Get Mystery Box with random crypto!

❤ የፍቅር ግጥም🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የሰርጥ አድራሻ: @selafeker
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.61K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 💔 ❤
💊🔮 ከፍቶሀል?🙍‍♂
ከፍቶሻል? 🙍‍♀
🚬 አስደስታችኋል ብዬ ቃል አልገባም😥 ስሜታችሁን ግን እጋራለው💔 እናም ማንም ሰው እንዲያፅናናኝ አልፈልግም 🙅‍♂
ለአድናቆት @Addisu32
Join 👇requests የሚለውን ይጫኑ 👇

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-02 08:15:02 የልጅነት የኳስ ጨዋታ ህጎች!

1 ምንጊዜም ሰፈር ውስጥ ወፍራሙ ልጅ ጎል ጠባቂ ነው።

2 ሁልጊዜ ጨዋታ የሚያልቀው ሁሉም ተጫዋች ከደከመው  ብቻ ነው።

3 አስር ጊዜ ጎል ስታስገባ ብትውልም የሚያሸንፈው መጨረሻ ላይ ጎል ያስገባው ቡድን ነው።

4 ዳኛ ቢኖርም በጩህትና በጭቅጭቅ ያሳመነው ያሸንፋል።

5 ምንጊዜም የኳሱ ባለቤት ካኮረፈና ከተበሳጨ  ጨዋታው ያልቃል።

6 ሁለት ጎበዝ ተጨዋች አንድ ቡድን ውስጥ መጫወት በልጅነት ህግ የተከለከለ ነው።

7 ድንገት ተቃራኒ ቡድኑ ፔናሊቲ ካገኘ የኳሱ ባለቤት ከመቅፅበት ጎል"ጠባቂውን አባርሮ ራሱ ጎል ጠባቂ ይሆናል።

8 ኳሱ ፎሪ ወጥቶ የሰው ግቢ ውስጥ ከገባ ያስገባው ልጅ ሙሉቀንና ሙሉ ለሊት ሸፋፋ እየተባለ ሲሰደብና ሲረገም ይውላል።

9 ምንጊዜም በጣም ጎበዙ ተጫዋች የኳሱ ባለቤት ጋር አንድ ቡድን ናቸው።

10 ጨዋታው አንዱን ቲም ከተቃራኒው ለመለየት አንዱ ቲም ከወገብ በላይ ራቁቱን ይጫወታል።

11 ምንጊዜም ጨዋታ የሚጀመረው ኳሷን ወደ ሰማይ በመጠለዝ ነው።

12 አጥቂ ተከላካይ የሚባል የለም ሁሉም ያጠቃል ሁሉም ይከላከላል የደከመው ወገቡን ይዞ በረኛውን ያወራዋል።

13 ምንጊዜም የኳሱ ባለቤት FIFA በለው።

14 ኦፍ ሳይድ የለም ግር ብለህ ታጠቃለህ ግር ብለህ ትከላከላለህ ግሪሳ ሁላ።

15 ድንገት በጨዋታ መሃል እናትህ ከጠሩህ ሰው ተክተህ ትሄድና ስትመለስ የተካህውን ሰው አባርረህ ጨዋታውን ከቆምክበት መቀጠል ትችላለህ።

ጨምሩበት!

@Addisu32
@selafeker


https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
1.8K viewsAddisu, 05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 08:12:05 የክህደት-ማረፊያ


