Get Mystery Box with random crypto!

በማዕከላዊ ጎንደር  ዞን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ  የእህቱን ልጅ አግቶ 150 ሽ ብር የጠየቀው ግለ | Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®

በማዕከላዊ ጎንደር  ዞን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ  የእህቱን ልጅ አግቶ 150 ሽ ብር የጠየቀው ግለሰብ በምዕራብ  አርማጭሆ ወረዳ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ።

የወረዳው ፖለስ ፅ/ቤት ሀላፊ ኢንስፔክተር አበበ ደጀን እንደተናገሩት  የታጋች ስም ህፃን አሜሪካው እያዩ  እንደ ሚባል ጠቁመው የ3 ዓመት ህፃን መሆኑን ተናግረው የአጋች ስም ገበያው በሌ ታረቀኝ  ሲሆን ነዋሪነቱ በምስራቅ  ደምቢያ ወረዳ የአይንባ  ንዑስ ወረዳ ነዋሪ እንደሆነ ጠቅሰው የእህቱን ልጅ በማገት 150 ሽ ብር ለመጠየቅ  መሆኑን ኢንስፔክተሩ  አስረድተዋል ።

ሰለሆነም አጋቹ በቁጥጥር ስር የዋለው በቀን 01/04/2015  ዓ/ም  ከምሸቱ 1:00  መሆኑን ከፖሊስ ያገኘነው  መረጃ  ያመለክታል ።

የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ኮሚኒኬሽን