2022-04-10 21:07:45
"1ሚሊየን ብር ስጪኝና ጴንጤ እሆናለሁ" ቢለኝ ብዙ ነገር አሰብኩኝ
_እውነት እንደው ማስተዋል ቢያቅተው እንጂ ስንትና ስንት ቢልዮን ዶላር ቢሰበሰብ የማይከፍለውን እዳውን ኢየሱስ ራሱን መስዋዕት አድርጎ ነፍሱን ያዳነለት ጌታ ቅራቅንቦ ብር ይቸግረዋል ብሎ ማሰቡ አይገርምም
አረ ተው ግድ የለህም ኢየሱስ በአንዳንድ ነገሮች አይጠረጠርም እሱን በገንዘብ አትተምነው ራሱን ሰጥቶህ የለ እንዴ እንኳን በአይን የሚታየውን ኮተት
ስማኝማክ ነፍሱን የሰጠህ ጌታ ፣ያኖረህ ጌታ እንዴት ሌላውን ይነፍግሀል ሁሉ በኢየሱስ እኮ ሙሉ ነው
የምድር ባለጠጎች ሀብታቸው ቢሰበሰብ የነፍሳችንን እዳ መክፈል ችሎ የዘላለም ህይወትና እረፍት አይሰጠንም ።
ማቴዎስ 6 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ስለዚህ፣ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤
³² አሕዛብ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለማግኘት ይጨነቃሉና፤ የሰማዩ አባታችሁም እነዚህ ሁሉ ለእናንተ እንደሚያ ስፈልጓችሁ ያውቃል።
³³ ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እሹ፤ እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል።
አትጨናነቅ ወዳጄ ሚስጥሩን ብትረዳው ይሻልሀል
ኢየሱስን በፈቃዳችን ወደህይወታችን ስናስገባ ግን ሁሉም አለን። የጎደለ ነገር በእግዚአብሔር አለም የለም ። "ብቻ ፅድቅና መንግስቱን ፈልጉ እንጂ ሌላው ይጨመርላችኋል " ይል የለ ቅዱስ ቃሉ በቃ እሱን ብቻ ይዞ መቀጠል ነው ሌላው አያሳስብም
ግን አንድ እውነት አለ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁ በነፃ የዘላለም ህይወትን አግኝተናል ይህ ዕረፍት ለተቀበሉት ሁሉ በስሙም ለሚያምኑት እንዲሁ በነፃ ተሰጥቷል
የእግዚአብሔር ማዳን አያልቅም ኢየሱስ የሞተው ዋጋ የከፈለው ለአለም ሁሉ ነው ለኔም ላንተም ለእናንተም ኢየሱስ ሞቶልናል በትንሳኤውም ሞትን ድል አድርጎ ሲነሳ የኛን ሞት ነው የሻረው
እኛ የምንም እዳ የለብንም በሞቱ ሞትን አሸንፈናል በስጋ ስናንቀላፋ የተዘጋጀልን ያማረ ቤት በሰማይ አለ በምድርም የሚያሳስበን አንዳች ነገር የለም ሁሉም ተፈፅሟል ህይወታችን የደስታ ነው
በሚያስጨንቀው አለም ውስጥ ሆነን ግን በውስጣችን ባለው ኢየሱስ በብዙ ዕረፍትና ስኬት እንኖራለን
የጨለምተኝነት ህይወት የለንም እንደውም እናንተ የአለም ብርሀን ናችሁ ተብለናል እናበራለን እንጂ አይጨልምብንም።
ብርሀንን የሚያሸንፍ ጨለማ የለምና በአሸናፊነት እንመላለስ ዘንድ በክርስቶስ የተሰጠን ማንነት የፈካ ነው።
ጌታ ይወዳችኋል እኔም እወዳድዳችኋለሁ ደህና ቆዩልኝማ
@sle_hiwot @sle_hiwot
@sle_hiwot @sle_hiwot
415 views18:07