Get Mystery Box with random crypto!

(✍ ስለ ህይወት✍)

የቴሌግራም ቻናል አርማ sle_hiwot — (✍ ስለ ህይወት✍)
የቴሌግራም ቻናል አርማ sle_hiwot — (✍ ስለ ህይወት✍)
የሰርጥ አድራሻ: @sle_hiwot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 794
የሰርጥ መግለጫ

👉 የህይወታችን ትርጉም የሚወሰነው በኛ መኖር ውስጥ በምናኖረው አካል ነው።
ማኖር ያለብን በእኛም ሊኖር የተገባው ኢየሱስ እሱ የህይወታችን ትርጉም ነው ህይወት ኢየሱስ ነው ስለ ኢየሱስ እናወራለን ተባረኩልኝ❤🙏
ለማንኛውም አስተያየትና ሀሳብ👉 @Elsinaaaa
@sle_hiwot
@sle_hiwot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-10 22:39:36 በሁሉም ነገር ላይ ኢየሱስ ጌታ ነው
ጌትነቱን እያሰቡ በርሱ ሙሉ በሙሉ ማረፍ ይሁንላችሁ

https://t.me/sle_hiwot
22 viewsedited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 14:36:06 መኖሪያችን የዘላለም አምላክ ነው!

የአንዳንድ ነገሮች መኖርና አለመኖር እግዚአብሔር እኛን እያስጓዘበት ላለው መንገድ መቃናት አያግዘውም ደግሞም አያስተጓጉለውም።
እንዴት እንዲያኖረን እያኖረን ያለው እሱ በራሱ እርግጠኛ ነው።
ደስ ሲል

https://t.me/sle_hiwot
86 views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 09:36:19 በመልካምነቱ ከክፉ ሁሉ ከልሎ ባይጠብቀን ኖሮ አስባችሁታል አይደለም መጨረሻችን አሁናችን ራሱ ምን ሊሆን እንደሚችል?? ዛሬን እንዲህ ባለ መልኩ እንድንኖር ሲያደርገን ስለብዙ ምህረቱ ሳስብ እገረማለሁ።
በኢየሱስ መደነቅ ይሁንላችሁ


https://t.me/sle_hiwot
117 views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 22:32:26 በእግዚአብሔር ፊት መንበርከክ

በአለም ኮተት ተፅዕኖ ስር ላለመውደቅ፣ በሀጢአት በተስፋ መቁረጥ ወዘተረፈ ፊት ላለመንበርከክና ላለመገዛት ከተፈለገ ሁሉን በሚችለው አምላክ ፊት መንበርከክ እና ለሱ መገዛት ግድ ይላል ....በጌታ ፊት በተንበረከክን ቁጥር የምድር ነገር ለኛ ይገዛል ይንበረከክልናል አለዛ ሁሌም ተሸናፊ ነን። ለአሸናፊነት ህይወት በተሸነፈ ልብ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ዋና ጉዳይ ነው።

ሁልጊዜ አምላክ እግዚአብሔርን ማውራትና የጠበቀ ህብረት ማድረግ እንዲሆን ለምንፈልገው አንዳች ነገር በብዙ ይጠቅማል..........ምንም አይነት ሁኔታ ቢፈጠር ይሄ ህብረት እንዳይቀልብን መሰዊያውችን እንዳይፈርስብን እንጠንቀቅ መጠበቂያችንን አንልቀቅ 1ቀን ውዳችን ሲመጣ እንዳያጣን "እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ሀይላቸውን ያድሳሉ......" አይደል የሚለው ቅዱስ ቃሉ እንደዚህ ካለን የማይጠባበቁ ሁሉ ሀይላቸውን አያድሱም ማለቱ ነው። ስለዚህ መጠበቅን እንልመድ በትዕግስት በፅኑ ተስፋ እንጠባበቅ። ከመጠበቂያችን ፈቀቅ ባልን ቁጥር ሀይላችን እየደከመ እንጂ እየታደሰ የሚሄድበት እድል አይኖርም።

