Get Mystery Box with random crypto!

❤ የፍቅር ግጥም🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የሰርጥ አድራሻ: @selafeker
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.61K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 💔 ❤
💊🔮 ከፍቶሀል?🙍‍♂
ከፍቶሻል? 🙍‍♀
🚬 አስደስታችኋል ብዬ ቃል አልገባም😥 ስሜታችሁን ግን እጋራለው💔 እናም ማንም ሰው እንዲያፅናናኝ አልፈልግም 🙅‍♂
ለአድናቆት @Addisu32
Join 👇requests የሚለውን ይጫኑ 👇

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-21 12:03:31 #የገንዘብ_ሳይኮሎጂ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ


The Psychology of Money በሚል ርእስ በሞርገን ሀውስል የተጻፈውና አለም አቀፍ ሽያጭ የተቀዳጀው መጽሐፍ #የገንዘብ_ሳይኮሎጂ በሚል ተተርጉሞ በገበያ ላይ ዋለ፡፡

ከ ሀምሳ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች  የተተረጎመው ይህ መጽሐፍ በብዙ ታላላቅ ሰዎችና በታላላቅ ሚዲያዎች እንዲህ ተሞካሽቷል፡-



የገንዘብ ሳይኮሎጂ መጽሐፍ በሚያስደምሙ ሀሳቦችና በገሃዱ አለም ሊተገበሩ በሚችሉ አስተምህሮዎች የተሞላ ነው። ከገንዘብ ጋር የተሻለ መስተጋብር እንዲኖራቸው ለሚፈልጉ ሁሉ እጅግ መነበብ ያለበት ነው። ሁሉም ሰው ይህ መጽሐፍ ሊኖረው ይገባል!
#ጄምስ_ክሊር
(በሚሊዮን ኪፒ የተሸጠው #የአቶሚክ_ሀቢትስ መጽሐፍ ደራሲ)

ለሃያ አንደኛው ክፍለዘመን የሚያስፈልግ ምርጥ የገንዘብ ሳይኮሎጂ መጽሐፍ
#ብሉምበርግ

ተደጋግሞ የሚነበብ፣ በቢዝነስ አለምም ውስጥ እግራቸውን ማስገባት ለሚፈልጉ ሁሉ የሚሆን
#ዘ_ኮሌጅ_ኢንቨስተር

በዓመታት መካከል የተገኘ ምርጥ እና ኦርጅናል ሀሳብን የያዘ ፋይናንስ መጽሐፍ
#ዘ_ዎል_ስትሪት_ጆርናል

እውነተኛና የማይረሱ ታሪኮችን በውስጡ ይዟል፤ ይህም መጽሐፉን ያለመሰልቸት እንዲነበብ አድርጎታል።
#ፎርቹን

ለሁሉም ስኬቶች እና ውድቀቶች ምክንያት ምን እንደሆነ በሚገባ የሚያሳይ መጽሐፍ
#ፎር_ሚኒት_ቡክስ

ሞርገን ሀውስል ብሩህ አእምሮ ካላቸው የፋይናንስ ጸሐፊያን መካከል አንዱ ነው። በሁሉም እድሜ ላይ ላሉ ሰዎች የሚሆን መጽሐፍ፤ ገንዘብን የማግኘት ሃሳብ ካለህ ከዚህ ጀምር!
#ቡክቶጵያ

ገንዘብ ላይ ከተጻፉ መጽሐፍት ሁሉ የላቀ መጽሐፍ!
#ዘኒው_ሄቭን_ሪቪው

በዚህ ድንቅ መጽሐፍ ገንዘብን ስለማሳደግ፣ ሀብት ስለ ማፍራት እና ሀብታም ሆኖ ስለመኖር፣ ስግብግብነት ስለሚያስከትለው ጉዳት፣ ስለ ኢንቨስትመንት እና ገንዘብን ስለተመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች አስገራሚ ጥበባትን ያስተምረናል፡፡

