Get Mystery Box with random crypto!

መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።(ትምህርት ሚኒስቴር) መውጫ ፈተና በሁሉም | Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®

መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።(ትምህርት ሚኒስቴር)

መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች በመጪው ሰኔ  ወር  በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር ) ገልጸዋል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ  ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት  በኋላ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ  አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥና፣ ይህም የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ነው ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ  ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ አቶ ሰይድ አሳስበዋል።

በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። (ዘገባውን ያገኘነው ከትምህርት ሚኒስቴር ነው)

በመጨረሻም፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለተፈታኝ  ተማሪዎቹ እና ለሁሉም አካዳሚክ ስታፍ ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው፣ተማሪዎችን በማብቃቱ ስራ ላይ ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ ሲል ያሳስባል።

ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
https://t.me/VOAamhara
https://t.me/VOAamhara
https://t.me/VOAamhara
#shere