እግዚአብሔር ደስ ለማሰኘት መትጋት፣ለፀሎት መትጋት፣ የጌታን ቤት እንደቀልድ አለማየት፣ ከተራ ልማድና ስርአት ያለፈ ቢሞሉት ቢሞሉት በማይጠገብ በሀያል መንፈስ መሞላት..............በብርቱ ረሀብ መጠባበቅ ይሁንላችሁ

እወዳድዳችኋለሁ መልካም ቆይታ

https://t.me/sle_hiwot
182 views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 14:34:29 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው

ሁሌም የእግዚአብሔርን አብሮነት ሳስብ ደስ ይለኛል። ከንቱ እንዳልሆንኩ መድረሻ እንዳለኝ ተቅበዝባዥ ብኩን እንዳልሆንኩ የያዘኝ ታማኝ እንደሆነ አስባለሁ

ዙሪያችንን ቃኝተን የሚገባን ባዶነት ብቻ ሲሆን ድቅድቁ ጨለማ ከፊታችን ተጋርጦ መራመድ ሲያቅተን የሚዳሰስና የሚጨበጥ አንዳች ነገር ባጣንበት ሀዘን በርትቶ መፅናናት ተስኖን በዚህ ሁሉ መሀል ግን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አለ።

ተስፋን የሰጠን እሱ የታመነ አምላክ ነው በዘላለም ፍቅሩ የወደደን መቼም የትም በምንም ሁኔታ የማይተወን ፣ እጃችንን የሚይዝ አብሮን የሚሆን አካል ፍለጋ ስንንከራተት ብቸኝነት ሲነግስብን ማንም የለኝም እንዳንል "አትፍሩ እኔ እስከ አለም ፍፃሜ ከእናንተ ጋር ነኝ ያለ አምላክ አለን" ኢየሱስ አይረሳንም አሁንም ይወደናል ይሄ ጌታ ይፈልገናል ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አይተወንም ኧረ እንኳንም በእጆቹ ተያዝን እንኳንም ሰበሰበን

አንዳንዴ አስባለሁ ጌታ በቤቱ ባይዘን ኖሮ እንደምናየው እና ላለመሆን እንደምንመኘው አመፀኛ ወጣት የማንሆንበት ምክንያት አልነበረም ፣ ሴሰኛና ርኩሰት የነገሰብን የምናደርገውን እያንዳንዱን ነገር ባለማስተዋል የምንፈፅም እንሆን ነበር በመንፈስ ቅዱስ ቀድሞ የገባን ፍቅር ከንቱ መሆኑን አስረድቶን ናቅነው እንጂ ፣ ሙታን ነበርን ሞታችንን በሞቱ ሽሮ ከህያዋን መንደር ቀላቀለን እንጂ። ከዚህ ሁሉ ጠብቆ በደሙ ዋጅቶ ሰው አድሮጎን ሲያበቃ መንገድ ላይ የሚጥል አምላክ አይደለም ደሞ የምን መፍራት የምን ተስፋ መቁረጥ ነው ኧረ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አለ። ምንም ውስጥ እንሁን እግዚአብሔር አለ።

ሰዎች አልተቀበሉንም ማለት እግዚአብሔር አልተቀበለንም ማለት አይደለም ፣ ማንም አይቶን እንዳላየና ሰምቶ እንዳልሰማ አልፎናል ማለት ጌታም እንደዛ ነው ማለት አይደለም።

ልቤ ብዙ ጊዜ አዝኖ ያውቃል ብዙ አልቅሼ አውቃለሁ ግን ለመልካም ሲሆንልኝና ስማርበት ሳልፈው እንጂ ሲሰብረኝ ወይም እዛው ሳለቅስ አልቀረሁም።

ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ። ነገር የተባለው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ከመኖሩ የተነሳ እኛን በአንዳች አይጎዳንም ምክንያቱም የያዘን አባታችን እሱ ልጆቹን ለየትኛውም ሁኔታ አሳልፎ የሚሰጥ ሰነፍ እረኛ አይደለም።

