Get Mystery Box with random crypto!

ከሩህ...

የቴሌግራም ቻናል አርማ shefaa12 — ከሩህ...
የቴሌግራም ቻናል አርማ shefaa12 — ከሩህ...
የሰርጥ አድራሻ: @shefaa12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136
የሰርጥ መግለጫ

<<የቀንህ ውብነት የሚለካው ወደ አሏህ በቀረብከው ልክ ነው>>

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-23 22:02:43 የመንገዴን እርዝመት የመንገዴን ትክክለኛ አቅጣጫ አካሄዱንም ጭምር አዋቂ አይደለሁም!።ምራን የኔ ወዱድ ችግሮቻችንን ሁሉ ወዳንተ ምንቀርብባቸው ኢማንን ምንሸለምባቸው አድርገን
99 viewshau:), edited  19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-28 07:04:06 የጀነት ቤቶች በዚክራችን ነው የሚገነቡት። ዚክር ስናቆም መላኢካዎችም መገንባቱን ያቆማሉ።'

ጁምዓ ሙባረክ


@shefaa12
159 viewshau:), 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-26 21:57:51 የዐይን ብርሃን ለረጅም ዓመት የሚቆየው መነፅር በመልበስ ሳይሆን ከሐራም ዐይንን ዝቅ በማድረግ ነው። መልካም ነገር በማየት የዐይን ብርሃናችንን እናርዝመው። በተለይ ምሽት ላይ!

@shefaa12
154 viewshau:), 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 05:40:10 አንደኛው ናይት ክለብ ውስጥ ሞተ፣
ሁለተኛው መስጂድ ውስጥ ሞተ።
የመጀመሪያው ሊዘፍን ሳይሆን ሊመክር ነበር የገባው ።
ሁለተኛው ሊሰግድ ሳይሆን ጫማ ሊሰርቅ ነበር የገባው።
እኛ ላያቸዉን እናይና የመሰለንን እንናገራለን ።
የልብ አውቃው ጌታ አላህ ግን በኒያቸው መሠረት ይፈርዳል።
ወደርሱ የምንቀርበው ማናችን እንደሆንን አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው።

@shefaa12
146 viewshau:), 02:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-22 21:49:24 ረቢ
.
ካንተ ሽሽት ከራስ ግጭት፤
የሩህ ሠላም ለዛ ማጣት!፤
እንዲከፈት. . . . .
በሩን ስቶ ከግድግዳ ጋ መፋለም፤
ፍሬ አፍስሶ አፈር መልቀም! ፤

ሂዶ ሂዶ ትርፋ ባዶ፤
አንተን ትቶ
ምን ተገኝቶ፤
.
Hau me/d

@shefaa12
135 viewshau:), edited  18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-20 22:43:54 ደሞ...ዝምብለን በሀሳብ ከመድከምና ከመዳከር፣
ህልማችንና ምኞታችንን ለአላህ ሠጥተን ብናድር፣
ፍቺዉን ጠዋት ላይ ስንነሳ እናገኝ ነበር

