Get Mystery Box with random crypto!

'በረካ' 8 (ነጃት ሀሰን) : ብናመሰግን እንደሚጨመርልን በዘላለማዊ ቃሉ ተላልፎልናል። በረካው በ | ከሩህ...

"በረካ" 8
(ነጃት ሀሰን)
:
ብናመሰግን እንደሚጨመርልን በዘላለማዊ ቃሉ ተላልፎልናል። በረካው በሽኩር!
የኛ ነገር ማመስገኛ ያጣን ይመስል ንፃሬ ውስጥ የሚገባ ነገር ካላገኘን ማመስገን ያለብን ሁሉ አይመስለንም እንጂ በኛ ላይ ስለፈሰሰው በረካ ሁሉ በእስትንፋሳችን ልክ ብናመሰግን ከፍለን ባልጨረስነው ነበር። ባለንበት ሀል ሁሉ <አልሐምዱሊላህ> ከሊሳናችን ባይጠፋ፡ እውን እየኖርን ያለውን የጥበት ሀያት እንኖር ነበር? ማማረር ለአንደበታችን እንዲህ ይገራ ነበር?

አልሐምዱሊላህ...ትዝታ ሁነው ስላለፉልን መጥፎ ለመሰሉን ወቅቶች!
አልሐምዱሊላህ... አሁን እየተጋፈጥናቸው ላሉ ከአለት የባሱ ስለመሰሉን የዱንያ ፈተናዎች!
አልሐምዱሊላህ... በአልሐምዱሊላሃችን በረካው ስለሚጎርፍብን!
አልሐምዱሊላህ... አልሐምዱሊላህ ማለትን ስላስቻለን!
በበረካው!

@shefaa12