Get Mystery Box with random crypto!

ተራዊሕ - 1 ወሩ የሑፋዞች ነው። የአላህን ቃል በማንበብ ወሩን ሙሉ በረመዷን ምሽቶች ላይ ይነ | ከሩህ...

ተራዊሕ - 1

ወሩ የሑፋዞች ነው። የአላህን ቃል በማንበብ ወሩን ሙሉ በረመዷን ምሽቶች ላይ ይነግሳሉ። ሰማይ ምድሩን በማራኪ ድምፆቻቸው ያዉዳሉ። ሰዎች የአላህን ቃል ይወዱ ዘንድ ሰበብ ይሆናሉ። ምንኛ ታደሉ በረቢ።

ሑፋዞች ልዩ የአላህ ሰዎች ናቸው። አላህ ከሰዎች አስበልጦ ሰዎች ፊት አቆማቸው። የሚሕራብ ንጉሶች አደረጋቸው። ይህም በርግጥ የአላህ ችሮታ ነው። እሱም ችሮታዉን ለሻው ሰው ይሠጣል። "የኽተሱ ቢረህመቲሂ መን የሻኡ።"
ልጅህን ቁርአን ስታስተምረው ፣ በተራው ቁርኣን ደግሞ ልጅህን ያስተምርልሃል።

የቁርኣን ወር
ረመዳኑኩም ሙባረክ

ለዚህ ትልቅ ኒእማ ያደረሠን አሏህ በብዙ.. ምስጋና ይገባው


@shefaa12