Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of education ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_minister — Ministry of education ® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ temhert_minister — Ministry of education ®
የሰርጥ አድራሻ: @temhert_minister
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 52.02K
የሰርጥ መግለጫ

Only for promotion
Contact us- @cr7_well

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 28

2022-08-29 08:07:03
ለ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪ ምዝገባ ከነሐሴ 23-ፃጉሜ 4/2014ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ይካሄዳል የአማራ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ልጆችን ማስተማር የዜግነት ግዴታን መወጣት መሆኑን በመረዳት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትን ወደ ትምህርት ቤት ልከው ዛሬውኑ ያስመዝግቡ ይላል ትምህርት ቢሮው።

መረጃው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ነው

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
6.1K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:22:37
በአማራ ክልል የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23 - ጳጉሜ 04 ይካሄዳል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በዚህም በ2015 የትምህርት ዘመን ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ቢሮው ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጷጉሜን 04/2014 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን የጠቆሙት የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጌታቸው ቢያዝን፤ በዚኽም 895 ሺህ 404 የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ገልጸዋል።

እድሜያቸው 7 ዓመት የሞላቸው ተማሪዎች 714 ሺህ 518 ተማሪዎች እንደሚመዘገቡም አስረድተዋል። በአጠቃላይ 745 ሺህ 708 የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው አንስተዋል።

በአጠቃላይ 4 ሚሊዮን 144 ሺህ 845 ተማሪዎች በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲኹም 1 ሚሊዮን 219 ሺህ 301 ተማሪዎች በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚመዘገቡ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።

ምዝገባው አዲስ ተማሪዎችን ብቻ ሳይኾን በተለያየ ጊዜ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን የሚያካትት እንደኾነ አቶ ጌታቸው አስረድተዋል። በ2014 ዓ.ም 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋልም ነው የተባለው። (አሚኮ)

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
8.0K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:01:09
የካናዳ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፍ ገለፀ
--------------------------------- ----------------------------------

የትምህርት ሚኒሰትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የካናዳ መንግስት አምባሳደር ከሆኑት ሚስተር ስቴፋኒ ጆቢን ጋር ነሐሴ 19/2014 ዓም ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ላይ የተነጋገሩ ሲሆን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሃ-ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ የካናዳ መንግስት ሊያደርግ ስለሚችለው ድጋፍ እና የበጎ ፈቃደኞች መምህራን ስምሪት ላይ ውይይት ተደርጓል።

የካናዳ አምባሳደር በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ አድንቀው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሃግብር ለማሳካትም በኤምባሲያቸው በኩል፣ በካናዳ ዓለምአቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስቴር እና የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎች አማካይነት እና በኦታዋ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ ግብረሃይል ጋር በመነጋገር እና በማስተባበር የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተለያዩ የለውጥ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
7.3K views05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 00:20:32
የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

ለወንዶች 41፣
ለሴቶች 40 እና
ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

ለወንዶች 39፣
ለሴቶች 38 እና
ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

#ENA

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
6.7K views21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:13:15
ለጂማ ዩንቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩንቨርሲቲ እንዲሰጥ መወሰኑን ተከትሎ ሁሉም ተማሪ ከዶርም መዉጣት ስላለበት

1ኛ. እረፍት ላይ ያላችዉ ንብረታችሁን ዶርም አስቀምጣቹ የሄዳቹ ተማሪዎች እስከ ጳጉሜ 05/13/2014 ዓ.ም ድረስ እንድታወጡ፤

2ኛ. ትምህርት ላይ ያለቹ ተማሪዎች ከግቢ ስትወጡ ንብረታችሁን ይዛችዉ እንድትወጡ እያሰሰብን፤ በተጠቀሰው ቀን ዉስጥ ንብረቱን የማይወስድና ይዞ በማይወጣ ተማሪ ለሚፈጠረዉ ችግር የመኝታ ክፍሉ ተጠያቂ እንደማይሆን በጥብቅ እናሳስባለን ።


ጅማ ዩኒቨርሲቲ

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
6.9K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 10:26:34
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራው ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
------------------------------------------------------------------------

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ስራ ሙሉ በሙሉ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የፈተና ዝግጅቱም የተማሪዎችን ልፋት ሊለካ በሚችል ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ውጤታማነት ከመፈተኛ ቦታ መረጣ ጀምሮ የፈተና ኮዶችን ብዛት ከፍ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የራሳቸው ጥረት ውጤት ለማግኘት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዋና ዳይሬክተሩ ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆችም መረጃዎችን ከተቋሙ እና ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ብቻ እንዲከታተሉም ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ መስከረም 30,2015ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
8.1K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 16:40:57
ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ይላል።

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናው እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
8.6K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 14:40:53 የ2014 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ይካሄዳል።

ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ይፈተናሉ

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 ስሆኑ በ 1ኛ ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 ይፈተናሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 361,279 ሲሆኑ በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11ይፈተናሉ።

የፈተናው ቦታ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ስሆን ፈታኞች ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ናቸው።

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
8.1K viewsedited  11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:51:53
“የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” መባሉ ስህተት ነው - ኢትዮጵያ ቼክ

