Get Mystery Box with random crypto!

ኢዜማ ኢዜማ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እንዲዘመርና ባንዲራው እንዲው | Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®

ኢዜማ

ኢዜማ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እንዲዘመርና ባንዲራው እንዲውለበለብ የሚደረገው "ሕገወጥ ተግባር" እንዲቆም ትናንት ባወጣው መግለጫ በድጋሚ ጠይቋል።

ኢዜማ ድርጊቱ በቶሎ ካልተገታ ወደ ሕግ ወስጄ መፍትሄ እንዲያገኝ አደርጋለሁ ብሏል። "ሕገወጡ" ድርጊት እንዲቆም የሚጠይቁ ደብዳቤዎችን ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ማስገባቱን የጠቀሰው ኢዜማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ግን ደብዳቤውን ሁለት ጊዜ አልቀበልም ማለቱን ገልጧል።

ፓርቲው ትምህርት ቢሮው በዚህ ድርጊቱ፣ "ለሕግ እንደማይገዛና በማናለብኝነት እንደሚንቀሳቀስ" አስመስክሯል በማለት ከሷል