Get Mystery Box with random crypto!

Abx አሥሩ የዚል-ሒጃ ቀናት *** ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ **** አላህ ሲያስብልን፣ ሲወደን | ከሩህ...

Abx

አሥሩ የዚል-ሒጃ ቀናት
***
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ
****
አላህ ሲያስብልን፣ ሲወደን እና ሊጠቅመን ሲፈልግ ምንዳዉና ችሮታው የሚነባበርባቸዉን ቀናትና ጊዜያት ጠቆመን፡፡
አስተዋይ ልቦና የሠጠው ሰው በትኩረት ይጠቀምባቸዋል፡፡ እንደዋዛ አያሳልፋቸዉም፡፡

አሥሩ ምርጥ ቀናት ነገ ሀሙስ ይጀምራሉ፡፡ ስለ ምርጥነታቸው በቁርኣን ተመስክሮላቸዋል፣ አላህ ምሎባቸዋል፣ የአላህን ቤት ጎብኝዎች ወደተከበረዉና የተቀደስው ሥፍራ መካ እና ዙርያው በመጉረፍ የሐጅን ሥርዓት ያከናዉኑባቸዋል፡፡

በቀናቱ ዉስጥ ምን መሥራት እንችላለን?
1- ከልብ ተፀፅቶ ወደ አላህ መመለስ፤
2- አላህን ማውሳት ማብዛት፣
3- መፆም፣
4- ኢስቲግፋር ማብዛት፣
5- መመጽወት
6- ዱዓእ ማድረግ፣
7- ሶላትን በወቅቱ መስገድ፣
8- ከኃጢኣት መራቅ፣
9- ስለ ቀናቱ ምርጥነትና እንዲጠቀሙባቸው ሌሎችን ማስታወስ፣
10- በነቢዩ ላይ ሶላዋት ማውረድ፣
11- መልካም ሥራዎችና ንግግሮች ለምሳሌ - ወደ አላህ መንገድ መጣራት፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ለጎረቤት መልካም መዋል፣ ወላጆችን ማስደሰት፣ አስቸጋሪን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ፣ የታመሙትን መጎብኘት፣ ለሙታን ዱዓ ማድረግ፣ ወንድም እህቶችን በሌሉበት በዱዓ ማስታወስ፣ የባለዕዳን ዕዳ መሰረዝ፣ የተቸገረን መርዳት፣ የታሠረን መጠየቅ፣ ሰዎችን አለማስቸገር፣ ቤተሰብን መንከባከብ፣ ለሠራተኞች ማዘን ...ሌሎችም ።

@shefaa12