የህይወት ታሪኬን...
እየገለጥኩ ሳይ..
ከእለታት አንድ ቀን አንቺን ተመለከትኩ፣
መልክሽን እንዳየሁ
የዘመናት ልቤን ለልብሽ አስረከብኩ፣
ተመልከች እንግዲ
የአንድ ቀን እይታ እድሜን ሲመግብሽ
የነገ ህይወትን
ከራስ ላይ ቀንሶ ላንቺ ሲለግስሸ
ቀናቶች፣
ሳምንቶች፤
እየተሻገሩ አዲስ ወራቶችን እኛ ላይ ፈጠሩ
የኔ እና አንቺን እውነት 
ወደ መተዋወቅ ቀርፀው አሻገሩ!
..........................................
ከእለታት አንድ ወር
የአይን ፍቅሬ ዘልቆ በልቤ ሲሰምር፣
የፍቅርሽ ቀመሩ
በኦና ልቤ ላይ ህይወትን ሲቀምር፣
ስ ት መ ለ ከ ቺ
እዝነት ወይም ፍቅር
በልብሽ ላይ ገዝፎ እኔን ስትመርጪ፣
አንድ አኔን ለማብራት
ጨለማ ህይወቴ ላይ እንደ ጧፍ ስትቀልጪ፣
የተረዳ ልቤ
ስለ ፍቅር ጥልቀት ሲሰብክ ያሳልፋል
እንደሻማ ህይወት
ለኔ ብርሀን ስትቀልጭ አመት ይቆጠራል!
....................................................
ከእለታት አንድ አመት..
ያፈቀርሹ እኔነት..
ከልብሽ ላይ ወጥቶ ጥለሽው ስትሄጂ፣
እንደሻማ ቀልጠሽ
የበራው ልቤ ላይ ስትረማመጂ፣
የፍቅርን እውነት
ከእምነቴ ላይ ፍቀሽ በይምሰል ስትፈጂ፣
አማኝ አፍቃሪሽን
ንፁህ ወዳጅሽን አንድ እኔን ስትከጂ፣
በቀናት፣
በወራት፣
እንዲሁም በአመታት፣
የተቀጣጠለ ነዶ የከሰመ የፍቅራችን እሳት፣
አንቺን ሲያጠፋ፣
አመድ እያረገ እኔን ያሻግራል ወደ እብደት ዘመናት!
.................................................
ከእለታት
ዘመናት
በሆነ አንድ ቀን ላይ የአይኔ ካንቺ ማረፍ
በሆነ አንድ ወር ላይ የልብሽ መሸነፍ
በሆነ አንድ አመት ላይ የፍቅራችን መክሸፍ
በሀሳቤ እየዋለ
ወደ እብዶች መንገድ ገፍቶ እየወሰደኝ
የተቀያየረው
ጨርቅ መሳይ ፍቅርሽ ጨርቄን እያስጣለኝ
በክህደትሽ ስካር
አንበሳ የነበርኩ'ን አይጥ አደረገኝ!
...........................................
ከእለታት ዘላለም
የክህደትሽ ክብደት
የኔን የዋህነት ታማኝነት ሰብሮ
ልክ ያለፈ ፍቅሬ
ጥለሽው ስትሄጂ ፍፁም ተቀይሮ
በቀናት ፧ በወራት
በአመታት ፧ ዘመናት የተገራ ልቤ ራሱን አፍቅሮ
የተከዳው ልቤ
ሌሎችን ይጠላል ፣ ማመን ተቸግሮ!

ጉድ ሰራሽኝ።

@Addisu32

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
1.6K viewsAddisu, 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 20:14:28 ዋው!!!

ዛሬ ቀኑ ደስ ይላል። ፀሐይ ለስላሳ ሙቀቷን እንደተለመደው ለሰው ልጅ እየሰጠች ነው። ወፎች ጥኡም የሆነ ዜማቸውን እያሰሙ ነው። ሰዎች ሁሉ የእለት ስኬታቸውን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ናቸው። ይህች ቀን የእኔም ናት። ሥራዎቼን ሁሉ በብቃት የምከውንባት ሌላ ተጨማሪ ቀን። በዚች ቀን ሁሉን ነገር በብቃት እንደምወጣባት እርግጠኛ ነኝ። ሥኬት ከእኔ ጋር ናት። አምላኬ ሆይ አመሰግንሀለሁ ፣ ይህችን ቀን የእኔ ስላደረካት።


[ለአእምሮዎ ብሩህ ቃላትን ይመግቡ]

             ብሩህ ቀን ተመኘን።


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

@Addisu32

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
32 viewsAddisu, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 20:11:34
አንደበት ባይኖረኝ ፣
ልሳኔ ቢታሰር፣
ምንም ኩልትፍ ብሆን ፣
ቢያቅተኝ መናገር ፣
እንዳለ ግን ይግባሽ ፣
ብዙ ብዙ ነገር ፣
በዝምታዬ ዉስጥ ፣
ሺ መዉደድ ሺ ፍቅር፡፡

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

@Addisu32
@selafeker
61 viewsAddisu, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 17:51:30 ተጋበዙልኝ
529 viewsAddisu, 14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 17:51:30 https://www.facebook.com/nebilnur22/videos/198841169141245/?mibextid=WPBo4E68yvx9pgQK
531 viewsAddisu, 14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 20:06:25
@Addisu32
@Addisu32
@selafeker
1.3K viewsAddisu, edited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 18:54:11 https://vm.tiktok.com/ZMYcMJcM1/
549 viewsAddisu, 15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 12:07:13
1.1K viewsAddisu, 09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 12:05:23

እንኳን ለ 1444ኛው የዒድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
                
በመላው አለም የምትኖሩ የእስልምና እምነት ተከታይ ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን ለ1443ኛው የዒድ  በአል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን።

የዒድ በአል የእዝነት ÷ የመተሳሰብ ÷ አብሮ የመብላትና የመፈቃቀር በአል በመሆኑ በየ አካባቢያችን በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን እያሰብን እንዋል።

          ዒድ ሙባረክ !!!

@Addisu32
1.1K viewsAddisu, 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