@shefaa12
119 viewshau:), 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-20 12:36:33 መካሪም
(ክፍል አስር)
(ያስ)
*
*
<<አድናኔ... ይቺን ደጅ አስጥተሃት ና...>> አክስቴ አስማ በመዘፍዘፊያ የተቀመጠውን በርበሬ እየጠቆመችኝ። ደስ እያለኝ ተነስቼ ትናንት ሪድዋን ሲያደርግ እንዳየሁት አስጥቼው ተመለስኩ።
<<ኮረሪማውን ደግሞ ከማድቤት ታመጣልኝ... ቁጭ ባልኩበት የተወሰኑትን ልፈልፍላቸው።>> ስቅቅ እያለች ሌላኛውን ትዕዛዝ አከለች። <<አብሽሪ ደስ ያለሽን እዘዢኝ አክስቴ... እኔ ማለት እኮ እንደ ሪድዋን ልጅሽ ነኝ>> ፈገግ ብዬ ላመጣላት ገባሁ። ኮረሪማ ያለችውን ማወቅ ተስኖኝ አንድ 3ቴ በስህተት ከተመላለስኩ በኋላ አመጣሁላት። በኔ መሳሳት እየሳቀች ህመሟን ትንሽ ረሳችው። ከ3 ቀን በፊት መኝታቤት በወንበር ቆማ እቃ ስታወርድ ወድቃ እግሯ በጣም ተጎድቷል። ወገቧንም ስላመማት ተደግፋ ካልሆነ መቆምም መቀመጥም እየተቸገረች ነው። አላህ ብሎላት እንጂ አልጋው ቢመታት ልትሞትም ትችል ነበር። እንዲ ታማም ቢሆን ግን ሪድዋን እያገዛት የቤቱን ስራ ቀጥ አድርጋ መያዟ አልቀረም። ትናንት ደግሞ በርበሬ ከምታስፈጭላቸው ሴቶች አንዷ ደውላ ስላዘዘቻት ስራውን ለመስራት እያገዝኳት ነው። አጎቴ ማሻአላህ ቤቱን አሟልቶ ቢይዝም አክስቴ ስራ መፍታት ስለማትወድ የጀመረችው ስራ መሆኑን ነግሮኛል። ሪድዋን ቤት ስለሌለ እኔን ስታዘኝ ተሳቃ ነው። አሁን እንደውም ከቅድሙ ትንሽ ቀለል ሳይላት አልቀረም። ከጎኗ ቁጭ ብዬ ኮረሪማውን እየሰበርኩላት እሷ እየፈለፈለች እያለ የጊቢው በር ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩ።
.
<<አሰላሙ አለይኩም አሱዬ... እንዴት ነሽልኝ? አሞኛል ስትዪ እኮ ተጨንቄ...>> የድካሟን እያለከለከች አክስቴን ዘይራት ተቀመጠች። ከዚህ በፊት አይቻት አላውቅም... ከንግግራቸው እንደተረዳሁት ግን ዘመድ ሳትሆን ወዳጅ ነገር ናት። በዚሁ ጀምረው ለግማሽ ሰዓት ያህል ስለደህንነታቸው የመሳሰሉትን ሲጠያየቁ ቆዩ።
<<እና ቆይ ካመመሽ አትተዪውም እንዴ? ሌላ ቀን አይደርስልሽም ነበር?>> ሴትየዋ ሌላ ጥያቄ ቀጠለች።
<<አይ አይሹ... ለኔ አይይለም። ለሰው ስለሆነ እንዲደርስላቸው ብዬ ነው የጀመርኩት።>> አክስቴ ፈገግ እያለች መፈልፈሏን ቀጠለች።
