Get Mystery Box with random crypto!

መቀሌ የመከላከያ ሠራዊት  መቐሌ ሊገባ ነው በደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መሰረት  ህወሓ | Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®

መቀሌ

የመከላከያ ሠራዊት  መቐሌ ሊገባ ነው

በደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መሰረት  ህወሓት ሁሉንም ከባድ እና የቡድን መሣሪያዎቹን ለመከላከያ ሠራዊት እንዲያስረክብና የፌደራል መንግሥትም መቀሌን እንዲረከብ የሚያስችል ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል፡፡

ከትግራይ ክልል የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ህወሓት በሰላም ስምምነቱ መሰረት በተለያዩ ግንባሮች  የሚገኙ ከባድ እና የቡድን መሣሪያዎቹን ለመከላከያ ሠራዊት ለማስረከብ በመቀሌ አቅራቢያ በሚገኝ  ሥፍራ እየሰበሰበ ይገኛል፡፡ ታጣቂዎቹንም ከሁሉም ግንባር በማምጣት የተሓድሶ ሥልጠና ወደሚሰጥባቸው  ካምፖችም አስገብቷል፡፡ ይህን ተከትሎም በስምምነቱ መሰረት የመከላከያ ሠራዊት በጥቂት ቀናት  መቐሌን እንዲረከብ መግባባት ላይ ተደርሶና አቅጣጫ ተቀምጦ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ መንግሥት በተከታታይ እየወሰደ የሚገኘው እርምጃ ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት ቁርጠኛ መሆኑን እንደሚያሳይ፤ ህወሓትም የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ያከናወናቸው እንቅስቃሴዎች ተስፋ ማጫራቸው የተለያዩ ምላሾች እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያውያንን እርስበእርስ በማጋጨት ትርፍ ለማግኘት ተጠንስሶ የነበረው ሴራ እየከሸፈ መምጣቱን መላው ዜጋ እንደ ትልቅ ብሥራት ሲቀበለው፤ በጠላት ሰፈር ግን ያልተገመተ መርዶ ሆኖ እዬዬው እንዲበረክት አድርጓል፡፡  ይሁንና ሁሉንም ጎራ ያስማማው አንድ ጉዳይ ይህንን ሂደት ወደ ኋላ የሚቀለብስ ኃይል አለመኖሩ ነው፡፡

በመላው ኢትዮጵያውያን በተለይ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋ የተጣለበት የሰላም ስምምነት በመሰረታዊ አገልግሎቶች እጥረት ሲፈተን የነበረውን ኅብረተሰብ መከራ ስለሚያቀል፤ ከትምህርት ገበታ ተገልለው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን ተስፋ ስለሚያለመልም፤ በልጆቻቸው የተነሳ የሚሳቀቁትን እናቶችንም እንባ ስለሚያስቆም ሁሉም ለተግባራዊነቱ የድርሻውን ያበርክት፤ ሰላም ይስፈን::