#አስበህ_ሀብታም_ሁን የተሰኘውን መጽሐፍ የተረጎመው ውድሰው ደግዋለ ተርጉሞታል

#የገንዘብ_ሳይኮሎጂ_The_Psychology_of_Money መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
976 viewsAddisu, 09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 12:02:54
889 viewsAddisu, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 12:42:58 #ሁሉ_ከንቱ_ነው!!
#የዓለማችን ታዋቂ የፋሺን ዲዛይነር እና ፀሐፊ የነበረቺው ኪርዛይዳ ሮድሪጉዌዝ ከዚህ ዓለም በደረጃ 4 የሆድ ካንሰር በ2018 ከመሰናበቷ በፊት የሚከተለውን መልእክት አስተላልፋ ነበር።

1 በዓለማችን ውዱ አውቶሞቢል በጋራዤ ውስጥ ነበረኝ፤ አሁን የምንቀሳቀሰው ግን በዊልቼር ነው።

2 መኖሪያዬ በሁሉም አይነት ዲዛይነሮች በተሰሩ አልባሳት መጫሚያዎች እና ውድ ዕቃዎች የተሞላ ነበር፤ ዛሬ ግን ከሆስፒታል በተሰጠኝ እራፊ ጨርቅ ተጠቅልያለሁ።

3. በቂ ገንዘብ ባንክ ውስጥ አለኝ፤ አሁን ግን ልጠቀምበት አልችልም።

4 ቤቴ ልክ እንደ ቤተመንግሥት ነው፤ አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በታጣፊ አልጋ/ በድንክ አልጋ ላይ ቀርቻለሁ።

5 ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ሌላ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መሄድ እችል ነበር፤ አሁን ግን ጊዜዬን የማሳልፈው ከአንድ የሆስፒታል ላብራቶሪ _ ወደ ሌላው የሆስፒታል ላቦራቶሪ በመንከላወስ ነው።

6 መቶዎች ፈርሚልኝ ይሉኝ ነበር (ከመቶዎች ጋር ስምምነት እፈርም ነበር)፤ ዛሬ ፊርማዬ የዶክተሮች ማስታወሻ ሆኗል።

7 ፀጉሬን ለማስዋብ ዘጠኝ ጌጣጌጦች ነበሩኝ። አሁን ግን አናቴ ፀጉር አልባ ሆኗል።

8 በግል አውሮፕላን (ጀት) ወዳሻኝ ስፍራ እበር ነበር። አሁን ግን ወደ ሆስፒታል ለመሄድ እንኳ ሁለት የሚሸከሙኝ/ የሚደግፉኝ ሰዎች ያስፈልጉኛል።

9 የተትረፈረፈ ምግብ ቢኖርም፤ የምመገበው በቀን ሁለት የመድኃኒት እንክብሎች እና ሲመሽ ጥቂት የጨው ጠብታ ብቻ ነው።

#ይህ ቤት፣ ይህ አውቶሞቢል ይህ ጀት ይህ ዕቃ በርካታ የባንክ አካውንቶች የበዛ ክብርና ዝና፣ ሁሉም ዛሬ ለእኔ እርባና ቢስ ናቸው።
#የትኞቹም የከበረ ዋጋ ያላቸው ቁሶች ለህመሜ ማስታገሻ አይሆኑም።
#እውነተኛ ሕይወት ማለት ለበርካታ ሰዎች እንዲደሰቱ እና በፈገግታ እንዲሞሉ ማድረግ ነው
ከሞት በስተቀር ምንም እውነት የለም ሕይወት እንደ ጤዛ አጭር ናት።
ስናገኝም ለሌሎች መትረፍ ይሁንልን!!!!

