Get Mystery Box with random crypto!

❤ የፍቅር ግጥም🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የሰርጥ አድራሻ: @selafeker
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.61K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 💔 ❤
💊🔮 ከፍቶሀል?🙍‍♂
ከፍቶሻል? 🙍‍♀
🚬 አስደስታችኋል ብዬ ቃል አልገባም😥 ስሜታችሁን ግን እጋራለው💔 እናም ማንም ሰው እንዲያፅናናኝ አልፈልግም 🙅‍♂
ለአድናቆት @Addisu32
Join 👇requests የሚለውን ይጫኑ 👇

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-07 14:39:22 ከቁንጅና የቀጠለ part 5

ቃሏ ..
ለምን ተከተልከኝ? የምትል ጥያቄ!
እንባዋ ይወርዳል
ደግሞም ታወራለች
ጠዋት ነው ምዕራቤ ምሽት ነው ምስራቄ!
ብላ ታለቅሳለች

ቃሏ ሲተነተን
ምስራቅ ብርሀን ነው የፀሀይ መውጫ
ምዕራብ ጨለማ ነው የጨረቃ መምጫ
ይሄ ተፈጥሮ ነው
በኑረት መንገድ ላይ
ብርሀንም ጨለማም የግል ነው ምርጫ!

ማለት..

የዚች ሴት ብርሀን
የዚች ሴት ፀሀይ ምሽት ላይ ይወጣል
የዚች ሴት ጨለማ
የዚች ሴት ፀሀይ ሲነጋ ይጠልቃል
የህይወት መስመሯ ከሌላው ይቃረናል!
ብዬ ስብሰለሰል
ጨለማ ቤቷ ውስጥ አንድ ህፃን ያለቅሳል።

ወደ ልጁ ድምፀት
ፊቷን ዘንበል አርጋ
ልጄ ነው እያለች፣
በደብዛዛው ቤቷ
ደብዛዛ ፊቷ ላይ
ጥርሷን ትጭራለች።

ይህቺ ሴት ቀጠለች

18 አመቴ ላይ ይኽንን ህፃን ወለድኩኝ፣
18 አመቴ ላይ የልጁን አባት ቀበርኩኝ፣
18 አመቴ ላይ ይኽንን ስራ ጀመርኩኝ፣
እኒህ ሁሉ ጠባሳዬን
በውብ ገላዬ ላስታውስ ቁጥሩን ግን ተነቀስኩኝ።

አለችኝና አነባች፣
እኔም አልቅሼ አቀፍኳት፣
አንቺ ሴት በጣም ቆንጆ ነሽ
ወላሂ ብዬ ማልኩላት፣
እሳት የሆነ ከንፈሯን
ከንፈሬ ላይ ለኮሰችው፣
አዳፋ የሆነ ገላዬን
በእቅፏ አጠበችው፣

ህፃን ልጇን ተመለከትኩ
እሷን መሳይ መልዐክ ነው፣
እሷን ደግሞ ተመለከትኩ
ንግስት ነው የምትመስለው፣

በጨምዳዳ ፊቴ መሀል ፈገግታዬን አሳያኋት
ታስጠላለህ ብላ አለችኝ
የወደድኩላት ምዐፀቷን በስላቄ መለስኩላት!

ያንን ሳቋ ለቀቀችው፣
ይሄን ልቤ ለከፈችው፣
በፈገግታዋ ተረታሁ፣
ገላዋን አቅፌ አነጋሁ፣
ምዕራብ ነው ባለችው ጠዋት
ምስራቅን ሆኜላት ወጣሁ።


አላለቀም የሷ ህይወት

ግጥሙ ግን አልቋል

@Addisu32
@selafeker


https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
420 viewsAddisu, edited  11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 14:18:14 በፈጣሪህ ተደገፍ!!!
ህይወትህን የሚቀይረው ከሰው ጠብቀህ የምታገኘው ነገር አይደለም፤ ፀጋው፣ ስጦታው፣ ቸርነቱ ከማያልቀው ከፈጣሪህ ከምታገኘው በረከት ነው ህይወትህ የሚቀየረው።

ወዳጄ በጭራሽ ከሰው እንዳጠብቅ፤ ሰው ማለት ሸንበቆ ነው የሆነ ቀን መቀንጠሱ አይቀርም! ከፈጣሪ ቀጥሎ ራስህን እመነው!!!

