Get Mystery Box with random crypto!

ሳታነቡ ባታልፉ ደስ ይለኛል ሰሞኑን ስለቅድስና በጣም እያሰብኩ ነበር..............ያሰ | (✍ ስለ ህይወት✍)

ሳታነቡ ባታልፉ ደስ ይለኛል

ሰሞኑን ስለቅድስና በጣም እያሰብኩ ነበር..............ያሰብኩትም የማየውና የምሰማው ነገር አስደንግጦኝ ነበር

ሀጢያት እንዲህ ይለመዳል እንዴ የምልበት አጋጣሚ አጋጥሞኝ ያውቃል። ወጣት እማይደለሁ በብዛት በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ የተለያየ የሀጢአት ግብዣ ይቀርብልኛል(በርግጥ ወደው አይደለም በውስጣቸው ያለው ክፉ መንፈስ እንጂ) እነዚ ሰዎች ያሳዝኑኛል የአብዛኛው ተመሳሳይ ቢሆንም አንዳንዱ ከባህልም ከሰው መሆንም የወጣ ዝቅጠት የተሞላበት አፀያፊ ጥያቄ ከጆሮዬ ያጎርፉታል በጣም እደነግጣለሁ____ በተለይ ደሞ በጌታ ቤት እየተመላለሱ እንዲህ አይነቱ ሀሳብ ከነሱ አንደበት ሲሰማ ልብ ይሰብራል ጌታን አንዳንድ እህቶችም እንዲሁ በድፍረት ሀጢአት ውስጥ ሰምጠው ወዴት እየሄዱ እንደሁ አይታወቃቸውም

አሁን አሁን ከአህዛቡ በላይ ጴንጤው ያስፈራኛል ግን ምነው እንዲህ መርከስ ??? እግዚአብሔር እኮ የቅድስና አምላክ ነው ርኩሰት አያስደስተውም።
ዝሙት ለመስራት እንዲህ መቻኮል ራስን ለስሜት ብቻ ማስገዛት ምን አይነት ውድቀት ነው ከድርጊቱ ቀድሞ በወሬ የሚረክሰውን ቤቱ ይቁጠረው____ ጌታን እንደዚ የሀጢአትና የርኩሰት ቃላትን ያለልክ መድፈር በጣም ያስፈራል።

ያለተቀናቃኝ በነፃነት ማምለክ መቻላችን የክርስትናን እውነትና ልዩነት ካቀለለብን በባርት ቀንበር ደግመን ተይዘናል ወይም ነፃነቱ ጎድቶናል ማለት ነው!

“እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ አላቸው። እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው አሉት።”
— ዮሐንስ 8፥41

ሰው ባያይ እግዚአብሔር ያያል እኮ። የተሰወረ ሀጢአትን ሰው ባይሰማ እግዚአብሔር ይሰማዋል።

በጣም የሚያሳዝነው ደሞ ወንዱ ጴንጤ ከአህዛብ ሴቶች ጋር ሲዘሙት እነዛ ሴቶች "አልቀረም ክርስትና ኢየሱስ ከለወጠ እንትናን አይለውጠውም ነበር? እሱን ያልቀየረ እኔን አይቀይርም" ማለታቸው አይቀርም። ሴቷ ጴንጤም ከአህዛብ ወንዶች ጋር ስትዘሙት እንደዛው ነው።
በዚህ ስርአት አጥነት ውስጥ የሚከሰተው ያልተፈለገ እርግዝናስ? ማስወረዱም ነፍስ ማጥፋት ነው ወንጀልም ሀጢአትም ሆኖ ይቀመጣል ።ፀፀቱስ ቢሆን... እውነት ጌታ በዚህ ደስ ይሰኛል??? __እሺ ቀጣዩ ትውልድስ???????

የአብዛኛው ወጣት ትዳር ላይ ያለውን አቋም ስንቃኝ ደግሞ "ማግባት አልፈልግም ግን ልጅ እወልዳለሁ" የሚል ሀሳብ ነው ያላቸው ። እሺ መች የቀመሱት ትዳር ነው ያስጠላቸው? ___ገና ወጣት ሊሆን ያለ ህፃን ራሱ እንደዚሁ ይላል ጌታን ያሳዝናል እግዚአብሔር ያከበረውን ለማጣጣል ያበቃን ምን ይሆን?????? ትዳርን ጠልቶ ልጅን ማሰብ እኮ የተገለጠ ሀጢአት ነው እግዚአብሔር በዝሙት ኑሩ አላለም ከትዳር ውጪ ያለው ግንኙነት ዝሙት ስለሆነ።

ይመስለኛል ትዳር ተቃዋሚዎቹ ወጣትነታቸው ላይ ሰይጣን በሴሰኝነት ቀንበር የገዛቸው ናቸው። የዚህ አይነት አቋም ያላችሁ ሰዎች ጌታን ተስተካከሉ ልላችሁ እወዳለሁ ራስን መመርመር አይከፋም ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው አልረፈደም።

ኢየሱስን እንጂ ሀጢአትን እንድንሰብክ አልተጠራንም። በኛ የልጁ መልክ እንጂ ሀጢአት ሊገለጥ አይገባም።

“መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።”
— ማቴዎስ 5፥16

በእንደዚህ አይነት ሀሳብ የተቸገራችሁ ሰዎች እባካችሁ ተመለሱ በጌታ ቤት ሆናችሁ ድናችሁ ስታበቁ ድጋሜ ለባርነት ራሳችሁን አትስጡ ዛሬም በምንም አይነት ድካም ልትሆኑ ትችላላችሁ ኢየሱስ መድሀኒት ነው ይፈውሳችኋል ።

በዚህ ነገር የተጠመዳችሁ ሁሉ ነገሩ እንደሚስጨንቃችሁና እንደሰለቻችሁ ግልፅ ነው መፋታት አቃታችሁ እንጂ ። በዚህ አይነት ወጥመድ ውስጥ ያሉ ሰዎች ልትመክሯቸው ስትፈልጉ "ኧረ እስኪ አታስጨንቁኝ በቃ ተውኝ" ነው ሚሏችሁ እንጂ የተያዙበትን ነገር አዎ ብለው አይቀበሉም። የማይቀየር አቋምና በራስ መተማመንም የላቸውም።

ለበሽተኞች ግድ ባይለው ኖሮ መድሀኒታችን ሆኖ ባልመጣ ነበረ ! ዛሬም ይፈልጋችኋል ኢየሱስ ይወዳችኋል ያበረታችኋል

መልካም ቆይታ

እኔም በጣም እወዳችኋለሁ

https://t.me/sle_hiwot