<<አሃ ዘመድ ነገር ናቸዋ...>> ድምጿን ከቅድሙ ቀነስ አድርጋ የመታዘብ አይነት አክስቴን እያየቻት።
<<ኧረ አይደሉም... አላውቃቸውም ደውለው ነው ያዘዙት>>
<<እንዴ? እና ለማታውቂው ሰው ነው ይሄን ሁሉ ኮረሪማ የምትጨምሪው?>> በመገረም እያየችን።
<<አዎ... ምነው? ችግር አለው?>> አክስቴ ግራ መጋባቷ ያስታውቃል። በእውነቱ እኔም የሴትየዋ መደነቅ አልገባኝም።
<<የዋህ አግኝተው ይበዘብዙሻል አይደል? በተወደደ ኑሮ ይሄ ሁሉ ኮረሪማ የገባበት በርበሬ አስፈጭተሽማ አትችዪውም። ከሁሉም ቀነስ ቀነስ አድርገሽ ስማቸውን ብቻ ማስገባት ነው እንጂ። ሌላው የከበረው እንዳንቺ ስለሚሰራው ይመስልሻል እንዴ? በዚ አይነት ይሄ ሁሉ ዝንጅብልና ነጭ ሽንኩርትም ሊገባበት ነው ትዪኝ ይሆናል እኮ...>> አይኗን በመዘፍዘፊያዎች ተከምረው ወደ ተቀመጡት እቃዎች እየወረወረች።
<<ሃሃሃ አይ አይሹ... እና እንደ ሌሎቹ ሸክላ ጨምሪበትም ልትዪኝ ነው?...ሃሃሃ>> አክስቴ ከልቧ እየሳቀች። የሴትየዋን ንግግር በየዋህነት ነበር ያየችው። እኔ ግን አናዳኛለች።
<<እሱንማ አላልኩሽም.... እኔም እኮ እሰግዳለሁ እቴዋ ምን ሆነሻል? ባዕድ ነገር ጨምሪ አላልኩሽም... ግን አንድ ሁለቱን ቅመሞች ታልፊያቸዋለሽ። ሌሎቹን ደግሞ ቀነስ አድርገሽ ትጨምሪያለሽ። ዋጋው ረከስ ያለውን ታበዢዋለሽ። ወላሂ የምሬን እኮ ነው... እኔ የባሌ እህት ስትነግድ ስለማውቅ ነው። አሁን እንዴት ከብራለች መሰለሽ...ብትጠሪያት አትሰማም..>>
<<አይ አይ በቃሽ አይሹዋ... እሱ ሃራም ነው። የግድ የወጣ ስርቆሽ ካልሆነ ማታለል ሃላል ነው ያለው ማነው?>> አክስቴ ቆጣ አለች።
<<ማለት? ይሄ ማታለል ነው ልትዪኝ ነው?>>
<<አዎ ነው! ንግድ እኮ በጣም ከባድ ስራ ነው... የሰዎች ሃቅ ወደ ራስሽ ከመጣ በአላህ ፊት ያስጠይቃል። ለዘመድ ወይ ለምታውቂው ሲሆን አይደለም ትክክለኛ ስራ... ሁሉም ቦታ ለሚያይሽ ጌታ ስትዪ ነው። ሙስሊም ከሆንን፤ ከሰገድን... እንዴት እናታልላለን? <ያታለለ ከኛ አይደለም> የሚለው የነቢና ሰ.ዐ.ወ ንግግር ሊይዘን ይገባል። ሌሎች ስለከበሩበት አይደለም ጉዳዩ... ለኔ የሚታየኝ ዛሬ አጭብርብረው በበሉት ያህል ነገ መጠየቃቸው ስለሆነ አዝንላቸዋለሁ። የኔ አርአያ የነሱ ማደግ ሳይሆን ማንኛውንም ነገር ስሸጥ አይቡን ነግሬ እንድሸጥ የሚያስገድደኝ ሃይማኖቴ ነው። አላህ እኮ