እግዚአብሔር በማዳኑ፣ በምህረቱ ፣በቸርነቱና በማፅናናቱ በብዙ ፍቅር አብሮን አለ። የሚያስብልን የሚጠነቀቅልን አባት አለ ያለርሱ ፈቃድ የፀጉራችን አንዷ ዘለላ እንኳን አትወድቅም

መልካም ቆይታ እወዳድዳችኋለሁ

https://t.me/sle_hiwot
382 views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 22:57:23 በነገርሽ ላይ ሰይጣን አፈ ቅቤ ነው "ኧረ እስኪ ድርቅ አትበይ ቀለል አድርጊው" ይልሻል አ? እንዳትሰሚው ሩጫሽን ቀጥይ እምቢ በይ።ሀጢአት ላይ ተለሳልሶ የተሳካለት ሰው አናውቅም ድርቅርቅ በይ እሺ እህቴ ........... ትንሽ ከድርቅናሽ ወጥተሽ ከላላሽ አጣጥፎ ጠቅልሎ የሚጎርስ ዲያብሎስ እንጂ በርክሰትሽ ደስ ብሎት "በርቺ የሚል አምላክ" የለሽም

https://t.me/sle_hiwot
361 views19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 21:54:24 የህሊና ፀፀት የማያስከትለውን ራስንም ሰውንም የማይጎዳውን የዋህነት የተሞላበትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖር ትልቅ ነገር እንደሆነ አስባለሁ

በህይወት መንገዳችን ብዙ አይነት ሰዎች ያጋጥሙናል፤ አንዳንዶቹ "ምርጥ ሰው ማለት እንዲህ ነው" የሚያስብሉ ሲሆኑ፤አንዳንዶች ደሞ በተቃራኒው የሰው ፍጥረት የተባለ እንድንጠላ እይታችን ላይ መጥፎ ተፅዕኖ ያሳድራሉ

በዚህ ሁሉ ስናልፍ ግን እንዲህ ብናስብ መልካም ነው:- "ማንም ምንም ሊሆን ይችላል ምንም ሊያደርግ ይችላል ከሰው ጋር በህብረት መኖር አማራጭ የሌለው ምርጫችን፣ አምላክ የሰጠን መርህና የህይወት ክፍላችን ዋነኛው ተግባር ነው" ስለዚህ የህሊና ፀፀት የማያስከትለውን ራስንም ሰውንም የማይጎዳውን የዋህነት የተሞላበትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንድንኖር ፀጋው ለሁላችን ይብዛ። በፍፁም የዋህነትና ብልህነት በብዙ ሰላም መኖር ይሁንልን

“ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።”
— ገላትያ 6፥9

Maybe አጋጥሟችሁ ከሆነ አላውቅም ግን ክርስቶስን በእኛ ለማሳየት(ሰዎች እኛን አይተው የልጁን መልክ እንዲያዩ )ካለን ረሀብ የተነሳ ክርስቶስን ለመምሰል ዳዴ በምንልበት የህይወት መንገድ ለመልካም ያሰብነው ለክፉ ተተርጉሞብን ልንደነግጥ እንችላለን፣ እየቆሰልን እንስቃለን እያስቀየሙን ነገሩን አቅልለነው እናልፋለን፣ በብልጣብልጥነት እያታለሉን or እየዋሹን እያወቅነው ለነገሩም ሰውኛ ምላሽ መስጠት እየቻልን በሞኝነት ዝም ብለን ልናልፍ እንችላለን። ያን ጊዜ እነ እከሌም ማጭበርበሩን ይጨምራሉ በዚያ ሰአት ጌታ ትዕግስቱን ካልሰጠን እኛም ከነሱ የባስን ተንኮለኞች የምንሆንበት እድል ሰፊ ነው። ፀጋው ይርዳን