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
705 viewsAddisu, 09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 18:21:40 መጥላት አልወድም፡፡ ስጠላም ለምወደው ነገር ስል ነው፡፡ የምወዳቸው ነገሮች እንዳይጐዱብኝ ጐጂውን በጥላቻ ማራቅ አለብኝ፡፡ እውነተኛ መውደድ ከብዙ ቅርፊት የተሰራ ነው፡፡ አንደኛው ቅርፊት በወረት ወይንም በጥላቻ ተቀርፎ ሲወድቅ አዲስ የመውደድ ቆዳ ከስር ብቅ ይላል፡፡

ለሰው ልጅ ያለኝ ጥቅል ውዴታ የዚህ ተምሳሌት ነው፡፡ ብዙ አይነት ስም ያላቸውን ግለሰቦች ወድጄ ጠልቻለሁ፡፡ እንደ ቅርፊቱ፡፡ በሰው ልጅ ስም የሚጠራውን ማንነት ግን ልጠላው አልችልም፤ አልፈልግምም፡፡

የጥበብ ስራን እወዳለሁ፤ ስለ ጥበብ ሰሪው ግን ግድ የለኝም፡፡ የጥበብ ስራውን በመውደዴ የጥበብ ሠሪው ተወዳጅ እንዲሆን ሊያደርግልኝ የቻለ ማንም የለም፡፡...ስሪቱ ከሰሪው በላይ ነው፡፡
ከማውቀው ሰው ይልቅ የማላውቀውን ሰው የበለጠ እወዳለሁኝ፡፡ ሰውየውን ሳላውቀው እኔ ነኝ በምናቤ የቀረጽኩት፤ የተጠበብኩበት፡፡ ሰውዬውን ሳውቀው እኔ የሰራሁት መሆኑ አከተመ፡፡

የተፈጥሮው ሰው፦ ሆዳም ነው፣ ራስ ወዳድ ነው፣ ፈሪ ነው፣ ወይንም ሞኝ ነው፣ ሲያወራ ይጮሃል፣ ሲያላምጥ ይንጣጣል፣ ውሃ ካጣ ይግማማል... ማለቂያ የለውም... ወዘተ ወዘተርፈ፡፡ ከሰው ሰው ከስህተት የስህተት አይነት ይለያያል፡፡ ከጥላቻ በራቀበት እና ወደ መውደድ በቀረበበት መጠን የተሻለ ሰው ይባላል እንጂ ትክክል ግን የለም፡፡ የተሻለ ስህተት ትክክል አይደለም፡፡

የማላውቀውን ሰው እንጂ የማላውቀውን ስራ ግን ወድጄ አላውቅም፡፡ ስራውን ለመውደድ ስራውን ከሰራው ሰው ጋር ሳይሆን ከስራው ብቻ ጋር መተዋወቅ አለብኝ፡፡ መዋደድ በእዳ መልክ ግንኙነት በተቆራኙት መሀል ሊፈጥር ይችላል፡፡

የማይነጠል ቁራኛን መጥላት አያዋጣም፡፡ መውደድ ብቻ ከሆነ አማራጩ መዋደዱ የዕዳ ባህርይ የተላበሰ ይሆናል፡፡ የስጋ ዝምድና ወይንም የስጋ ዝምድናን ለመመስረት ሲባል የሚፈጠር የስሜት ቁርኝት፤ ..መውደድ.. በእዳ ...ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡ መውደድ በዕዳ እንጂ መጥላት በዕዳ ግን የለም፡፡

ጥበብን መውደድም እዳ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ በተለይ በሚያስጠላ አመት ውስጥ መውደድን ተሸክሞ መጓዝ ግዴታ ሲሆን፡፡

ሰማዩን አሁንም እወደዋለሁ፡፡ (እርግጥ ካየሁት ወደ አንድ አመት ከመንፈቅ አልፎኛል እንጂ፡፡ ቀና ብዬ ሰማዩን ባየው እንደ ድሮው በክዋክብት አበባ እና በፌንጣ ጩኸት እና በልብ ፀጥታ የተሞላ ሳይሆንልኝ ቢቀር፤ እጠላዋለሁ፡፡ ከምጠላው በድሮ ትዝታዬ ሆኜ መውደዴን ብቀጥል ይሻላል) ለውጥን እወዳለሁ፡፡ ግን የምወደው በምኞት ብቻ እንዳይሆን እሰጋለሁ፡፡ በጽንሰ ሐሳብ፣ በቲዎሪ ብቻ፡፡ ቲዎሪው ተግባር ሆኖ ለውጥ ሲመጣ ግን ሆዴን ባር ባር ይለኛል (Bar ፈልጌ ፉት እልበታለሁ)

