Get Mystery Box with random crypto!

የህሊና ፀፀት የማያስከትለውን ራስንም ሰውንም የማይጎዳውን የዋህነት የተሞላበትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ | (✍ ስለ ህይወት✍)

የህሊና ፀፀት የማያስከትለውን ራስንም ሰውንም የማይጎዳውን የዋህነት የተሞላበትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖር ትልቅ ነገር እንደሆነ አስባለሁ

በህይወት መንገዳችን ብዙ አይነት ሰዎች ያጋጥሙናል፤ አንዳንዶቹ "ምርጥ ሰው ማለት እንዲህ ነው" የሚያስብሉ ሲሆኑ፤አንዳንዶች ደሞ በተቃራኒው የሰው ፍጥረት የተባለ እንድንጠላ እይታችን ላይ መጥፎ ተፅዕኖ ያሳድራሉ

በዚህ ሁሉ ስናልፍ ግን እንዲህ ብናስብ መልካም ነው:- "ማንም ምንም ሊሆን ይችላል ምንም ሊያደርግ ይችላል ከሰው ጋር በህብረት መኖር አማራጭ የሌለው ምርጫችን፣ አምላክ የሰጠን መርህና የህይወት ክፍላችን ዋነኛው ተግባር ነው" ስለዚህ የህሊና ፀፀት የማያስከትለውን ራስንም ሰውንም የማይጎዳውን የዋህነት የተሞላበትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንድንኖር ፀጋው ለሁላችን ይብዛ። በፍፁም የዋህነትና ብልህነት በብዙ ሰላም መኖር ይሁንልን

“ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።”
— ገላትያ 6፥9

Maybe አጋጥሟችሁ ከሆነ አላውቅም ግን ክርስቶስን በእኛ ለማሳየት(ሰዎች እኛን አይተው የልጁን መልክ እንዲያዩ )ካለን ረሀብ የተነሳ ክርስቶስን ለመምሰል ዳዴ በምንልበት የህይወት መንገድ ለመልካም ያሰብነው ለክፉ ተተርጉሞብን ልንደነግጥ እንችላለን፣ እየቆሰልን እንስቃለን እያስቀየሙን ነገሩን አቅልለነው እናልፋለን፣ በብልጣብልጥነት እያታለሉን or እየዋሹን እያወቅነው ለነገሩም ሰውኛ ምላሽ መስጠት እየቻልን በሞኝነት ዝም ብለን ልናልፍ እንችላለን። ያን ጊዜ እነ እከሌም ማጭበርበሩን ይጨምራሉ በዚያ ሰአት ጌታ ትዕግስቱን ካልሰጠን እኛም ከነሱ የባስን ተንኮለኞች የምንሆንበት እድል ሰፊ ነው። ፀጋው ይርዳን

አንዳንዴ "ጌታ ሆይ እኔ በፈለኩትና ይመቻል ባልኩት መንገድ ሄጄ አንተን ደስ ከማያሰኝ ነገር ጋር እንዳልቀጥል እና አንተ በኔ እንዲሆን ከፈለከው ነገር ጋር እንዳልተላለፍ አደራ" ብለን እየፀለይን ፀሎታችንን የሚፈትን ነገር ያጋጥመናል ያኔ ሞኝነት በሚመስል የዋህነት በክርስቶስ ባለን ተስፋ በእምነት ከሰማይ ጋር እያወራን እንኖራለን

“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ፥ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል።”
— ያዕቆብ 5፥7

መልካም ቆይታ እወዳድዳችኋለሁ

https://t.me/sle_hiwot