@Addisu32

@selafeker

775 viewsAddisu, 11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 20:48:01
ይሄ ፍትሃዊ ውሳኔ ነውን!?
================
በዛምቢያ መንገድ ዳር ቆሻሻ ምትለቅም የአእምሮ ታማሚ ሴትን ያስረገዘው ግለሠብ በፍርድ ቤት እንዲያገባት ወይም 10 አመት እንዲታሰር ፈረደበት! የዛምቢያ ተወላጅ እና የመንግሥት ሰራተኛ የሆነው ግለሠብ መንገድ ዳር የምትተኛዋን የአእምሮ ታማሚዋን ግለሠብ ማታ ማታ አካባቢው ከሚገኘው መኖርያው ወጥቶ እየሄደ ቀስ ብሎ ጨለማ ተገን አድርጎ ምታድርበት ድንኳን ድረስ እየሄደ በትናንሽ ስጦታ በማባበል አስረግዟታል። ግለሰቡ በፖሊስ ተይዞ ክስ የተመሠረተበት ሲሆን ፍርድቤቱም ለግለሰቡ 2 ምርጫ ሰጥቶታል። አንደኛ ያስረገዛትን ሴት አግብቷት ልጁን በጋራ እንዲያሳድጉ ምርጫ የተሰጠው ሲሆን፣ ሁለተኛ የመጀመሪያውን አማራጭ የማይቀበል ከሆነ ለ10 አመታት እንዲታሰር ፈርዶበታል።

@Addisu32


https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
1.2K viewsAddisu, edited  17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 16:22:22 በአንድ ወቅት ቢል ጌትስን “ካንተ የሚበልጥ ሃብታም አለ ወይ?” (ልብ በሉ ቢል ጌትስ ቁጥር አንድ ሃብታም በነበረበት ወቅት ነው) ተብሎ ተጠይቆ የሰጠውን አስገራሚ ምላሽ blogpost በMy Life Chapter ገፁ ላይ በ2017 አስነብቦ ነበር:: ምላሹ መሳጭና አስተማሪ ስለሆነ እንዲህ አቅርቤዋለሁ።

“ከብዙ ዓመት በፊት ነው: ኒውዮርክ ኤርፓርት ውስጥ ጋዜጣዎችን ሳይ አንዱ ጋዜጣ ላይ የተፃፈውን ርዕስ ወደድኩትና ጋዜጣውን ልገዛው ፈለኩ:: ነገር ግን ምንም ገንዘብ አልነበረኝም እና ጋዜጣውን አስቀምጬ ስሄድ ያ ጋዜጣ ሻጭ ጥቁር ልጅ ጠራኝና ‘ይህ ጋዜጣ ያንተ ነው:: ውሰደው::’ አለኝ:: ‘ምንም ገንዘብ የለኝም ልገዛክ አልችልም’ ስለው ‘ምን ችግር የለውም ውሰደው’ ብሎ ጋዜጣውን ሰጠኝ::

ከ3 ወር በሗላ እዛው ኤፓርት ሄድኩኝ እና እዛ ጋዜጣ ሻጭ ልጅ ጋር ተገናኜን:: በአጋጣሚ አሁንም ልገዛ ፈልጌ ገንዘብ አልነበረኝም:: አሁንም ልጁ ጋዜጣውን በነፃ ሰጠኝ:: አሁንስ ደግሜ ልቀበልክ ብለው ‘ምንም ችግር የለውም ውስደው ሰጥቼሃለሁ’ ብሎ ጋዜጣውን በነፃ ለሁለተኛ ጊዜ ሰጠኝ።
ከ19 ዓመት በሗላ ሃብታም እንዲሁም ታዋቂ ሆንኩ:: በዚህ ጊዜ ልጁን አግኝቼ ብድሩን ልመልስለት ማፈላለኩ ጀመርኩ:: ከአንድ ወር ፍለጋ በሗላ እገኘሁት:: ‘ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ?’ ብዬ ጠየኩት እሱም ‘አዎ ዝነኛው: ሃብታሙ ቢል ጌትስ ነክ’ አለኝ:: እኔም ‘ከብዙ አመት በሗላ ሁለት ጋዜጦች በነፃ ሰጥተህኛል: እናም ብድርክን ልመልስልክ እፈልጋለሁ:: ስለዚህ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ንገረኝና ላድርግልህ’ አልኩት:: እሱም ‘ምንም ነገር ብታደርግልኝ ብድሬን መመለስ አትችልም’ አለኝ::’ እኔም በጣም ተገርሜ ‘ለምን?’ አልኩት:: እሱም ‘እኔ የሰጠሁህ ደሃ እያለሁ ካለኝ ላይ ቀንሼ ነው:: አንተ ግን የምትሰጠኝ ሃብታም ሆነክ ከተረፈክ ላይ ነው:: ስለዚክ ብድሬን ልትመልስ አትችልም::’ አለኝ::
በርግጠኝነት ያ ልጅ ከኔ የበለጠ ሃብታም ነው:: “
ምን ለማለት ነው ሰውን ለመርዳት የግድ እስኪተርፈን ድረስ መጠበቅ የለብንም:: ካለን ላይ ማካፈል የበለጠ ዋጋ አለው።


