Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ሰዎች ሁኔታቸዉን ስናይ ብቻ የረመዷንን መግባት የሚጠቁሙን አሉ። ስታስተዉላቸው እንዲሁ | ከሩህ...

አንዳንድ ሰዎች ሁኔታቸዉን ስናይ ብቻ የረመዷንን መግባት የሚጠቁሙን አሉ።
ስታስተዉላቸው እንዲሁ ፆመኞች መሆናቸዉን ታውቃለህ፣ አላህ የሠጣቸዉን ዕድል ለመጠቀም ከወትሮ ለየት ባለ ሁኔታ ወደ መልካም ነገር ይሽቀዳደማሉ፣ ፆምን ፆም ያስመስላሉ፣ በዒባዳ ዉለው ያድራሉ፣ ቁርኣን አብዝተው ያነባሉ፣ ዚክር ላይ ይበረታሉ፣ ሶደቃ በፍቅር ይሰጣሉ፣ ከትርፍ ንግግር ይቆጠባሉ ።

አንዳንዶች ደግሞ አሉ። በረመዷንም ሆነ ከረመዷን ዉጭ ያው ናቸው። ምንም የተለወጠ አይመስላቸዉም፣ ጊዜያትም ሆነ ወራት እነርሱ ዘንድ ልዩነት የላቸው፣ በፊት ክፉ ናቸው አሁንም ክፋታቸዉን አልተዉም፣ በፊትም ይሳደባሉ አሁንም ይሳደባሉ፣ በፊትም ይዋሻሉ አሁንም ይዋሻሉ፣ በፊትም ያማሉ አሁንም ያማሉ፣ በፊትም ጊዜያቸዉን በከንቱ ያጠፋሉ አሁንም እዚያው አሉ።

አላህ የቀናትን ልዩነት ያሳውቀን። በአግባቡ ከሚጠቀሙባቸውም ያድርገን

ረመዳኑኩም ሙባረክ

@shefaa12