2022-12-18 15:01:57
“ለዐቅመ-ሐዋህ መድረስ” እና “የወር አበባ ማየት” ልዩነትበአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው”፡፡ ሱራ አጥ ጠላቅ 65፥4“ዐቅመ-ጋብቻ” ማለት አንድ ተባእት ለዐቅመ-አደም ሲደርስ እና አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ ስትደርስ ማለት ነው። ለምሳሌ “የቲም”
يَتِيم ስንል አጠቃላይ “ወላጅ-አልባ” ማለትም “እናትና አባቱ” ወይም “አባቱን በልጅነቱ በሞት የተነጠቀ ሕፃን” ማለት ነው። የቲሞች እራሳቸው ይችሉ ወይም አይችሉ እንደሆነ ይፈተናሉ፥ ይህም ፈተና ለጋብቻ እስከሚደርሱበት ድረስ ነው፦
የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡ሱራ አን ኒሳእ 4፥6“ኢዛ”
إِذَا ማለት “ጊዜ” ማለት ሲሆን የጊዜ ተውሳከ-ግስ ነው። ጋብቻ የራሱ የሆነ ጊዜ እንዳለው አመላካች ነው፥ ይህም ጊዜ ለማመልከት “ጋብቻን እስከደረሱ” ድረስ በማለት ይናገራል። “በለጉ”
بَلَغُوا ማለት “ለጋብቻ በሰሉ” ማለት ነው፥ “በለገ”
بَلَغَ ማለት “ለጋብቻ በሰለ” ማለት ሲሆን “በለገት”
بَلَغَت ማለት ደግሞ “ለጋብቻ በሰለች” ማለት ነው። “ባሊግ”
بَٰلِغ ማለት እራሱ “ዐቅመ-ጋብቻ” Puberty” ማለት ነው፦
ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ” የሚለውን ሙጃሂድ፦ “ለዐቅመ-ጋብቻ ነው” ብሏል፥ ዐበይት ምሁራን፦ “ለዐቅመ-ጋብቻ” ለጋዎች ኢሕቲላም ሲኖራቸው ነው” ብለዋል።
አቢ ዳውድ በሡናው እንደዘገበው፥ ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦ “ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም።ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 4፥6 ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ እንደተረከው፦ “የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦ “ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም”። ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 12“ዐቅመ-ጋብቻ” አካል ተራክቦ ለማድረግ ሲበስል ነው፥ ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት ስለሌለ የቲሞች እራሳቸው እንዲችሉ ይፈተናሉ። “ኢሕቲላም”
احْتِلاَم ማለት አንድ ልጅ ወይም አንዲት ልጂት ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ ነው። ይህ ፈሳሽ እስኪመጣ ድረስ ለዐቅመ-ጋብቻ ስላልደረሱ የሚሠሩት ሥራ አይመዘገብም፦
ዓኢሻህ “ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦ “ብዕር ከሦስት ሰዎች ተነስቷል። እነርሱም፦ የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ፣ ዕብደ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ፣ ልጅ እስኪጎሎብት ድረስ”።ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 48በእንቅልፍ ልብ፣ በዕብደት እና በእንጭጭነት የሚደረግ ሥራ መላእክት አይመዘግቡትም። አንድ ሕጻን ለዐቅመ-አደም ከደረሰ የሰው ቤት ዘው ብሎ አይገባም፥ ከዚያ ይልቅ አንኳክቶ ያስፈቅዳል፦ ከእናንተም ሕፃናቶቹ አቅመ አዳምን በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ፡፡ሱራ አን ኑር 24፥59አሁን እዚህ አንቀጽ ላይ “ኢዛ”
إِذَا የሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ የዐቅመ-ጋብቻ ጊዜ አመላካች ነው፥ ይህንን ዐቅመ-ጋብቻ ለማመልከት “በለገ”