وَيْلٌ لِّلْمُطَفِّفِينَ¤

{ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡} እኮ ነው ያለን። የጌታሽን ቁጣ መካፈሉ የሚያስቀና ነገር ነው አይሹ? መታመን እኮ ለራስሽ እና ለጌታሽ ነው... ነገ ሌላ የሚከራከርልሽ ገንዘብም ሰውም የለም። ወላህ የምሬን ነው...ስትሸጪ ብቻ አይደለም ስትገዢም ጭምር አለማታለል አማናን እንደመጠበቅ ነው። በነቢና ጊዜ ገዢውም ሻጩም አላህን ፈሪ ስለነበር ለሰላት አዛን ሲሰሙ ሱቃቸውን ባዶ ትተው ሲሄዱም የሚነካው አልነበረም። ዛሬ ላይም አንቺ ማንም የሌለበት ሱቅ አግኝተሽ ብትቸኩዪ እንኳን እቃውን አንስተሽ ብሩን በቦታው አስቀምጠሽ መሄድ ይኖርብሻል... አላህ ያይሻላ! እከሌ እኮ ባዶ ሱቅ ገጥሞት እቃ አንስቶ መጣ፤ ብልጥ ነው ጀግና ነው ስትዪ ብሰማሽ እናደዳለሁ እንጂ አልቀናም። ስለከፈልኩ ሞኝ ብትዪኝም አልመለስም... አላህ ሁኔታዎችን የሚያመቻችልን እኮ ሊፈትነን ነው። አልሃምዱሊላህ ሞልቶኝ የተረፈኝ ሴት ነኝ... ስለዚህ የጠራ ስራ ለጌታዬ ስል እሰራለሁ። ገንዘብን ተጠቅመሽ ጌታሽን ስትከጂው ገንዘብን ተጠቅሞ ይቀጣሻል... ቅጣቱ እኮ ከባድ ነው። አሊም ቢሆን ስራውን ልጀምር ሳስብ ያስጠነቀቀኝ እና ያስማለኝ ትልቁ ነገር ለደንበኞቼ አይቡን ተናግሬ እንድሸጥላቸው ነው። አሊ አይቡን ሳይነግር የሚሸጠው ምንጣፍ የለም... ብዙ ወዳጆቹ ያከስርሃል እያሉ ይወተውቱታል። ግን አላህ ብሎለት ሰዎች በዚህ ስራው ይወዱታል፤ መደዳ ካሉ ሱቆች የሱን ሱቅ በስም ፈልገው ነው የሚገዙት። እኔም በተቻለኝ አቅም አይብ የሌለበትን ስራ ለመስራት እሞክራለሁ። አንቺም በቻልሽው አስተሳሰብሽን ብታስተካክዪው ነው ኸይር የሚኖረው...>> አስረድታት ስትጨርስ ወደ መፈልፈሉ ተመለሰች። ደግ አደረገቻት... ንግግሯ አናዶኝ ነበር። አክስቴ እንደ አጎቴ ዳር ዳሩን ሄዳ መመለስ አይሆንላትም... ቆጣ ትላለች። ሴትየዋ በአክስቴ ምላሽ መደንገጧ ያስታውቃል። ለደቂቃዎች ዝምታ ቤቱ ውስጥ ሰፈረ።
<<እሱስ ልክ እኮ ነሽ አሱዬ... እኔ መች እንዲ አሰብኩት። እንዲ የሚያስቆጣሽም አልመሰለኝ... ተዪው በቃ። ለራስሽ አሞሽ አባባስኩብሽ...>> ነገሩን ለመሸፋፈን እየሞከረች። <<በይ አስቀምጪ እሱን... አምጣውማ ተቀበላት። በቃ እኔ እጨርሰዋለሁ አንቺ አረፍ በዪ... ለዛሬ ያልሆንኩሽ...>> እጇን ጭምር እያወናጨፈች። አክስቴ በአካኋኗ ሳቅ ብላ ነጭ ሽንኩርቱን በመፈልፈል እንድታግዛት ተስማሙ። ቅያሜ የማይዘልቅበት ወዳጅነታቸው ደስ ይላል። ሌላ ርዕስ አንስተው መጨዋወታቸውን ቀጠሉ፤ እኔም እየተመላለስኩ እነሱን ማገዙን ተያያዝኩት።
*
*
ይቀጥላል...

@shefaa12
119 viewshau:), 09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-20 12:02:04 አንዳንድ ጊዜ ሁሉ ነገራችን እያለቀሰ ዐይናችን ብቻ የማያለቅስበት ሁኔታ አለ።
አላህ ግን ወደ ዉስጥም ወደ ዉጭም የምናነባዉን ያውቃል ።

@shefaa12
84 viewshau:), 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 22:40:40 አጀማመሩን አትይ፣ ኢብሊስም ሲጀመር ሙእሚን ነበር።

አሏህ ሆይ ኻቲማችንን አደራ።

@shefaa12
86 viewshau:), 19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 11:46:14 ዱዓ አርጌ፣ አላህን ለምኜ ምንም ያገኘሁት ነገር የለም የሚል ካለ በርግጥ ጌታዉን አላወቀም ።

@shefaa12
290 viewshau:), 08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