Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና! መምህርት መስከረም አበራ በድጋሜ ታሰረች! የፖለቲካ ተንታኝ እና መምህር መስከረም | Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®

ሰበር ዜና!

መምህርት መስከረም አበራ በድጋሜ ታሰረች!

የፖለቲካ ተንታኝ እና መምህር መስከረም አበራ የፌዴራል የጸጥታ አካላት ልብስ በለበሱ ግለሰቦች መወሰዷን ባለቤቷ አቶ ፍፁም ገብረሚካኤል ለአማራ ድምጽ ገለጹ።

ዛሬ ከቀኑ 11 ሰአት ገደማ 22 አካባቢ ከባለቤቷ ጋር ተቀምጣ በነበረችበት ወቅት የደህንነት አካላት ነን ያሉ ግለሰቦች እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ልብስ የለበሱ አካላት ለጥያቄ እንፈልግሻለን በሚለው ወደ ፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደወሰዷት ባለቤቷ ተናግሯል።

ባለፈው ግንቦት ወር በርካታ ጋዜጠኞች እና የማኅበረሰብ አንቂዎች በመንግስት የጸጥታ አካላት በታሰሩበት ወቅት መስከረምም ታስራ እንደነበር የሚታወስ ነው። መምህርት መስከረም "ንቃት" በሚል የዩቲዩብ ቻናሏ የፖለቲካ ሀሳቦቿን በማጋራት ትታወቃለች።