ድሮ ያደኩት ሰፈር መንገዱ እንዴት እንደነበር ማስታወስ ተስኖኛል፡፡ መለወጡን በተስፋ ወድጃለሁ፡፡ ሲለወጥ ባዶ ሆኖ አስጠልቶኛል፡፡
መውደድ እና መጥላት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ወይ? ብዬ ግር እሰኛለሁ፡፡ ምኞትን መውደድ? ምኞቱ ተወልዶ በእግሩ ሲሄድ ለመጥላት ነው እንዴ? በምኞት ደረጃ የተወደደ ምኞቱ የተሳካ ለት ይጠላል፡፡ በምኞት ደረጃ የተጠላ በስኬት ደረጃ ይወደዳል ማለት ነው...ምን አይነት ዲያሌክቲክስ ነው ጃል? ይኼ ማለት እኮ በምኞት ..መልካም አዲስ አመት.. ያልነው ምርቃት መጥፎ አሮጌ አመት ሆኖ በእርግማን ይሸኘናል ማለት ነው፡፡

ለማንኛውም ግን ጥበብን እወዳለሁ፡፡ መጥላት የምወዳቸው ብዙ ሌላ መውደዶች አሉኝ፡፡ ግን ለጥበብ ይሄ አይሰራም፡፡ ጥበብን ስመኘውም እንደ ተግባሩ እወደዋለሁ፡፡ ጥበብን ከእውነታ ጋር ለማቆራኘት መሞከሩን ነው የምጠላው፡፡
.
ጠዋት በእግሬ እያዘገምኩ ማሰብ እወዳለሁ፡፡ የምጠላው ከብዙ ጉዞ በኋላ የሚሰማኝን ድካም ነው፡፡ ፎቶግራፎችን በሙሉ እወዳለሁ፡፡ ዘመናት ባለፉ ቁጥር ጥበብ ይሆናሉ፡፡ ባዶ ክፍል ውስጥ ከሀሳቤ ጋር መቀመጥ እወዳለሁ፡፡ ሌላ ጭንቅላት ሲያንኮራፋ በማልረበሽበት፡፡ የአሮጌ መጽሐፍትን ሽታ እና ክብደት እወዳለሁ፡፡ ቴሌቪዥን እየተመለከትኩ በቴሌቪዢኑ ውስጥ የራሴን ቴሌቪዥን ከፍቼ መመልከት እወዳለሁ፡፡

ትርጉም ያላገኘሁላቸው መውደድ እና ጥላቻዎችም በብዛት አሉ፡፡ እንዴት ልደረድራቸው፣ ወይንም ላስወግዳቸው እንደምችል ፍቺ ያላገኘሁላቸው ነገሮች፡፡ ትርጉም የዋጋ መለኪያ አንዱ መስፈርት ነው፡፡ የሰዎችን (የሰው ልጆችን) ቆራጥነት፣ ታጋይነት፣ ጠንካራነት፣ ቀዳዳ ፈላጊነት ብዙ አዎንታዊ መገለጫዎቹን እወዳለሁ፡፡ ግን አንዳንዴ ደግሞ ቆራጥ፣ ታጋይ፣ ጠንካራ የሆኑለት ነገርን (አላማን) የተሳሳተ እምነት ሲሆን እጠላለሁ፣የምወደውን ነገር ከምጠላ ግን የጠላሁትን ነገር በአዲስ እይታ ተመልክቼ ብወድ ይሻለኛል፣ ምናልባት መውደድ ከመጥላት ይሻል ይሆናል ፣ወዳጅም ደግሞ ከጠላት፡፡