ሼርርርር



(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣

@Addisu32


https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
310 viewsAddisu, 13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 11:37:01 ቡድንህን አዋቅር

ምን ግዜም ልትረሳው የማይገባ ነገር ልንገርህ። ብቻህን ሆነህ የህይወትን ውጣ ውረድ ማሸነፍ ወይም  ስኬታማ መሆን አትችልም።  የተሻለ ሰው መሆን ከፈለግህ ሌሎች የተሻሉ ሰዎች ለመሆን መነሳሳቱ ያላቸውን ጓዶች አብሮነት መስርት። ታላቁ መጸሐፍ "ከጠቢብ ጋር ጠቢብ ትሆናለህ ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ትሆናለህ " ይላል። የወደፊት ህይወትህ አብረሀቸው የምትውላቸውን ሰዎች ይመስላል። ስለዚህ የምትሻውን ስኬት ሊያጓናጽፉ የሚችሉ ጓደኞችን እና ወዳጆችን ምረጥ።

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ አዲስ

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

@Addisu32

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
561 viewsAddisu, 08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 11:32:00 ☞  ጠቃሚ ምክሮች  ☜


  ቁንጅና ለትዳር ዋስትና አይሆንም!
  መታመም ማለት ትሞታለህ ማለት አይደለም!
  ሃብታም መሆን የጥሩ እድል ትርጉም አይደለም!
  ጥሩ ቤት ውስጥ መኖር የድሎት ምንጭ አይሆንም!
  ጥሩ መኪና መንዳት ለምትደርስበት ቦታ ዋስትና
አይሰጥህም !
  ለቤተሰብህ ዶክተር ብትቀጥር ቋሚ የጤና ዋስትና አይኖርህም!
  ብዙ መማር ጥበበኛ አያደርግህም!
 ሃብታም  ማግባት ለደስተኛ ለህይወት ማረጋገጫ አይሆንም!
  ክርክር ማሸነፍ ትክክል መሆን አይደለም !
:
*
ገነት የማያሸልም ምንም ነገር ብትሰራ ጊዜያዊ እና
ውሸት ነው ። ያለ አምላክ የሚራመድ ሰው በድን
ነው፣አንተ በራስህ ላይ ስልጣን የለህም* አንተ
ሰውነትህን ታያለህ እሱ ደምስርህን ያያል ። ሁሉም
ነገር ለርሱ ይቻላል በሁሉም ነገር ውስጥ አምላክህን ጣልቃ አስገባ።



━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ Addisu

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

@Addisu32



https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
509 viewsAddisu, 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 11:28:57
ገና ስትፀነስ በሕይወት ዘመንህ ትልቅ ቦታ የመድረስ ምርጫ ተመነሻውም የተሰጠህ መሆኑን ተገንዘብ። ፈጣሪ ሕይወት ሰጥቶኻል፥ ሕይወትህን ደርዝ የምታስይዘው ግን አንተ ነህ። ቢያንስ መሞከር አለብህ። ወኔ ማለት መለወጥ እምትችለውን ነገር መለወጥ መቻል ነው። እረኛ እንድሆን ተፈርዶብኛል ካልክ እረኛ ሆነህ ትቀራለህ።…" (26)

