2022-12-15 19:28:28
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
የሁሉም ክልል ተማሪዎች በሁለተኛው ዙር ለፈተናው እንዲቀመጡ የተለየ ሲሆኑ እነርሱም፦
• የመጀመሪያ ዙር ፈተናን በወሊድ ወይም በእርግዝና ምክንያት መፈተን ያልቻሉ፣
• በህግ ጥላ ስር ወይም በማረሚያ ቤት ሆነው በነበረው መፈተኛ ሁኔታ ለመፈተን ያልቻሉ፣
• የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወይም የፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ልዩ ኃይል አባል ሆነው በወቅቱ በግዳጅ ላይ በመሆናቸው ያልተፈተኑ፣
• በህመም ወይም ተቀባይነት ባገኘና ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ፈተና ያልወሰዱ፣
• ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ያልተፈተኑ፣
• በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አንድ ፈተና እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው፣
• ተቀባይነት ባገኙ ችግሮች ምክንያት ፈተና እንዲወስዱ የተወሰነላቸው።
የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ https://t.me/Temhert_Minister
https://t.me/Temhert_Minister
3.8K views16:28