            "መጥላት የማልወዳቸው"   
             ከሚል መጣጥፍ የተቀነጨበ።
                      ሌሊሳ ግርማ

              ውብ አዳር
@Addisu32

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
718 viewsAddisu, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 19:22:01 ወዳጄ ሆይ

አንዳንድ ጊዜ አጠገብህ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን በቀላሉ ሲያገኙና በትምህርት ፣ በሥራ በትዳር ... ቶሎ ስኬትን ሲጨብጡ ታያለህ። አንተ ግን አንድ ቦታ ቆመሃል። ወቅቱ የእነርሱ ነውና ከመቅናት ይልቅ ባገኙት ስኬት የደስታቸው ተካፋይ ሁን። ለእነርሱ ያደረገ አምላክ ላንተም እንደሚያደርግልህ እመን።

ይኸውልህ ፤

የማንጎ ዛፍ የቡርቱካን ዛፍን ከርሱ ወቅት ቀድሞ ምርትን ስለሚሰጥ አይጨነቅም። ስኬት፣ በወቅት የሚታጨድ መኸር ነው፣ወቅትህ ሲሆን ምንም ነገር ከመንገድህ ሊቆም አይችልም። የአንበሳ በዝግታ መራመድ ስንፍናን ወይንም ድካምን አያመለክትም፤ ያለመውን አደን በእጁ ለማስገባት እርምጃውን እያሰላ እንጂ። የሰዎች ፈጥነው መራመድ አያውክህ።

የራስህን ኑሮ ኑር!

ፈጣሪህን ታመን። ልብ በል፤ ቤትህን በፍጥነት ሠርተህ መጨረስህ ሳይሆን ንፋስና ጎርፍን መቋቋም የሚችል ጠንካራ አድርገህ መሥራትህ ነው ቁምነገሩ። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። የእውቀት ሰውና ጠንካራ ሠራተኛም ሁን! ደግሞ ሁሉንም አታገኝም!አንተ የተሳፈርክበት አውሮፕላን መሬት ሲያርፍ፣ ከዛ መሬት የሚነሣ አውሮፕላን አለ፤ ሌሎች ደግሞ ለመነሳት በሂደት ላይ ይገኛሉ። ሁሉም መዳረሻቸው የተለያየ ነው፤ ምናልባትም ወዳንተ መነሻ ሊሆን ይችላል። አየህ ህይወት እንዲ ናት፤ "ደረስኩ" ብለህ ስታስብ ሌሎች ያንን ሥፍራ "ጥለው" ሲነሱ ታገኛቸዋለህ። አንዳንዶቹ አንተ ወደ ተነሳህበት፣ ሌሎቹም ወደ ሌላ።

በልጅ ማጣት ምክንያት ቀን ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች እንዳሉ በልጆቻቸው ምክንያት ቀንና ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች አሉ፣ባል ባለማግባታቸው የሚጨነቁ ሰዎች እንደገጠሙኝ ሁሉ በማግባታቸው የሚጨነቁም ሰዎች ገጥመውኛል። በሥራ እጥረት ምክንያት የታመሙ እንዳሉ በሥራ ብዛት ምክንያት የሚታመሙ አሉ። ልጆቻቸው ፈተና ላይ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡላቸው የሚጨነቁ እንዳሉ፣ ልጆቻቸው ጥሩ ትምህርት ቤት እንዲገቡላቸው የሚጨነቁ አሉ።

እናም ወዳጄ

ህይወት እንዲህ ነው፤ በቃ! ሁሉንም የኛ ልናደርግ አንችልም!፣ ንፋስን አባሮ እንደመያዝ ነውና። ሁሉንም ነገር የራስህ እንዲሆን ከመድከም ይልቅ ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር። ከአንዱ ምእራፍ ወደ ሌላው ምእራፍ እንደሚያሸጋግርህም ፈጣሪህን ታመን። ሁልጊዜም በአምላክህ ደስ ይበልህ! በእምነትም ኑር!