ከ865 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና "Mereja TV" የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ “የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” የሚል መረጃ ማጋራቱን ታይቷል። ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማጣራት የተጋራውን ቡክሌት የመረመረ ሲሆን መረጃው ሀሠተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት “የዘንድሮ” ነው ተብሎ የተጋራውን የታሪክ ፈተና ቡክሌት በ2013/14 ዓ.ም የተሰጠ እንጂ አዲስ አለመሆኑን ተመልክተናል። በተጨማሪም ጉዳዩን በተመለከተ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ የተሰራጨውን መረጃ መመልከታቸውን ገልጸው ሀሠተኛ መሆኑንና የተጋራው የፈተና ቡክሌት በ2013/14 (2021) ዓ.ም የተሰጠ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድተዋል።

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
18.3K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 10:57:37 የት/ት ፍኖተ ካርታ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ11ኛ-12ኛ ክፍል ናቹራል ሳይንስ ዲፓርትመንት የሚሰጡ የት/ት አይነቶች::
====================
አንድ ክ/ጊዜ 45 ደቂቃ አለው፡፡

በቀን 7 ክ/ጊዜ

በሳምንት 35 ክ/ጊዜ

የት/ት ሠዓት በየፈረቃው 4ሰዓት ከ40 ደቂቃ ነው፡፡
====================
ቋሚ (7ቱ) የት/ት አይነቶች እና የክ/ጊዜ ብዛት:-
====================
1ኛ= የእንግሊዘኛ ቋንቋ የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 4 ፣የሳምንት የት/ት ሠዓት 3 ሰዓት እና የዓመቱ የት/ት 117 ሰዓት ነው፡፡
2ኛ= ሒሳብ ክ/ጊዜ 4፣ በሳምንት 3ሠዓት እና በአመት 117 ሠዓት አለው፡፡
3ኛ= ባዮሎጂ የሳምንት ክ/ጊዜ 3 ፣ የሳምቱ ሠዓት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና የአመቱ 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
4ኛ= ኬሚስትሪ በሳምንት3 ክ/ጊዜ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
5ኛ= ፊዚክስ በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፤ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
6ኛ= አይቲ በሳምንት 3 ክ/ጊዜ፣ በሳምንት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
7ኛ= ግብርና ት/ት በሳምን 3 ክ/ጊዜ ፣ በሳምንት 3ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡
አጠቃላይ የዋና የት/ት አይነቶች የሳምንት ክ/ጊዜ ብዛት 26 (17ሰዓት ከ20 ደቂቃ) እና በዓመት 676 ሰዓት ይሆናል፡፡
ተጨማሪ አማራጭ 5ቱ የሙያ ፊልዶችና በስሩ የሚገኙ የት/ት አይነቶች:-
===================
#አምራች(ማኑፋክቸሪግ) ፊልድ የመረጡ ተማሪዎች፡፡
====================
1ኛ= ብረተብረት ስራ
2ኛ=ጥገና(አውቶ) ስራ
3ኛ=የጨርቃጨርቅና የቆዳ ስራ
4ኛ=የእንጨት ስራ ናቸው፡:
===============
#ኮንስትራክሽን ፊልድ የመረጡ ተማሪዎች:-
===============
1ኛ=ኤሌክትሪክ ሲቲ
2ኛ=ቧንቧ ስራ
3ኛ=አናፂነት
4ኛ=የቀለም ቅብ ስራ ናቸው::
==================
#አይሲቲ ፊለድ የመረጡ ተማሪዎች:-
==================
1ኛ=አይቲ
2ኛ=የኮምፒዩየተር ጥገና እና ኔትወርክ
3=ዌብሳይት ዲዛይን
4ኛ=ኮምፒዩተር ንድፈ ዲዛይን ናቸው::
=====================
#ግብርና የመረጡ ተማሪዎች:-
=====================
1ኛ=ሰብል ማምረትና አስተዳደር
2ኛ=የእስሳት እርባታና አስተዳደር
3ኛ=የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር
4ኛ= የግብርና ቴክኖሎጂ ናቸው::
=================
ጤና ሳይንስ የመረጡ ተማሪዎች:-
=================
1ኛ=የግልና የማህበረሰብ ጤና እና የበሽታኛ አያያዝ::
2ኛ=የምግብና የማዕድ ጥናት
3ኛ=የህፃናት እንክብካቤና ደህንነት
4ኛ= ጤናማ ተዋልዶ ናቸው:: ስለሆነም እያንዳንዳቸው የሙያ የት/ት አይነቶች በሳምንት 3ክ/ጊዜ (3ሰዓት ከ15ደቂቃ) እና በዓመት 87 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው፡፡

በአጠቃላይ የቋሚና የሙያ የት/ት አይነቶች በሳምንት 35 ክ/ጊዜ ወይም 26 ሰዓት ከ15 ደቂቃ እና በዓመት 1023 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አለው:: ሰለሆነም የት/ት እቅዱ በዚህ ስሌት መሠረት የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡

@Temhert_Minister
@Temhert_Minister
7.9K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