አንዳንዴ "ጌታ ሆይ እኔ በፈለኩትና ይመቻል ባልኩት መንገድ ሄጄ አንተን ደስ ከማያሰኝ ነገር ጋር እንዳልቀጥል እና አንተ በኔ እንዲሆን ከፈለከው ነገር ጋር እንዳልተላለፍ አደራ" ብለን እየፀለይን ፀሎታችንን የሚፈትን ነገር ያጋጥመናል ያኔ ሞኝነት በሚመስል የዋህነት በክርስቶስ ባለን ተስፋ በእምነት ከሰማይ ጋር እያወራን እንኖራለን

“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ፥ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል።”
— ያዕቆብ 5፥7

መልካም ቆይታ እወዳድዳችኋለሁ

https://t.me/sle_hiwot
575 views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 07:13:28 በእግዚአብሔር እጅ እንደመያዝ ምን የሚያሳርፍ ነገር አለ Wawww
አቤት የኔ አባት በወቅቱ የሚያስፈልገንን የሚያደርግ
በክፉ መንገድ እንዳንሄድ አካሄዳችንን በምክሩ ቀን ከሌት የሚያስተካክል በመልካሙ መንገድ የሚመራ ድንቅ መሪ ድንቅ አምላክ

ብዙ ሰው ሊመክረን ይችላል ..ለምሳሌ ከኛ በዕድሜ፣በት/ት ደረጃ ወዘተ ታላቅ የሆነ ወይም በምናልፍበት አይነት የህይወት መንገድ ያለፈ ሰው ይሆናልና "በዚ መንገድ ሳልፍ እንዲህና እንዲህ አጋጥሞኛልና አንተም/ቺም ሊያጋጥምህ/ሽ ይችላልና በዚህና በዚያ መልኩ እለፍ/ኑር " ወዘተረፈ ይሉናል (በእውነቱ ችግር ውስጥ ገብቶ ከመማር በችግሩ ውስጥ ካለፉት መማሩ ይሻላልና የሰዎችን ከህይወት ገጠመኝ የተነሳ ምክር መቀበል እወዳለሁ አበረታታለሁም)......._______ይህ እንዳለ ሆኖ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በሚገባን ቋንቋ በሚያስፈልገን ሰአት የሚመክር አምላክ መሆኑ ያስደንቀኛልና "እንደሱ ያለ መካሪ የታለ?" እልና ሁሌ አመሰግናለሁ ።

ከምድር ሲስተም ከፍ ያለ ደስታና ዕረፍት እንድናገኝ ከተፈለገ "አንዳንድ እግዚአብሔርን የማያውቁት እንደሚሉት ደስታና እረፍት ለናንተ ምንድነው?" ሲባሉ ይሄንና ያንን አድርጊ ወይ ሆኖልኝ አርፋለሁ or እደሰታለሁ እንደሚሉት ሳይሆን እኛ ግን ምንም አይሁን ምንም አይከሰት እንዲሁ ደስ እያለን እንኖራለን። ለምን ሲባል የኛ ነገ የኛ ስኬት የኛ ህይወት ያለቀ የተቀደመ የተፈፀመ ነው የነገ ተስፋችን የአሁንም እርግጠኝነታችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፅኑ ነው። እንደተቀደመ አውቀን መንፈስ ቅዱስን እየሰማን የምንኖረው እንጂ ለማሸነፍ የምንጣጣርበት የህይወት አይነት የለንም ።

“ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
— መዝሙር 46፥10


ኢየሱስን እየሰማን ተጉዘን መዳረሻችን ከሀሰት ሰፈር በፍፁም አይሆንም ።
መንፈስ ቅዱስ ሲመራን ወደ እውነት ነው፣ ወደ ስኬት ነው፣ ወደ ብርታት ነው ።

እሱን ይዘን የምንፀፀትበትን ህይወት አንኖርም እሱ ነግሮን አድርገን ምነው ባላደረኩት ብለን የምናዝንበት ነገር አይኖርም።


ሳይመክረን ወይ ሳይመልሰን ረፍዶበት ችግር ውስጥ ከገባን በኋላ ደርሶ ረስቻቹ ነውኮ ብሎ አያስተባብልም ። በማይገባን መልኩ ነግሮን/መክሮን ወይም ያለጊዜው የሚለውን አዘባርቆ ተናግሮ አይፀፀትም። ልጆቹን እንደሚገባ የሚቀርፅ ሙያተኛ አባት ነው ያለን

“ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።”
— ዮሐንስ 16፥13

ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
¹⁸ ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

ተስፋ የሌለን ተቅበዝባዦች መካሪና አስተማሪ የሌላቸው ሰዎች አይደለንም ብቻ እንስማው እንጂ ሁሌም በሁሉም ስፍራ በሁሉም ጊዜ አለኝታና መሪ አለን። እሱም በሁሉም ስፍራ ላይ ሁልጊዜ የሚገኘው #ኢየሱስ ነው ።

መንፈስ ቅዱስ የሚለንን አጥርተን እንድንሰማ ዘንድ ጆሮዎቻችን ንቁ ይሁኑልን ይሁንላችሁ መስማት እንድንችል ደሞ ሌሎች ቀልባችንን፣ ሀሳባችንን እና ጊዜአችንን የሚሰርቁ ድምፆች ይራቁላችሁ


ደና ቆዩልኝማ እወዳችኋለሁ

በቴሌግራም ማግኘት የምትፈልጉ ቻነሌን ተቀላቀሉ https://t.me/sle_hiwot
532 views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:11:53 ልዩነት

ባለፉት ዘመናት አባቶቻችን ከኢየሱስ ጋር ነበርን ብለው ስለራሳቸው ሳይነግሯቸው ከንግግራቸው ተነስተው ከኢየሱስ ጋር የሰነበተ እነሱነታቸውን አዩ .....በአህዛብ መካከል በልዩነት የተገለጠ ኢየሱስን ኢየሱስን የሚሸት ህይወት መኖር እንዴት ያለ በረከት ነው።

አሁንም በኛ ዘመን በእግዚአብሔር ቃልና በፀሎት የተሞላ ውሎና አዳር ሲኖረን በህልውናው ውስጥ ስንሰነብት ሰው እኛን እንደተራ ሰው ማየት አይችልም ፣ በልዩነት አለመታየት አንችልም፣ አህዛብ እኛ ጋር ሲጠጋ "እነዚህማ የዋዛ አይደሉም" ብሎ መመስከር አለበት አምላኬ እንደባለጠግነቱ በዚህ በልዩነት መንፈስ ይባርካችሁ።


ሐዋርያት 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ሰዎቹም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ እንዲህ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፣ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩም ተገነዘቡ።
¹⁴ የተፈወሰውን ሰው እዚያው ከእነርሱ ጋር ቆሞ ስላዩት የሚናገሩበትን ሰበብ አጡ።
¹⁵ ስለዚህ ከሸንጎው እንዲያወጧቸው አዘዙ፤ ከዚያም በአንድነት ተሰብስበው ተመካከሩ፤
¹⁶ እንዲህም ተባባሉ፤ “እንግዲህ እነዚህን ሰዎች ምን እናድርጋቸው? በኢየሩሳሌም የሚኖር ሁሉ በእነርሱ እጅ የተደረገውን ድንቅ ታምር ዐውቆአል፣ ስለዚህ ይህንን ማስተባበል አንችልም፤

የሚገርመውኮ በአለም እውቀትና ጥበብ ከኛ በብዙ የሚልቁ ሰዎች ይኖራሉ። ግን ያለክርስቶስ ሁሉ ባዶ ነው አንተ በክርስቶስ ባገኘኸው ማንነት በሞገስና በማስፈራት ትበልጣለህና ያንተ ትንሿ ነገር ውድ ትሆናለች ትገንናለች
በአሸናፊነት እንድንኖር ይህ በክርስቶስ ያገኘነው ማንም የማይነጥቀን ማንነት ነው።