     መልካምነት ለራስ ነውና

           ውብ አሁን

@selafeker

የተሰማችሁን አድርሱን  @Addisu32
1.1K viewsAddisu, 16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 17:43:31 የክህደት-ማረፊያ


የህይወት ታሪኬን...
እየገለጥኩ ሳይ..
ከእለታት አንድ ቀን አንቺን ተመለከትኩ፣
መልክሽን እንዳየሁ
የዘመናት ልቤን ለልብሽ አስረከብኩ፣
ተመልከች እንግዲ
የአንድ ቀን እይታ እድሜን ሲመግብሽ
የነገ ህይወትን
ከራስ ላይ ቀንሶ ላንቺ ሲለግስሸ
ቀናቶች፣
ሳምንቶች፤
እየተሻገሩ አዲስ ወራቶችን እኛ ላይ ፈጠሩ
የኔ እና አንቺን እውነት 
ወደ መተዋወቅ ቀርፀው አሻገሩ!
..........................................
ከእለታት አንድ ወር
የአይን ፍቅሬ ዘልቆ በልቤ ሲሰምር፣
የፍቅርሽ ቀመሩ
በኦና ልቤ ላይ ህይወትን ሲቀምር፣
ስ ት መ ለ ከ ቺ
እዝነት ወይም ፍቅር
በልብሽ ላይ ገዝፎ እኔን ስትመርጪ፣
አንድ አኔን ለማብራት
ጨለማ ህይወቴ ላይ እንደ ጧፍ ስትቀልጪ፣
የተረዳ ልቤ
ስለ ፍቅር ጥልቀት ሲሰብክ ያሳልፋል
እንደሻማ ህይወት
ለኔ ብርሀን ስትቀልጭ አመት ይቆጠራል!
....................................................
ከእለታት አንድ አመት..
ያፈቀርሹ እኔነት..
ከልብሽ ላይ ወጥቶ ጥለሽው ስትሄጂ፣
እንደሻማ ቀልጠሽ
የበራው ልቤ ላይ ስትረማመጂ፣
የፍቅርን እውነት
ከእምነቴ ላይ ፍቀሽ በይምሰል ስትፈጂ፣
አማኝ አፍቃሪሽን
ንፁህ ወዳጅሽን አንድ እኔን ስትከጂ፣
በቀናት፣
በወራት፣
እንዲሁም በአመታት፣
የተቀጣጠለ ነዶ የከሰመ የፍቅራችን እሳት፣
አንቺን ሲያጠፋ፣
አመድ እያረገ እኔን ያሻግራል ወደ እብደት ዘመናት!
.................................................
ከእለታት
ዘመናት
በሆነ አንድ ቀን ላይ የአይኔ ካንቺ ማረፍ
በሆነ አንድ ወር ላይ የልብሽ መሸነፍ
በሆነ አንድ አመት ላይ የፍቅራችን መክሸፍ
በሀሳቤ እየዋለ
ወደ እብዶች መንገድ ገፍቶ እየወሰደኝ
የተቀያየረው
ጨርቅ መሳይ ፍቅርሽ ጨርቄን እያስጣለኝ
በክህደትሽ ስካር
አንበሳ የነበርኩ'ን አይጥ አደረገኝ!
...........................................
ከእለታት ዘላለም
የክህደትሽ ክብደት
የኔን የዋህነት ታማኝነት ሰብሮ
ልክ ያለፈ ፍቅሬ
ጥለሽው ስትሄጂ ፍፁም ተቀይሮ
በቀናት ፧ በወራት
በአመታት ፧ ዘመናት የተገራ ልቤ ራሱን አፍቅሮ
የተከዳው ልቤ
ሌሎችን ይጠላል ፣ ማመን ተቸግሮ!

