Get Mystery Box with random crypto!

ከሩህ...

የቴሌግራም ቻናል አርማ shefaa12 — ከሩህ...
የቴሌግራም ቻናል አርማ shefaa12 — ከሩህ...
የሰርጥ አድራሻ: @shefaa12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136
የሰርጥ መግለጫ

<<የቀንህ ውብነት የሚለካው ወደ አሏህ በቀረብከው ልክ ነው>>

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-30 06:48:55 Abx

አሥሩ የዚል-ሒጃ ቀናት
***
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ
****
አላህ ሲያስብልን፣ ሲወደን እና ሊጠቅመን ሲፈልግ ምንዳዉና ችሮታው የሚነባበርባቸዉን ቀናትና ጊዜያት ጠቆመን፡፡
አስተዋይ ልቦና የሠጠው ሰው በትኩረት ይጠቀምባቸዋል፡፡ እንደዋዛ አያሳልፋቸዉም፡፡

አሥሩ ምርጥ ቀናት ነገ ሀሙስ ይጀምራሉ፡፡ ስለ ምርጥነታቸው በቁርኣን ተመስክሮላቸዋል፣ አላህ ምሎባቸዋል፣ የአላህን ቤት ጎብኝዎች ወደተከበረዉና የተቀደስው ሥፍራ መካ እና ዙርያው በመጉረፍ የሐጅን ሥርዓት ያከናዉኑባቸዋል፡፡

በቀናቱ ዉስጥ ምን መሥራት እንችላለን?
1- ከልብ ተፀፅቶ ወደ አላህ መመለስ፤
2- አላህን ማውሳት ማብዛት፣
3- መፆም፣
4- ኢስቲግፋር ማብዛት፣
5- መመጽወት
6- ዱዓእ ማድረግ፣
7- ሶላትን በወቅቱ መስገድ፣
8- ከኃጢኣት መራቅ፣
9- ስለ ቀናቱ ምርጥነትና እንዲጠቀሙባቸው ሌሎችን ማስታወስ፣
10- በነቢዩ ላይ ሶላዋት ማውረድ፣
11- መልካም ሥራዎችና ንግግሮች ለምሳሌ - ወደ አላህ መንገድ መጣራት፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ለጎረቤት መልካም መዋል፣ ወላጆችን ማስደሰት፣ አስቸጋሪን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ፣ የታመሙትን መጎብኘት፣ ለሙታን ዱዓ ማድረግ፣ ወንድም እህቶችን በሌሉበት በዱዓ ማስታወስ፣ የባለዕዳን ዕዳ መሰረዝ፣ የተቸገረን መርዳት፣ የታሠረን መጠየቅ፣ ሰዎችን አለማስቸገር፣ ቤተሰብን መንከባከብ፣ ለሠራተኞች ማዘን ...ሌሎችም ።

@shefaa12
29 viewshau:), 03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 05:27:09 ሞልታ የነበረችው ጨረቃ እየጎደለች ሄዳ ከጨረቃዋ ማለቅ ጋር ረመዷንም ያልቃል። ደጋጎቹ የረመዷን ቀናት በጎደሉ ቁጥር በዒባዳ ብርታታቸው ያይል ነበር።

ረመዷን ዉድድር ነው። እኛ ደግሞ ለዉድድር የተለቀቅን ባሮቹ ነን። ትንፋሽ ሰብስቦ ፍፃሜን ለማሳመር መታገል አሁን ነው ወዳጄ።

አሏህ የሚቆጠሩ ቀናት አላቸዉ እዉነትም የሚቆጠሩ ጥቂት ቀናት ሄዱኮ በረቢ
ፍጠኑ ረመዷን እየፈጠነ ነው# እንደ በድር ድል ይሳካላችሁ።

@shefaa12
89 viewshau:), edited  02:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 12:20:23 ✿.。.:* ☆::. ✿.。.:* ☆::. ✿.。.:* ☆::. ✿

لا تنظر الى صغر الخطيئة ، و لكن انظر الى عظم من عصيت .
–ابن تيمية رحمه الله

<<የኃጢያትህን ትንሽነት ሳይሆን ያልታዘዝከውን አሏህ ታላቅነት ተመልከት>>.


