Get Mystery Box with random crypto!

ጾም ነፍስን ለመቆጣጠርና አቅጣጫ ለማሳየት ግዙፉ መንገድ ነው። ነፍስ ወደ አላህ የሚደረገው ጉዞ ላ | ከሩህ...

ጾም ነፍስን ለመቆጣጠርና አቅጣጫ ለማሳየት ግዙፉ መንገድ ነው። ነፍስ ወደ አላህ የሚደረገው ጉዞ ላይ መሰናክል የምትሆነው ክፉ ስትሆን ነው። በባሕሪዋ ደግሞ ደስ የሚላትን ማድረግና ግዴታ ከተደረጉባት ተግባራት መሸሽ ትመርጣለች። ይህን ባሕሪዋን ለማረም ደግሞ ጾም ምርጡ አምልኮ ነው። በዚህ መንገድ መጠቀም የፈለግን እንደሆነ በጾሙ ክፍለ ጊዜ አብዛኛውን በእንቅልፍ ልናሳልፈው አይገባም። ስናፈጥርም የምንወስዳቸውን ምግቦችና መጠጦች ማመጣጠን ይኖርብናል። የምግብ ዓይነታዎችንም ማብዛት ተገቢ አይደለም። አንድ ወይም ሁለት ዓይነት በቂያችን ነው።
አል-ሐሊሚይ እንዲህ ይላሉ፦ ‹‹ሐላል ስለሆነ ብቻ ለአንድ ሰው አብዝቶ መመገቡ ትክክል አይደለም። ምግብ በብዛቱ ሰውነቱን ይከብደዋል፤ ወደ እንቅልፍ ይገፋዋል፤ አምልኮ ይከለክለዋል። ስለዚህ ረሐቡን በሚያስረሳ ሁኔታ ይመገብ። የሚመገብበትን ዓላማም በአምልኮ ለመበርታትና ለመጠናከር ይሁን።›› ሹዐብ አል-ኢማን አልበይሀቂ 5/22

ከምግብና ከመጠጥ ከመጾም በተጨማሪ ከማይጠቅሙ ንግግሮች መጾም ይገባናል። ‹‹ምላስህን ያዝ!›› መፈክራች ሆኖ ከአላስፈላጊና ካልተፈቀዱልን ነገሮች ሁሉ በተቻለን አቅም እንጠበቅ።

አሏህ በብዙ ከሚያተርፋት ያድርገን

@shefaa12