ጉድ ሰራሽኝ።

@Addisu32

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
866 viewsAddisu, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 00:18:14 ቀድሼ ላግባሽ

እምነ በሃ ቅድስት ቤተክርስቲያን
,.... ወስዕልት በእንቆጳዝዮን
በሚለው ቃል ዜማ ስርአት መልሼ
እባክሽን ላግባሽ ራሴው ቀድሼ:
ተንስኡ እያልኩኝ በቅድስቱ ስፍራ
በቀኖናው ድርስት  ከእግዜሩ ጋር ላውራ
በሚፈተትበት የቁርባኑ መና
ከልቤ ላመስግን የግሌ ሁኚና
የልቤ ህዋሶች በእንግዳ ስሜት
በፍሰሐ ሰክረው በተመስጦ ስሌት
በምስጋና ድምፀት የማወጣው ዜማ
የጠለቀ እንዲሆን ከሰማይ ደመና
ነጠላ አጣፍተሽ አክሊሉንም ደፍተሽ
ህግሽን ጠብቀሽ ክብርን ተጎናፅፈሽ
ካባውን ደርበን  በእምነት ኪዳን ጥላ
በፈገግታ ልይሽ የግሌ ሁኚና

የኔታ የሰጡኝ የወንጌሉ በፍታ
ጠንክሮ እንዲፀና ፍፁም ሳይረታ
በግዕዝ ባራራይ ስርአት መልሼ
'እባክሽን ላግባሽ ራሴው ቀድሼ!
የህይወቴን ምስጢር የኑሮዬን ድርሳን
ልቤን ገልጩልሽ እያዜምኩኝ ምልጣን
በክርስትናሽ ስም ፀሎትን አድርሼ
የእለቱን ምስባክ ስንክሳር ከልሼ
እባክሽን ላግባሽ ራሴው ቀድሼ!

የተላለፍኩትን የኃጢአት ደዌ
በንስሐ ስሽር በገሐድ ነነዌ
የፈጣሪ ምሕረት ላንቺም እንዲመጣ
በተክሊል ሱባዔ ከበደሌ ልንጣ
አዎ የኔ መውደድ አንቺም ተለመኚ
ገነትም ቀላል ናት ብቻ ከኔ ሁኚ!
አንድም ለኔ ፅናት አንድም ላንቺ ጸጋ
ቃልሽን ሸልሚኝ ልቤ ባንቺ ይርጋ።
ውዴ
ስብሐት ለአብ ብዬ ሠራዊት ዘልቄ
በሐሴት ሰክሬ በደስታ ጠልቄ
ተክህኖ ለብሼ ስርአት መልሼ
እባክሽን ላግባሽ ራሴው ቀድሼ!


@Addisu32
@selafeker

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
413 viewsAddisu, 21:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 00:16:52 እንጨዋወት
.
.
እስቲ እንጨዋወት እንቃርም ጨዋታ
መሳቅ ያማረው ጥርስ ይዛል በፈገግታ።
ላፍታ ሰብሰብ እንበል መራራቅ ይገታ
ቀንዳም ሽልብ ሰይጣን ሉሲፈር ይረታ።
ድንበር አጥር ይፍረስ
እንጣል ያንድነት ዳስ
ምሬት ያደረቀው
የፊታችን ቆዳ
በሳቅ እንባ ይራስ።

ዘረኝነት ጥበት
ጎሰኝነት ዝቅጠት
           መዳረሻ ይጣ
በአንድነት ማእበል
በመውደድ ነበልባል
         ይወዝወዝ ይቀጣ።
ስጋህ ከስጋዬ
ደምህ ከደሜ ጋር
        ይዋሀድ ይቀየጥ
የፍቅራችን ድርሰት
እልቆ መሳፍር ገፅ
        ዝንት አለም ይገለጥ።

ይመታ ይወገር
የሕብረታችን ማገር
በአንድ ይሰናሰን
ኑሯችን ይመስጥር።
በዚች በአሁኗ
በሽራፊ ሰአት
በስባሪ ሰከንድ
ነገያችን ይቀመር።

