልል ብዙ አካባቢዎች ይህ የአማራ ክልል መዝሙር እንደ ከፋፋይ ተቆጥሮ ተማሪዎች የኢትዮጵያ መዝሙርን እንዲዘምሩ ይደረግ ነበር። አንዳንድ ክልሎች ደግሞ እንደ አሁኑ ማህበራዊ ሚዲያ ሳይኖር ህዝብን በመዝሙር መስደብን ስልት አድርገውታል። ሊረዝምባቸው ሆኖ ተቸግረው ይሆናል እንጅ ግለሰብ ጠቅሰው ቢሰድቡም ደስ የሚላቸው አይጠፉም።