Get Mystery Box with random crypto!

❤ የፍቅር ግጥም🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የሰርጥ አድራሻ: @selafeker
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.61K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 💔 ❤
💊🔮 ከፍቶሀል?🙍‍♂
ከፍቶሻል? 🙍‍♀
🚬 አስደስታችኋል ብዬ ቃል አልገባም😥 ስሜታችሁን ግን እጋራለው💔 እናም ማንም ሰው እንዲያፅናናኝ አልፈልግም 🙅‍♂
ለአድናቆት @Addisu32
Join 👇requests የሚለውን ይጫኑ 👇

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-08 15:22:32
የሰው ልጅ ሕልውና ምድር ላይ ሀ ብሎ ሲጀምር ጊዜ አሀዱ ብሎ መቁጠር እንደጀመረ ይገመታል። ምክንያቱም ሰው ከመፈጠሩ በፊትና ከሞተ በኋላ ስላለው አያውቅም፣ስለዚህ ህልውና ሲጀምር ጊዜ ጀመረ ፣ጊዜ ማለት በእጅ ውስጥ ያለ ነው። ትናንት አልፏል። ነገም ደግሞ አያስተማምንም። ስለዚህ ጊዜ ዛሬ ነው። በተለይ ደግሞ አሁን ።

ልማድ ብቻ ይዘን የትም ልንደርስ አንችልም፣ ባዶ ኩራት ይዘን እንቀራለን፣ ህልውናን መገመት ያለብን በስራ እንጂ በእድሜ: በሀሳብ እንጂ በትንፋሽ፡ በስሜት እንጅ በከንቱ የሚባክኑ ደቂቃዎች አይደለም ፣ ጊዜን የምናሰላው በልብ ትርታ መሆን አለበት።በስራ የማይገልጡትን ነገር በአፍ ብቻ መናገር ምላስን ማባለግ ነው።የባለገች ምላስ ህሊና ላይ ታምፃለች። እምነትና ድርጊት ከተለያዩ ምሰሶው በምስጥ እንደተበላ ቤት መዛግ ከዚያም መፍረስ ይመጣል ወና ቤት መሆን ነው።

ከተማራችሁት ወጣቶች የሚጠበቀው'ኮ ያገሪቷን ችግር በጥሞና አስተውላችሁ ዘላቂ መፍትሄ መሻት ነው፣ ለግልቢያውማ ማሀይምስ ብልጭ ካለበት ይጋልብ የለም እንዴ! ወደፊት ልንራመድ የምንችለው በወሬ በፍልስፍና በስራ በማይገለጥ የመፅሀፍ እውቀት አይደለም። ስርየታችን ስራ ነው፣ ስልጣን ይዞ በመኮፈስ ስልጣንን እንደ እውቀት በመቁጠር፣ ስልጣንን እንደ ሃላፊነት ሳይሆን እንደ መብት በማየት አይደለም በስራ እንደገና መወለድ ያስፈልጋል።

የኔ ጥሪ ስራ ነው። መናገር አላውቅም። ያ የጥሪ ሰዓት ሲደርስ በቆራጥነት መነሳቱ ሀጢያት አይደለም። ከማፍረስ መገንባት ፤ ከብዙ ምልልስ ትንሽ ስራን ፤ ከበቀል ይቅርታን ፤ከጥላቻ ፍቅርን ፤ ከማይምነት እውቀትን እመርጣለው።

                       በዓሉ ግርማ

          ውብ አሁን

@Addisu32
1.6K viewsAddisu, 12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 07:24:21 እውቀት ነፃ ያወጣል!

ብዙ ግዜ ዋጋ የምንከፍለው ባለማወቅ ነው! ሳናውቅ ወደ ጥፋት እንገባለን ሳናውቅ ስህተቶችን እንሰራለን ሳናውቅ እንበድላለን!

እናም ይህን ያደረጉት እኮ ስላላወቁ ነው ብሎ ስህተታችን ልክ ሆኖ አይገኝልንም ነገር ግን ከስህተትም ቢሆን መማር በራሱ ማወቅ ነው!

