Get Mystery Box with random crypto!

ልዩነት ባለፉት ዘመናት አባቶቻችን ከኢየሱስ ጋር ነበርን ብለው ስለራሳቸው ሳይነግሯቸው ከንግግራ | (✍ ስለ ህይወት✍)

ልዩነት

ባለፉት ዘመናት አባቶቻችን ከኢየሱስ ጋር ነበርን ብለው ስለራሳቸው ሳይነግሯቸው ከንግግራቸው ተነስተው ከኢየሱስ ጋር የሰነበተ እነሱነታቸውን አዩ .....በአህዛብ መካከል በልዩነት የተገለጠ ኢየሱስን ኢየሱስን የሚሸት ህይወት መኖር እንዴት ያለ በረከት ነው።

አሁንም በኛ ዘመን በእግዚአብሔር ቃልና በፀሎት የተሞላ ውሎና አዳር ሲኖረን በህልውናው ውስጥ ስንሰነብት ሰው እኛን እንደተራ ሰው ማየት አይችልም ፣ በልዩነት አለመታየት አንችልም፣ አህዛብ እኛ ጋር ሲጠጋ "እነዚህማ የዋዛ አይደሉም" ብሎ መመስከር አለበት አምላኬ እንደባለጠግነቱ በዚህ በልዩነት መንፈስ ይባርካችሁ።


ሐዋርያት 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ሰዎቹም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ እንዲህ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፣ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩም ተገነዘቡ።
¹⁴ የተፈወሰውን ሰው እዚያው ከእነርሱ ጋር ቆሞ ስላዩት የሚናገሩበትን ሰበብ አጡ።
¹⁵ ስለዚህ ከሸንጎው እንዲያወጧቸው አዘዙ፤ ከዚያም በአንድነት ተሰብስበው ተመካከሩ፤
¹⁶ እንዲህም ተባባሉ፤ “እንግዲህ እነዚህን ሰዎች ምን እናድርጋቸው? በኢየሩሳሌም የሚኖር ሁሉ በእነርሱ እጅ የተደረገውን ድንቅ ታምር ዐውቆአል፣ ስለዚህ ይህንን ማስተባበል አንችልም፤

የሚገርመውኮ በአለም እውቀትና ጥበብ ከኛ በብዙ የሚልቁ ሰዎች ይኖራሉ። ግን ያለክርስቶስ ሁሉ ባዶ ነው አንተ በክርስቶስ ባገኘኸው ማንነት በሞገስና በማስፈራት ትበልጣለህና ያንተ ትንሿ ነገር ውድ ትሆናለች ትገንናለች
በአሸናፊነት እንድንኖር ይህ በክርስቶስ ያገኘነው ማንም የማይነጥቀን ማንነት ነው።

የትም ቦታ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብቻ ኢየሱስ አብሮን ይሁን እንጂ አሸናፊ ነን ። አንገታችንን ደፍተን እየተሸማቀቅን፣ እየሰጋን፣ እያፈርን የምንኖርበት ምክንያት የለንም።

“እንግዲህ እባቡንና ጊንጡን እንድትረግጡ፣ በጠላትም ኀይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፤ የሚጐዳችሁም አንዳች ነገር አይኖርም።”
— ሉቃስ 10፥19 (አዲሱ መ.ት)

ጠላት የሚባል ነገር እንዳያገኘን ለዘለአለሙ በደሙ ተሸፍነን በድል የምንኖረው፣እንደኛ ብርታት ሳይሆን በፀጋው በምህረትና በቸርነቱ የምንኖረው የድል ህይወት እሱ ክርስትና ነው። ያልዳነም ሰው ይሄን የደስታና የእረፍት ኑሮ መኖር ስንችልና ኑሮአችንን በአይናቸው ሲያዩ ነው ከ ያሳረፈንን ጌታ ወደውና ፈቅደው መፈለግ የሚጀምሩት አለዛም ከነሱ የተለየ የድል ህይወት ከሌለን የሆነ ያልሆነው እኛን ካስጨነቀን እንደምድር ስርአት ማሰብ ጀምረን ከአለም ጋር ከተመሳሰልን ምን አይተው ይምጡ??????

በክርስቶስ የተለየን ህዝብ የምንሆንበት ፀጋ ለሁላችን ይብዛልን
ደና ቆዩልኝማ እወዳችኋለሁ

https://t.me/sle_hiwot