እንጂማ
ምን ሊበጅ ጠበንጃ
ምን ሊበጅ ምንሽር
ቁና እህል ላይሰፍር
ምን ሊበጀን መንደር
ምን ሊበጀን ሰፈር
አጥር ሰው ላይቀብር።

እስቲ እንጨዋወት እንቃርም ጨዋታ
መሳቅ ያማረው ጥርስ ይዛል በፈገግታ።
ላፍታ ሰብሰብ እንበል መራራቅ ይገታ
ቀንዳም ሽልብ ሰይጣን ሉሲፈር ይረታ።

   ማይክል ሰለሞን
      (የቡዜ ልጅ)

@Addisu32
@selafeker


https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
372 viewsAddisu, 21:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 10:18:21
ገበሬዉ ሁለቱን አህያዎች አንደኛዉን ጨዉ አንደኛዉን ባዶ በርሜል ጭኖ እየሄደ ነዉ።
ወገቡ ሊቆረጥ ደርሶ የሚንገዳገደዉ የጨዉ ኩንታሎችን የተሸከመዉ አህያ: ባዶ በርሜል የያዘዉ አህያ በፍጥነት ሲጓዝ ሲመለከት ጊዜ ከችግሩ ለመዉጣት አንድ ነገር ለማድረግ
ወሰነ።

"ወንዝ አካባቢ ሲደርሱ ዉሃ ዉስጥ በመዉደቅ ሸክሙን ማቃለል!" ከጥቂት ጉዞ በኋላ ወንዝ ጋር ደረሱና ጨዉን የተሸከመዉ አህያ እንዳቀደዉ አደረገ። እቅዱ ተሳክቶለትም ዉሃዉ በኩንታሉ ዉስጥ ያለዉን ጨዉ በከፊል አጥቦ ወሰደዉ፣ከቆይታ በኋላ ከወደቀበት ሲነሳ ከገመተዉ በላይ ሸክሙ ቀለለዉ። እንደ ጓደኛዉም ዘና ብሎ በፍጥነት መሄድ ቻለ።

ይህን የተመለከተዉ በርሜል ተሸካሚ አህያ ከመጀመሪያዉ የበለጠ እንዲቀለዉ በመሻት ልክ እንደጓደኛዉ ዉሃ ዉስጥ ተዘፈቀ።ግና ከቆይታዎች በኋላ ሲነሳ ወገብ ዛላዉ ሊቆረጥ ምንም አልቀረዉም።ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ በርሜሎቹ በዉሃ ተሞልተዉ ስለነበር የጉዞዉ እጣ-ፈንታ በብርክ፣ምጥና እንፉቅቅታ ወድቆ እየተነሳ መኳተን ሆነ።

ሌላዉ የጠቀመዉና የለወጠዉ የህይወት መንገድ እኛን ላይጠቅመን ይልቁንስ ሊጎዳን ይችላልና የሌላን ሰዉ እርምጃ ከመከተላችን በፊት ምክንያትና ዉጤቱን ማመዛዘን ይገባናል! ማንኛዉም ችግር ሲገጥመን ማንኛዉንም እርምጃ ከመዉሰዳችን በፊት አዕምሯችንን ማሰራትና ቆም ብለን ማሰላሰል ካልቻልን ለነጻነት ያሰብነዉ መንገድ የባሰ ጭንቅና መከራን ሊያመጣብን ይችላል!

በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ እኛ ዘንድ ያለዉን ጸጋ ማየት ተስኖን ዓይናችን የባተለበትን ሩቅ ማለም የነበረንን ሊያሳጣን ይችላልና ማመስገንን እልመድ! ጭፍን ተከታይነት ለራስም ሆነ ለሌላዉም እዳ እንጂ ትርፍ የለዉም!

       ውብ ቀን

@selafeker
@Addisu32
902 viewsAddisu, 07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 08:59:41
946 viewsAddisu, 05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