Get Mystery Box with random crypto!

በእግዚአብሔር እጅ እንደመያዝ ምን የሚያሳርፍ ነገር አለ Wawww አቤት የኔ አባት በወቅቱ የሚ | (✍ ስለ ህይወት✍)

በእግዚአብሔር እጅ እንደመያዝ ምን የሚያሳርፍ ነገር አለ Wawww
አቤት የኔ አባት በወቅቱ የሚያስፈልገንን የሚያደርግ
በክፉ መንገድ እንዳንሄድ አካሄዳችንን በምክሩ ቀን ከሌት የሚያስተካክል በመልካሙ መንገድ የሚመራ ድንቅ መሪ ድንቅ አምላክ

ብዙ ሰው ሊመክረን ይችላል ..ለምሳሌ ከኛ በዕድሜ፣በት/ት ደረጃ ወዘተ ታላቅ የሆነ ወይም በምናልፍበት አይነት የህይወት መንገድ ያለፈ ሰው ይሆናልና "በዚ መንገድ ሳልፍ እንዲህና እንዲህ አጋጥሞኛልና አንተም/ቺም ሊያጋጥምህ/ሽ ይችላልና በዚህና በዚያ መልኩ እለፍ/ኑር " ወዘተረፈ ይሉናል (በእውነቱ ችግር ውስጥ ገብቶ ከመማር በችግሩ ውስጥ ካለፉት መማሩ ይሻላልና የሰዎችን ከህይወት ገጠመኝ የተነሳ ምክር መቀበል እወዳለሁ አበረታታለሁም)......._______ይህ እንዳለ ሆኖ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በሚገባን ቋንቋ በሚያስፈልገን ሰአት የሚመክር አምላክ መሆኑ ያስደንቀኛልና "እንደሱ ያለ መካሪ የታለ?" እልና ሁሌ አመሰግናለሁ ።

ከምድር ሲስተም ከፍ ያለ ደስታና ዕረፍት እንድናገኝ ከተፈለገ "አንዳንድ እግዚአብሔርን የማያውቁት እንደሚሉት ደስታና እረፍት ለናንተ ምንድነው?" ሲባሉ ይሄንና ያንን አድርጊ ወይ ሆኖልኝ አርፋለሁ or እደሰታለሁ እንደሚሉት ሳይሆን እኛ ግን ምንም አይሁን ምንም አይከሰት እንዲሁ ደስ እያለን እንኖራለን። ለምን ሲባል የኛ ነገ የኛ ስኬት የኛ ህይወት ያለቀ የተቀደመ የተፈፀመ ነው የነገ ተስፋችን የአሁንም እርግጠኝነታችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፅኑ ነው። እንደተቀደመ አውቀን መንፈስ ቅዱስን እየሰማን የምንኖረው እንጂ ለማሸነፍ የምንጣጣርበት የህይወት አይነት የለንም ።

“ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
— መዝሙር 46፥10


ኢየሱስን እየሰማን ተጉዘን መዳረሻችን ከሀሰት ሰፈር በፍፁም አይሆንም ።
መንፈስ ቅዱስ ሲመራን ወደ እውነት ነው፣ ወደ ስኬት ነው፣ ወደ ብርታት ነው ።

እሱን ይዘን የምንፀፀትበትን ህይወት አንኖርም እሱ ነግሮን አድርገን ምነው ባላደረኩት ብለን የምናዝንበት ነገር አይኖርም።


ሳይመክረን ወይ ሳይመልሰን ረፍዶበት ችግር ውስጥ ከገባን በኋላ ደርሶ ረስቻቹ ነውኮ ብሎ አያስተባብልም ። በማይገባን መልኩ ነግሮን/መክሮን ወይም ያለጊዜው የሚለውን አዘባርቆ ተናግሮ አይፀፀትም። ልጆቹን እንደሚገባ የሚቀርፅ ሙያተኛ አባት ነው ያለን

“ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።”
— ዮሐንስ 16፥13

ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
¹⁸ ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

ተስፋ የሌለን ተቅበዝባዦች መካሪና አስተማሪ የሌላቸው ሰዎች አይደለንም ብቻ እንስማው እንጂ ሁሌም በሁሉም ስፍራ በሁሉም ጊዜ አለኝታና መሪ አለን። እሱም በሁሉም ስፍራ ላይ ሁልጊዜ የሚገኘው #ኢየሱስ ነው ።

መንፈስ ቅዱስ የሚለንን አጥርተን እንድንሰማ ዘንድ ጆሮዎቻችን ንቁ ይሁኑልን ይሁንላችሁ መስማት እንድንችል ደሞ ሌሎች ቀልባችንን፣ ሀሳባችንን እና ጊዜአችንን የሚሰርቁ ድምፆች ይራቁላችሁ


ደና ቆዩልኝማ እወዳችኋለሁ

በቴሌግራም ማግኘት የምትፈልጉ ቻነሌን ተቀላቀሉ https://t.me/sle_hiwot