✿.。.:* ☆::. ✿.。.:* ☆::. ✿.。.:* ☆::. ✿


@shefaa12
103 viewshau:), 09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 10:41:03 "በረካ" 8
(ነጃት ሀሰን)
:
ብናመሰግን እንደሚጨመርልን በዘላለማዊ ቃሉ ተላልፎልናል። በረካው በሽኩር!
የኛ ነገር ማመስገኛ ያጣን ይመስል ንፃሬ ውስጥ የሚገባ ነገር ካላገኘን ማመስገን ያለብን ሁሉ አይመስለንም እንጂ በኛ ላይ ስለፈሰሰው በረካ ሁሉ በእስትንፋሳችን ልክ ብናመሰግን ከፍለን ባልጨረስነው ነበር። ባለንበት ሀል ሁሉ <አልሐምዱሊላህ> ከሊሳናችን ባይጠፋ፡ እውን እየኖርን ያለውን የጥበት ሀያት እንኖር ነበር? ማማረር ለአንደበታችን እንዲህ ይገራ ነበር?

አልሐምዱሊላህ...ትዝታ ሁነው ስላለፉልን መጥፎ ለመሰሉን ወቅቶች!
አልሐምዱሊላህ... አሁን እየተጋፈጥናቸው ላሉ ከአለት የባሱ ስለመሰሉን የዱንያ ፈተናዎች!
አልሐምዱሊላህ... በአልሐምዱሊላሃችን በረካው ስለሚጎርፍብን!
አልሐምዱሊላህ... አልሐምዱሊላህ ማለትን ስላስቻለን!
በበረካው!

@shefaa12
97 viewshau:), 07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 10:32:15 ረመዷን
(8)
**
ሰዎች ድምፃችንን ይሰማሉ፣ አንተ ግን ዉስጣችንን ትሰማለህ።
የልባችንን ለቅሶ የምትሰማ፣ የዉስጣችን መሻት የምታውቅ አሏሀች ን ሆይ! በፆመ አንጀታችን ለመንንህ፣ በደረቅ ጎሮሮኣችን ተማፀንንህ። መሻታችንን ሁሉ ሙላልን፣ ሓጃችንን ሁሉ ፈጽምልን፣ የምንፈልገዉን ሁሉ ስጠን።
ያ ረብ!

@shefaa12
70 viewshau:), edited  07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 19:46:18 ጾም ነፍስን ለመቆጣጠርና አቅጣጫ ለማሳየት ግዙፉ መንገድ ነው። ነፍስ ወደ አላህ የሚደረገው ጉዞ ላይ መሰናክል የምትሆነው ክፉ ስትሆን ነው። በባሕሪዋ ደግሞ ደስ የሚላትን ማድረግና ግዴታ ከተደረጉባት ተግባራት መሸሽ ትመርጣለች። ይህን ባሕሪዋን ለማረም ደግሞ ጾም ምርጡ አምልኮ ነው። በዚህ መንገድ መጠቀም የፈለግን እንደሆነ በጾሙ ክፍለ ጊዜ አብዛኛውን በእንቅልፍ ልናሳልፈው አይገባም። ስናፈጥርም የምንወስዳቸውን ምግቦችና መጠጦች ማመጣጠን ይኖርብናል። የምግብ ዓይነታዎችንም ማብዛት ተገቢ አይደለም። አንድ ወይም ሁለት ዓይነት በቂያችን ነው።
አል-ሐሊሚይ እንዲህ ይላሉ፦ ‹‹ሐላል ስለሆነ ብቻ ለአንድ ሰው አብዝቶ መመገቡ ትክክል አይደለም። ምግብ በብዛቱ ሰውነቱን ይከብደዋል፤ ወደ እንቅልፍ ይገፋዋል፤ አምልኮ ይከለክለዋል። ስለዚህ ረሐቡን በሚያስረሳ ሁኔታ ይመገብ። የሚመገብበትን ዓላማም በአምልኮ ለመበርታትና ለመጠናከር ይሁን።›› ሹዐብ አል-ኢማን አልበይሀቂ 5/22