"ስለዚህ አለማወቃችን ሰበብ ስለማይሆንልን በተቻለን መጠን ለማወቅ እንጣር በየግዜው እንማር"

መልካም ቀን ተመኘን

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)
በየቀኑ አነቃቂ መልክቶችን ከፈለጉ ይቀላቀላሉ ይቀላቅሉ
@Addisu32

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
1.6K viewsAddisu, 04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 16:56:20

           ፍቅር መሸነፍ ነው
           ፍቅር እጅመስጠት ነው

ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው ፍቅር ከምክንያት ውጭ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው

ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጭ መሆን ነው
       ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው

ያስፈራል ፍቅር የማይታከሙት ህመም የማይጠገን ቁስል የማያባራ እንባና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል

የሚያስፈራው ያፈቀርነው ሰው ሳይሆን ማፍቀር ራሱ ነው፡

ካፈቀርክ በኀላ እኔ የምትለው ሁሉ ይጠፋል

ለራሳችን ትርፍ እንሆናለን በፈቃደኝነት ከራሳችን የምናስቀድመው የምናስበልጠው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው

    ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው
እጅ መስጠት፣ ወዶ መግባት፣ ከራስ መነጠል፣ መጥፋትና በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ነው።

  Joine and share

@Addisu32

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
2.0K viewsAddisu, 13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 08:27:46 ​​
#ፀናለሁ

ትመጣለች ብለዉ ተስፋ እያሰነቁኝ
ስንት ጊዜ ነጋ ስንት ጊዜ መሸ ሳቅ እንደናፈቅሁኝ

አንቺ ግን
በናፍቆትሽ ገመድ ታስሮ 'ሚጠብቅሽ
በእንባ 'ሚታጠበው ያው ቡቡው አድናቂሽ

እንዲሉሽ ፈልገሽ
ልክ እንደመስቀል ወፍ ታይተሽ ትጠፊያለሽ

አበቦች ሲፈኩ ደምቀሽ ትመጪና ሲከስሙ ስትከስሚ
ስጠብቅሽ ውዬ ተስፋዬ ተሟጦ ጠርቼ ገጣሚ

"በል እንግዲህ ሆዴ ካለው ተላመድ
ቢያስሩበት አያጠብቅ በስባሳ ገመድ"

የሚለውን ስንኝ ከነፍሴ እንዲያዋህድ

እንድረሳሽ ብሎ ቅኔ እየዘረፈ ስንኝ ቢያሰናኝም
እንኳንስ ሊያስረሳኝ ትዝ አልሽኝ ሲገጥም

እናም እርሳኝ ካልሽኝ መርሳቱን አልችልም
ቀሰሩብኝ ብዬ ዓለሜን አልሰጥም
አስበኝ ካልሽኝ ግን አስታውሰኝ ካልሽኝ ግን እጠብቅሻለሁ ጊዜው ለ'ኔ እስኪቆም

ዓለሜን አፅድቆ የወል ሀቅ እስኪያረግ
ውጣ ቢሉኝ ገደል ውረድ ቢሉኝ 'ረግረግ
እከተልሻለሁ ዳንኤል ነኝ አልፈራም
እወድቅ ቢሆን እንጂ ከቶ አልሰበርም .


https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
2.0K viewsAddisu, 05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 08:21:47 የማያሽር...ጠባሳ
፨።።። ።።።፨

ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ
ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ
ከልብ ውስጥ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ
ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ
ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ
አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ
ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ
ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ
ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ
ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ
.
.
.
ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን
በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን
ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ
በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።።።።።።