የትም ቦታ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብቻ ኢየሱስ አብሮን ይሁን እንጂ አሸናፊ ነን ። አንገታችንን ደፍተን እየተሸማቀቅን፣ እየሰጋን፣ እያፈርን የምንኖርበት ምክንያት የለንም።

“እንግዲህ እባቡንና ጊንጡን እንድትረግጡ፣ በጠላትም ኀይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፤ የሚጐዳችሁም አንዳች ነገር አይኖርም።”
— ሉቃስ 10፥19 (አዲሱ መ.ት)

ጠላት የሚባል ነገር እንዳያገኘን ለዘለአለሙ በደሙ ተሸፍነን በድል የምንኖረው፣እንደኛ ብርታት ሳይሆን በፀጋው በምህረትና በቸርነቱ የምንኖረው የድል ህይወት እሱ ክርስትና ነው። ያልዳነም ሰው ይሄን የደስታና የእረፍት ኑሮ መኖር ስንችልና ኑሮአችንን በአይናቸው ሲያዩ ነው ከ ያሳረፈንን ጌታ ወደውና ፈቅደው መፈለግ የሚጀምሩት አለዛም ከነሱ የተለየ የድል ህይወት ከሌለን የሆነ ያልሆነው እኛን ካስጨነቀን እንደምድር ስርአት ማሰብ ጀምረን ከአለም ጋር ከተመሳሰልን ምን አይተው ይምጡ??????

በክርስቶስ የተለየን ህዝብ የምንሆንበት ፀጋ ለሁላችን ይብዛልን
ደና ቆዩልኝማ እወዳችኋለሁ

https://t.me/sle_hiwot
403 views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 07:28:57 ሳታነቡ ባታልፉ ደስ ይለኛል

ሰሞኑን ስለቅድስና በጣም እያሰብኩ ነበር..............ያሰብኩትም የማየውና የምሰማው ነገር አስደንግጦኝ ነበር

ሀጢያት እንዲህ ይለመዳል እንዴ የምልበት አጋጣሚ አጋጥሞኝ ያውቃል። ወጣት እማይደለሁ በብዛት በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ የተለያየ የሀጢአት ግብዣ ይቀርብልኛል(በርግጥ ወደው አይደለም በውስጣቸው ያለው ክፉ መንፈስ እንጂ) እነዚ ሰዎች ያሳዝኑኛል የአብዛኛው ተመሳሳይ ቢሆንም አንዳንዱ ከባህልም ከሰው መሆንም የወጣ ዝቅጠት የተሞላበት አፀያፊ ጥያቄ ከጆሮዬ ያጎርፉታል በጣም እደነግጣለሁ____ በተለይ ደሞ በጌታ ቤት እየተመላለሱ እንዲህ አይነቱ ሀሳብ ከነሱ አንደበት ሲሰማ ልብ ይሰብራል ጌታን አንዳንድ እህቶችም እንዲሁ በድፍረት ሀጢአት ውስጥ ሰምጠው ወዴት እየሄዱ እንደሁ አይታወቃቸውም

አሁን አሁን ከአህዛቡ በላይ ጴንጤው ያስፈራኛል ግን ምነው እንዲህ መርከስ ??? እግዚአብሔር እኮ የቅድስና አምላክ ነው ርኩሰት አያስደስተውም።
ዝሙት ለመስራት እንዲህ መቻኮል ራስን ለስሜት ብቻ ማስገዛት ምን አይነት ውድቀት ነው ከድርጊቱ ቀድሞ በወሬ የሚረክሰውን ቤቱ ይቁጠረው____ ጌታን እንደዚ የሀጢአትና የርኩሰት ቃላትን ያለልክ መድፈር በጣም ያስፈራል።

ያለተቀናቃኝ በነፃነት ማምለክ መቻላችን የክርስትናን እውነትና ልዩነት ካቀለለብን በባርት ቀንበር ደግመን ተይዘናል ወይም ነፃነቱ ጎድቶናል ማለት ነው!

“እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ አላቸው። እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው አሉት።”
— ዮሐንስ 8፥41

ሰው ባያይ እግዚአብሔር ያያል እኮ። የተሰወረ ሀጢአትን ሰው ባይሰማ እግዚአብሔር ይሰማዋል።

በጣም የሚያሳዝነው ደሞ ወንዱ ጴንጤ ከአህዛብ ሴቶች ጋር ሲዘሙት እነዛ ሴቶች "አልቀረም ክርስትና ኢየሱስ ከለወጠ እንትናን አይለውጠውም ነበር? እሱን ያልቀየረ እኔን አይቀይርም" ማለታቸው አይቀርም። ሴቷ ጴንጤም ከአህዛብ ወንዶች ጋር ስትዘሙት እንደዛው ነው።
በዚህ ስርአት አጥነት ውስጥ የሚከሰተው ያልተፈለገ እርግዝናስ? ማስወረዱም ነፍስ ማጥፋት ነው ወንጀልም ሀጢአትም ሆኖ ይቀመጣል ።ፀፀቱስ ቢሆን... እውነት ጌታ በዚህ ደስ ይሰኛል??? __እሺ ቀጣዩ ትውልድስ???????

የአብዛኛው ወጣት ትዳር ላይ ያለውን አቋም ስንቃኝ ደግሞ "ማግባት አልፈልግም ግን ልጅ እወልዳለሁ" የሚል ሀሳብ ነው ያላቸው ። እሺ መች የቀመሱት ትዳር ነው ያስጠላቸው? ___ገና ወጣት ሊሆን ያለ ህፃን ራሱ እንደዚሁ ይላል ጌታን ያሳዝናል እግዚአብሔር ያከበረውን ለማጣጣል ያበቃን ምን ይሆን?????? ትዳርን ጠልቶ ልጅን ማሰብ እኮ የተገለጠ ሀጢአት ነው እግዚአብሔር በዝሙት ኑሩ አላለም ከትዳር ውጪ ያለው ግንኙነት ዝሙት ስለሆነ።

ይመስለኛል ትዳር ተቃዋሚዎቹ ወጣትነታቸው ላይ ሰይጣን በሴሰኝነት ቀንበር የገዛቸው ናቸው። የዚህ አይነት አቋም ያላችሁ ሰዎች ጌታን ተስተካከሉ ልላችሁ እወዳለሁ ራስን መመርመር አይከፋም ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው አልረፈደም።

ኢየሱስን እንጂ ሀጢአትን እንድንሰብክ አልተጠራንም። በኛ የልጁ መልክ እንጂ ሀጢአት ሊገለጥ አይገባም።

“መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።”
— ማቴዎስ 5፥16

በእንደዚህ አይነት ሀሳብ የተቸገራችሁ ሰዎች እባካችሁ ተመለሱ በጌታ ቤት ሆናችሁ ድናችሁ ስታበቁ ድጋሜ ለባርነት ራሳችሁን አትስጡ ዛሬም በምንም አይነት ድካም ልትሆኑ ትችላላችሁ ኢየሱስ መድሀኒት ነው ይፈውሳችኋል ።

በዚህ ነገር የተጠመዳችሁ ሁሉ ነገሩ እንደሚስጨንቃችሁና እንደሰለቻችሁ ግልፅ ነው መፋታት አቃታችሁ እንጂ ። በዚህ አይነት ወጥመድ ውስጥ ያሉ ሰዎች ልትመክሯቸው ስትፈልጉ "ኧረ እስኪ አታስጨንቁኝ በቃ ተውኝ" ነው ሚሏችሁ እንጂ የተያዙበትን ነገር አዎ ብለው አይቀበሉም። የማይቀየር አቋምና በራስ መተማመንም የላቸውም።

ለበሽተኞች ግድ ባይለው ኖሮ መድሀኒታችን ሆኖ ባልመጣ ነበረ ! ዛሬም ይፈልጋችኋል ኢየሱስ ይወዳችኋል ያበረታችኋል

መልካም ቆይታ

እኔም በጣም እወዳችኋለሁ

https://t.me/sle_hiwot
494 views04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