ከምግብና ከመጠጥ ከመጾም በተጨማሪ ከማይጠቅሙ ንግግሮች መጾም ይገባናል። ‹‹ምላስህን ያዝ!›› መፈክራች ሆኖ ከአላስፈላጊና ካልተፈቀዱልን ነገሮች ሁሉ በተቻለን አቅም እንጠበቅ።

አሏህ በብዙ ከሚያተርፋት ያድርገን

@shefaa12
66 viewshau:), 16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 23:14:47
በቁርአን የምንዋብበት ሳምንት ይሁንልን!
ኸይሩን የምንሰማበት፤
ደጉን ምናገኝበት ።

@Shefaa12
63 viewsMame , 20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 13:21:04 አንዳንድ ሰዎች ሁኔታቸዉን ስናይ ብቻ የረመዷንን መግባት የሚጠቁሙን አሉ።
ስታስተዉላቸው እንዲሁ ፆመኞች መሆናቸዉን ታውቃለህ፣ አላህ የሠጣቸዉን ዕድል ለመጠቀም ከወትሮ ለየት ባለ ሁኔታ ወደ መልካም ነገር ይሽቀዳደማሉ፣ ፆምን ፆም ያስመስላሉ፣ በዒባዳ ዉለው ያድራሉ፣ ቁርኣን አብዝተው ያነባሉ፣ ዚክር ላይ ይበረታሉ፣ ሶደቃ በፍቅር ይሰጣሉ፣ ከትርፍ ንግግር ይቆጠባሉ ።

አንዳንዶች ደግሞ አሉ። በረመዷንም ሆነ ከረመዷን ዉጭ ያው ናቸው። ምንም የተለወጠ አይመስላቸዉም፣ ጊዜያትም ሆነ ወራት እነርሱ ዘንድ ልዩነት የላቸው፣ በፊት ክፉ ናቸው አሁንም ክፋታቸዉን አልተዉም፣ በፊትም ይሳደባሉ አሁንም ይሳደባሉ፣ በፊትም ይዋሻሉ አሁንም ይዋሻሉ፣ በፊትም ያማሉ አሁንም ያማሉ፣ በፊትም ጊዜያቸዉን በከንቱ ያጠፋሉ አሁንም እዚያው አሉ።

አላህ የቀናትን ልዩነት ያሳውቀን። በአግባቡ ከሚጠቀሙባቸውም ያድርገን

ረመዳኑኩም ሙባረክ

@shefaa12
71 viewshau:), 10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 23:19:29 ተራዊሕ - 1

ወሩ የሑፋዞች ነው። የአላህን ቃል በማንበብ ወሩን ሙሉ በረመዷን ምሽቶች ላይ ይነግሳሉ። ሰማይ ምድሩን በማራኪ ድምፆቻቸው ያዉዳሉ። ሰዎች የአላህን ቃል ይወዱ ዘንድ ሰበብ ይሆናሉ። ምንኛ ታደሉ በረቢ።

ሑፋዞች ልዩ የአላህ ሰዎች ናቸው። አላህ ከሰዎች አስበልጦ ሰዎች ፊት አቆማቸው። የሚሕራብ ንጉሶች አደረጋቸው። ይህም በርግጥ የአላህ ችሮታ ነው። እሱም ችሮታዉን ለሻው ሰው ይሠጣል። "የኽተሱ ቢረህመቲሂ መን የሻኡ።"
ልጅህን ቁርአን ስታስተምረው ፣ በተራው ቁርኣን ደግሞ ልጅህን ያስተምርልሃል።

የቁርኣን ወር
ረመዳኑኩም ሙባረክ

ለዚህ ትልቅ ኒእማ ያደረሠን አሏህ በብዙ.. ምስጋና ይገባው


@shefaa12
93 viewshau:), edited  20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 22:31:14 'እንዴት ነህ?' ባሉህ ጊዜ
'አልሐምዱ ሊላህ ትልቅ ኒዕማ ዉስጥ ነኝ' ያልክ እንደሆነ ትልቅ ኒዕማ እንደሚፈስልህ አትጠራጠር ።
በምንም ዉስጥ ሁን በምን፤አሏህን አብዝተህ አመስግን።


@shefaa12
103 viewshau:), edited  19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