بَلَغَ የሚል የግስ መደብ ይጠቀማል።
አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ የመድረሷ የመጀመሪያው እና ዐቢይ ምልክት አድሬን-አርክ “adrenarche” አካሏ ለተራክቦ ዝግጁ ሲሆን እንዲሁ ጡቷ ሲያጎጠጉጥ ቴል-አርክ “thelarche” እና ብብቷና ብልቷ አካባቢ ጸጉር መብቀል ፑብ-አርክ “Pubarche” ሲጀምር የምታመነጨው ፈሳሽ “Vaginal lubrication” እንጂ የወር አበባ አይደለም፥ የወር አበባ ማየት አንዲት ሴት ለዐቅመ-ሐዋህ መድረሷን ከሚያሳዩ ሁለተኛ እና ንዑስ ምልክት ዕንቁላል ማምረት ጎናድ-አርክ “gonadarche” እንዲሁ የወር አበባ ደም ሜን-አርክ “menarche” ነው። አንዲት ሴት ስታርጥ የወር አበባ ይቋረጣል፥ ያኔ የምታመነጨው ፈሳሽ ያለ የወር አበባ ተራክቦ ማድረግ ትችላለች። ምክንያቱም ተራክቦ ለማድረግ የወር አበባ ብቻውን መስፈት አይደለም፥ የወር አበባ ለፅንስ እንጂ ለተራክቦ መስፈት አይደለም፦
እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፡፡ ሱራ አጥ ጠላቅ 65፥4“ዒዳህ”
عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው። “ዐደፍ” ለሚለው የገባው ቃል “መሒድ”
مَحِيض ሲሆን “የወር አበባ” ማለት ነው። አንድ ወንድ ከዐደፍ ያቋረጠች ማለትም ያረጠች ሴት ለመፍታት ምናልባት አርጣለች ተብሎ እግዝና ስለሚከሰት የሦስት ወር ጊዜ ይኖራታል። አንዲት ሴት ልጅ ለዐቅመ-ሐዋህ ስደርስ ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግና የሚያጣብቅ ቀለም አልባ እና ሽታ አልባ ቀጭን ፈሳሽ “nocturnal emission” አላት፥ ነገር ግን ይህ ፈሳሽ ኖሮ የወር አበባዋ ሳይመጣ ብዙ ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ይህንን የወር አበባ ያላዩ ሴቶች መሃል ላይ እንቁላል ማምረት ችለው እርግዝና ሊከሰት ስለሚችል ሦስት ወር ባል የማይፈታበት ጊዜ አለ፦
የተጻፈውም ዒዳህ ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ አሳብ አታድርጉ፡፡ አላህም በነፍሶቻችሁ ያለውን ነገር የሚያውቅ መኾኑን ዕወቁ፤ ተጠንቀቁትም፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ መኾኑን ዕወቁ፡፡ሱራ አል በቀራ 2፥235እንግዲህ ዐቅመ-ሐዋህ ጅማሬው አካላዊ ሽግግር”physical transition” የሆኑት ጡቷ ማጎጥጎጥ፣ ብብትና ብልት አካባቢ ጸጉር ማብቀል፣ የተራክቦ ፈሳሽ ማመንጨት ሲሆን ቀጣዩ የእንቁላል እድገት “ovarian development” ልጅ ለመፅነስ መደላድል ነው፥ እንቁላሉ የወንድ የዘር ሕዋስ ካላገኘ የወር አበባ ሆኖ ይወጣል። ይህንን በቅጡ ያልተረዱ ሚሽነሪዎች ዐይናቸውን በማንሸዋረር “የወር አበባ ያላየች ሴት” የሚለውን “ለዐቅመ-ሐዋህ ያልደረሰች” ብለው በማውረግረግ ኢሥላምን ሊዘልፉ ይፈልጋሉ፥ ይህ የደፈረሰ መረዳት ከላይ ያለውን ተስተምህሮት ጥልልና ጥንፍፍ አድርጎ ካለማየት የመጣ የተሳከረ መረዳት ነው። በኢሥላም ምንም ነገር መጉዳት አይፈቀድም፥ ጉዳትም ካለ በቂሷስ ይፈረዳል እንጂ ጉዳት አይመለስም፦
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ “መጉዳት የለም፥ ጉዳትንም መመለስ የለም”።ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 34አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።
ኡስታዝ ወሒድ ዑመር
ወሠላሙ ዐለይኩም
ለተጨማሪ ንባብ
https://tiriyachen.org/?p=4149
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
314 views12:01