ሕይወት ትርጉምና እና ዓለማ ያላት እንደሆነች ይሰማኛል። ልብህን ማድመጥ እንድትማር ነው ይህን ሁሉ ላንተ መንገሬ። ልብህ የፈቀደው ነገር ዕጣፈንታህ ነው። ፈጣሪ ያን ፈቃድ በልብህ ያሳድረዋል፣ እንግዲህ ያንተ ሥራ የሚሆነው ልብህ የሚነግርህን መከተል ነው። ዛሬ፥ ልቤ የሚያዘውን የምከተል በመሆኔ ነጻ ሰው ነኝ። የችግሮቼ ሁሉ ምንጭ እኔው ራሴ ነበርኩ። ይህንንም ለመረዳት ዓመታት ፈጅቶብኛል።" (57)

           "ኀሠሣ"  በሕይወት ተፈራ
  
            ውብ ቀን

@Addisu32


https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
515 viewsAddisu, 08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 16:45:12 አንቺ እፉዩ ገላ....
ይህ ላባሽ ገለባ..
ተከተይኝ አትበይ
ገደል እንዳልገባ..
እፍፍፍ....ሂጂ  ብረሪ..
ከኔ ላያፀናሽ አትደናበሪ..
እፍፍፍ ሂጂልኝ በቃ
ራቂ ከነፍሴ..
ተስፋ ነው መናኖሬ
አንድ ሀቄን ታቅፌ...
ያዉቃል ባለነፍሴ
መኖርሺን አልሻም...
ሚዛን ላትደፊ
ሂጅ  ከኔ አታመሽም...
ሂጂልኝ ከነፍሴ
ዘመናት እራቂኝ...
በነሽ እስክትጠፊ
ካቅምሽ አታቃይኝ! ሂ...ጂልኝ
   

@Addisu32

1.2K viewsAddisu, 13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 15:16:43
ሐና!

"አቤት ቲቸር!" ድንገት በመጠራቷ ደንግጣ ታፈጣለች። የክፍላችን ጎበዝ ተማሪ ናት ሐና…

"የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎት ምንድ ነው?" ይጠይቋታል።

"ምግብ…ልብስ…መጠለያ" መለሰችው እንላለን እኛ በሽክሹክታ። ገና ትላንት ነው አከባቢ ሳይንስ መምህራችን ያስተማረችን።

"አይደለም! በጭራሽ አይደለም! ሳይንሱ እውነታውን ጋርዶብናል። እንጀራ ማን ሕሊና ውስጥ ቦታ ሰጠው? 'የምድር ፍሬ፣ የወንዝ ውሃ ይሙላህ' የተባለን ሆድ ማነው የሰው መሠረት ያደረገው? የለም! በየጫካው በየዱሩ የሚኖሩ ወገኖቻችን ርቃናቸው ጌጣቸው ነው፤ ቤትስ ቢሆን - የሰው ልጅ ተንኮሉን ሊከልል፣ ለግርዶሹ ስም አወጣ።

ልጆች ልብ በሉ…የሰው መሠረታዊ ፍላጎት አንድ ነው፣ እሱም ፍቅር ነው። ካለፍቅር ሰው የቁም ሙት ነው። ሰው ሰውን ሲያፈቅር፣ ሰው አምላኩን ሲያፈቅር፣ ሰው አገሩን ሲያፈቅር፣ ሰው እውነትን ሲያፈቅር፣ ሰው ነፃነትን ሲያፈቅር ነው ሕያው የሚሆነው። ሰው ነገውን ሲወድ፣ ነገውን ሲያፈቅር ነው ነገ ለሚፈጠር ትውልድ ፍቅር የሚያወርሰው…እስትንፋሱ የሚቀጥለው።"

                      "ዶክተር አሸብር፣
                         የታረሙ ነፍሶች"115          
                     በአሌክስ አብርሃም

             ውብ ምሽት


@selafeker

@Addisu32
1.3K viewsAddisu, 12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 21:37:27 ምክር ለወዳጅ

ምክር ብትሰማ በነፃ ትማራለህ።ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው።በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው።ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ።

በአመት የካብከውን በዕለት የምትንደው በቁጣህ ነውና አትቆጣ።ቁጣ አውቀህ እንዳላወቀ ለፍተህ እንዳለፋ የሚያደርግ በመልካም መሰረት ላይ የአገዳ ቤት የሚሰራ ነው።በገዛ እጅህ ዋጋህን እንዳታሳንሰው ቁጣህን ያዘው።

በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ።ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል።ሰምቶ ማመን ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ።የሰማንያ አመት እውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ አመት መኖር የለብህም።ሰማንያ አመት ከኖሩት በትህትና መጠየቅ ይገባሀል።

አይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ።ነገ እንድትደርስ የትላንቱን አትርሳ።የምትሔድበት እንዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ።

ክፍት አይሙቅህ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ።ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና።ተግባርህ የምርጫህ ውጤት ነውና አስብበት።ክፋ ሰርተህ እንቅልፍ ሲወስድህ ሰይፍ ላይ መተኛትህን እወቅ።

ማግኘት ማጣት የኑሮ ተራ እንጂ አደጋ አይደለም።የተቀበልከው ያንተ ያልነበረውን ነው የተወሰደብህም ያንተ ያልሆነውን ነውና አታንጎራጉር።

ስትጠግብ የምትራብ ስትራብ የምትጠግብ አይመስልህም።ነገር ግን ሁሉም ይለወጣል።ዛሬ ያለኸው በጨለማው ከሆነ ቀጥሎ ብርሃን ነውና ደስ ይበልህ።ዛሬ ያለኸው በብርሃን ከሆነ ቀጥሎ እንዳይጨልምብህ ተጠንቅቀህ ያዘው።በመከራ ውስጥ ካለው ሰው በድሎት ውስጥ ላለው ቀጥሎ አስፈሪ መሆኑን አስብ።በእውነት ጥጋብህ እንዳለፈ ረሀብህም እንደሚያልፍ እመን።

የትላንትናውን ምሽት ስትይዝ አይነጋም ብለህ ሳይሆን ብርሃንን ተስፋ አድርገህ ነው።ከሌሊት ቀጥሎ ሌሊት አይመጣም።ከሌሊት ቀጥሎ ቀን ይሆናል።እንዲሁም ከዛሬ መከፍትህና ሀዘንህ በሀላ ታላቅ መፀጰናናት ይሆናል።

ሁሉም የራሱ ትግል አለውና እንደ እገሌ ምነው ባደረገኝ አትበል።ትዕግስት ስጠኝ ብለህ ለምን እንጂ።በዚህ አለም ላይ የሚታዘንለት እንጂ የሚቀናበት ሰው የለምና።

እገሌ ይናገርልኝ እገሌ መልስ ይስጥልኝ ከሚል ጥገኝነት ተላቀቅ።ጥቂትም ቢሆን በማታውቀው ሙያ ሰራተኞችን ተማምነህ ስራ አትጀምር።ስልጣን ሲሰጡህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን።ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከሀላ ሆነህ አትቅደም።

የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ።የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን።የትላንቱንም አስብ።አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና።

ታሪክን በጣም ወቃሽ አትሁን።አንተም በታሪክ ፊት ነህና ተጠንቀቅ።ያለፋት ተመልሰው መጥተው ያበላሹትን ማበጀት አይችሉም።አንተ ግን እድል አለህና እወቅበት።ታሪኬ እንዲያምር ብለህ አስመሳይ ፃድቅ አትሁን።ዛሬ በቅንነት የምትሰራው ግን ለታሪክህ ይተርፋል።ስራህን ስራ እንጂ ለስምህ አትኑር።አለም እንደ እቅድህ አይደለምና።

ሰዎች ሁሉ እንደ እኔ ካላሰቡ ብለህ አትጥላቸው።ሰው ላንተ ፈቃድ የተፈጠረ አይደለም።ደግሞም ነፃ ፈቃድ ያለው ፍጡር ነው።ነፃ ፈቃዱን እያከበርክለት ወደ እውነት ምራው።ከጠባብ ድንኳንህ ውጣ።

ዛሬ ዋሽተህ ማምለጡ ድል ይመስልሀል።የታወቀብህ ቀን ግን በውሸትህ ያመነህ ሰው በእውነትህ ግን አያምንህምና አትዋሽ።ውሸታምና አመንዝራ ተለውጠው እንኳ ቶሎ የሚያምናቸው አያገኙምና ከውሸት እራቅ።

እጅግ ግልፅነት እብድ ያደርጋል።እጅግ ዝምታም ወዳጅ ያሳጣልና ንግግርህና ዝምታህ በቦታው ሲሆን ውበት ይሆናል።

የእኔ መናገር ምን ይለውጣል?ብለህም ስህተትን አትለፍ።የእኔ አስተዋጵኦ ምን ይጠቅማል?ብለህም ስጦታህን አትጠፍ።

                     

        ውብ አዳር

@selafeker
@Addisu32

@Addisu32





https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
580 viewsAddisu, edited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