        
@Addisu32
https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
1.8K viewsAddisu, 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 08:20:37 ማዘኔ ብሶት ወለደ
ተደብቄ አላለቀስኩም
ቢበዛምኝ የጠላት ጦር
ቢያይልብኝ የአለም ኩርኩም
በልቤ ሲቃ ሲመረት
በጥርሶቼ ሳቅ ነገድኩኝ
ገና ብዙ ይገጥመኛል
ገና ህይወትን መች ኖርኩኝ
ብዬ ልቤን አደነደንኩ
እግዛቤር ይመስገን አልኩኝ
ገና ብዙ ገና ገና
መኖሬ ካልጠፋ በቀር
ፈተናም አይጠፋምና
እፍ ሲሉኝ ተቀጣጠልኩ
ሲያጠፉኝ ሆንኩኝ ውብ ፋና
ተገታገትኩ ተፋተኩኝ
ጥርሴን ነከስኩኝ ደፍሬ
ጌታ ያልፈራው አዳም
እስከመች ለሰው አፍሬ
ተፍጨረጨርኩ በክልሌ
በምህዋሬ ጭል አልኩኝ
የህይወት አድዋን ጀመርኩ
ያለችኝን ጠጠር ላኩኝ
የዳዊት ወንጭፋ እግዛቤር
እኔንም ደግፍ እያልኩኝ
በጣሉኝ እጥፍ ተነሳው
አትችልም ሲሉ ጎበዝኩኝ
በደፉብኝ ውሀ አበብኩ
በቃጠሉኝ ፀሀይ ፈካው
እኔ የራሴ ሚዛን አለኝ
እንዴት ነው በሰው ምለካው
ጊዜን ለመቅደም ታግዬ
ተወዳደርኩ ከማይችሉት
የነሱ ቀንበር መች ሊችል
የኔን ስቃይ ቢቀበሉት
ወዲህ ሲሉኝ ወዲያ ጠፋው
ተደብቄም አላለቅስኩ
ከአንድም ቀን በላይ አልተከፋው
አለም ወደዛዛዛዛዛዛ ሲገፈኝ
እኔ አለምን ወዲያያያያያ ገፋው
ሽልማቴን ባላቀውም ስኖር በጣም ብዙ ለፋው
መሞትማ በምን እድል
መኖር ነው ለካ እሚያስከፋው
በሞተው ህያው ስቀና ለኖረ ሁሉ እያለቀስኩ
ፈጣሪ ቻል አለኝና ለዚች ቀን ፈተና ደረስኩ
ጀምበር ወጣ በማለዳ ሰርክ ፀሀይ ስትቃና
ሳሬ ቀኑ ደስ ሲል የምል ጥቅስ የለኝምና
ከግርግዳዬ ፊት ለፊት የከተብኩት በብራና
ሁል ጊዜ እንድቆፈጥን በህይወት እንድሆን ጀግና
እንደዚ ብላ ከትማለች
።።።(<<ከባድ ነው የዛሬው ፈተና>>)።።።

@Addisu32
2.0K viewsAddisu, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 11:27:36 ሀያል ፍቅር

ያሉትን ይበሉ ተዋቸው ይናገሩ
ሲያወሩ ውለው ሲያወሩ ይደሩ

ወረኛው ቢበዛ ስራ ፈት አሳባቂ
አምላክ አለን ለኛ የፍቅራችን ጠባቂ

"እንዲ ሆነ" ቢሉ ቢመሰክሩ በየተራ
ፍቅራችን ላይቆም ምንም ቢወራ

መሰረታችን ፍቅር ነው መቼም ማይለካ
ህይወት ነው እስትንፋስ በምንም የማይተካ


       ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                  •═••• •••═•
  
     @Addisu32
      
815 viewsAddisu, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 21:24:25 ፍቅር ሲሰጥ የሚሳሳ ሠው ግን ምን አስቦ ነው እውነቴን እኮ ነው ፍቅር ያልቃል እንዴ ??
Its not only about relationship አንዳንድ ሰዎች ከገንዘባቸው ይበልጥ ፍቅር ሲሰስቱ አያለሁ... ከሰው መቀበል የምንፈልገውን ነገር መሰሰት ግን አይከብድም እንደኔ እንደኔ ከፍቅር በላይ በብዙ የምንሰጠው ነገር የለንም
                    ... ስጡ

@Addisu32
1.3K viewsAddisu, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 18:15:26
ይህ ፕላትፎርም እንዴት ነው እናንተጋ እኔ በጣም ተመችቶኛል
https://shells.work/#/pages/public/reg?invter=L357085403

በባንክ ከ 3000 ብር በላይ ከፍሎኛል 

በቪድዬ እንዴት እንደምንሰራ ከፈለጋችሁ



1.4K viewsAddisu, edited  15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 18:08:32 https://t.me/ahadu_bank_officialbot?start=r059184725
1.3K viewsAddisu, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