Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ፍጡራን አትፀልዩ! “ዱዓ” دُعَآء የሚለው ቃል በቁርአን 22 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ትርጉ | Tiriyachen | ጥሪያችን

ወደ ፍጡራን አትፀልዩ!

“ዱዓ” دُعَآء የሚለው ቃል በቁርአን 22 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ትርጉሙ “ልመና” “ጥሪ” “ፀሎት” የሚል ፍቺ ሲኖረው ለአንዱ አምላክ የሚቀርብ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ፣ መለማመንን ያሳያል፣ ዱዓ በቀውል ከሚደረጉ የአምልኮ አይነት አንዱ ነው፣ አብዛኛው ሰው ወደ ፍጡራን ዱዓ ያደርጋል፤ ነገር ግን ፍጡራን ወደ እነርሱ የሚደረግላቸው ዱዓ እስከ ቂያማ ቀን አያቁም ዝንጉዎች ናቸው፣ በቂያማ ቀን ግን ያንን ዱዓ ሰምተው እንደማያውቁ ይመሰክሩባቸዋል፣ በሰው ልብ ያለውን የሚያውቅ፣ የሁሉንም ልመና በአንድ ጊዜና በተለያየ ቦታ አይቶና ሰምቶ የሚመልስ አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦

2:186
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ ፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ
أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ
ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡


40፥60
ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከማምለክ የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ
وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدْعُونِىٓ أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِى سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ

60:1
እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን የማውቅ ስሆን ወደነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ፤

34:11
እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና።

መለመን፣ መጎባደድ፣ ማሸርገድ፣ መተናነስ አላህን ብቻ ነው፤ እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም፦

7፥197
እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም።
وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ

1፥5
አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን።
إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ


የሚገርመው አጋሪዎች ዱዓ በማድረግ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው የሚይዙት አላህ፦ “ባሮቼ” የሚላቸውን መላእክትንና ነቢያትንም ነው፦

18፥102
እነዚያ የካዱት *ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን* የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲዎች መስተንግዶ አዘጋጅተናል።
أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَن يَتَّخِذُوا۟ عِبَادِى مِن دُونِىٓ أَوْلِيَآءَ ۚ إِنَّآ أَعْتَدْنَا جَهَنَّمَ لِلْكَٰفِرِينَ نُزُلًۭا


3:80
“መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ” ሊያዛችሁ አይገባዉም፤ እናንተ ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክሕደት ያዛችኋልን?

43:19
“መላክትን እነርሱ የአልረሕማን ባሮች” የሆኑትን ሴቶች አደረጉ፤ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በርግጥ ትጻፋለች፤ ይጠየቃሉም።

38:45
“ባሮቻችንንም” ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆበንም፣ የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የኾኑን አውሳላቸው፡፡

አንድ ሰው አንድ ነገር አምላክ አርጎ ያዘ ማለት አምላክ ብሎ መጥራት ብቻ ሳይሆን አምላክ አድርጎ መያዝም ነው፣ ያ ማለት ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠትን ያመለክታል፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦

25:43
ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን اتَّخَذَ ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?

ሰዎች ከአላህ ሌላ አማልክትን ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው ቢይዙም የትንሳኤ ቀን እነዚያ ዱዓ ሲደረግላቸው የነበሩት አካላት ከአምላኪዎች ተቃራኒ በመሆን አምልኮ እንዳልተቀበሉ ይክዳሉ፦

19፥81-82
*ከአላህም ሌላ አማልክትን* ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው *ያዙ*
وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةًۭ لِّيَكُونُوا۟ لَهُمْ عِزًّۭا
ይከልከሉ፤ *ማምለካቸውን በእርግጥ ይክዷቸዋል፡፡ በእነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል*
كَلَّا ۚ سَيَكْفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمْ وَيَكُونُونَ عَلَيْهِمْ ضِدًّا

28:62-63
አላህ የሚጠራባቸውንና እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው የሚልበትን ቀን አስታውስ፤ እነዚያ በእነርሱ ላይ ቃሉ የተረጋገጠባቸው ይላሉ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ እነዚያ ያጠመምናቸው ናቸው፡፡ እንደጠመምን አጠመምናቸው፡፡ ከእነርሱ ወደ አንተ ተጥራራን፡፡ *”እኛን ያመልኩ አልነበሩም”*፡፡