Get Mystery Box with random crypto!

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ሁሌም የእግዚአብሔርን አብሮነት ሳስብ ደስ ይለኛል። ከንቱ እንዳ | (✍ ስለ ህይወት✍)

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው

ሁሌም የእግዚአብሔርን አብሮነት ሳስብ ደስ ይለኛል። ከንቱ እንዳልሆንኩ መድረሻ እንዳለኝ ተቅበዝባዥ ብኩን እንዳልሆንኩ የያዘኝ ታማኝ እንደሆነ አስባለሁ

ዙሪያችንን ቃኝተን የሚገባን ባዶነት ብቻ ሲሆን ድቅድቁ ጨለማ ከፊታችን ተጋርጦ መራመድ ሲያቅተን የሚዳሰስና የሚጨበጥ አንዳች ነገር ባጣንበት ሀዘን በርትቶ መፅናናት ተስኖን በዚህ ሁሉ መሀል ግን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አለ።

ተስፋን የሰጠን እሱ የታመነ አምላክ ነው በዘላለም ፍቅሩ የወደደን መቼም የትም በምንም ሁኔታ የማይተወን ፣ እጃችንን የሚይዝ አብሮን የሚሆን አካል ፍለጋ ስንንከራተት ብቸኝነት ሲነግስብን ማንም የለኝም እንዳንል "አትፍሩ እኔ እስከ አለም ፍፃሜ ከእናንተ ጋር ነኝ ያለ አምላክ አለን" ኢየሱስ አይረሳንም አሁንም ይወደናል ይሄ ጌታ ይፈልገናል ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አይተወንም ኧረ እንኳንም በእጆቹ ተያዝን እንኳንም ሰበሰበን

አንዳንዴ አስባለሁ ጌታ በቤቱ ባይዘን ኖሮ እንደምናየው እና ላለመሆን እንደምንመኘው አመፀኛ ወጣት የማንሆንበት ምክንያት አልነበረም ፣ ሴሰኛና ርኩሰት የነገሰብን የምናደርገውን እያንዳንዱን ነገር ባለማስተዋል የምንፈፅም እንሆን ነበር በመንፈስ ቅዱስ ቀድሞ የገባን ፍቅር ከንቱ መሆኑን አስረድቶን ናቅነው እንጂ ፣ ሙታን ነበርን ሞታችንን በሞቱ ሽሮ ከህያዋን መንደር ቀላቀለን እንጂ። ከዚህ ሁሉ ጠብቆ በደሙ ዋጅቶ ሰው አድሮጎን ሲያበቃ መንገድ ላይ የሚጥል አምላክ አይደለም ደሞ የምን መፍራት የምን ተስፋ መቁረጥ ነው ኧረ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አለ። ምንም ውስጥ እንሁን እግዚአብሔር አለ።

ሰዎች አልተቀበሉንም ማለት እግዚአብሔር አልተቀበለንም ማለት አይደለም ፣ ማንም አይቶን እንዳላየና ሰምቶ እንዳልሰማ አልፎናል ማለት ጌታም እንደዛ ነው ማለት አይደለም።

ልቤ ብዙ ጊዜ አዝኖ ያውቃል ብዙ አልቅሼ አውቃለሁ ግን ለመልካም ሲሆንልኝና ስማርበት ሳልፈው እንጂ ሲሰብረኝ ወይም እዛው ሳለቅስ አልቀረሁም።

ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ። ነገር የተባለው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ከመኖሩ የተነሳ እኛን በአንዳች አይጎዳንም ምክንያቱም የያዘን አባታችን እሱ ልጆቹን ለየትኛውም ሁኔታ አሳልፎ የሚሰጥ ሰነፍ እረኛ አይደለም።

እግዚአብሔር በማዳኑ፣ በምህረቱ ፣በቸርነቱና በማፅናናቱ በብዙ ፍቅር አብሮን አለ። የሚያስብልን የሚጠነቀቅልን አባት አለ ያለርሱ ፈቃድ የፀጉራችን አንዷ ዘለላ እንኳን አትወድቅም

መልካም ቆይታ እወዳድዳችኋለሁ

https://t.me/sle_hiwot