Get Mystery Box with random crypto!

❤ የፍቅር ግጥም🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የሰርጥ አድራሻ: @selafeker
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.61K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 💔 ❤
💊🔮 ከፍቶሀል?🙍‍♂
ከፍቶሻል? 🙍‍♀
🚬 አስደስታችኋል ብዬ ቃል አልገባም😥 ስሜታችሁን ግን እጋራለው💔 እናም ማንም ሰው እንዲያፅናናኝ አልፈልግም 🙅‍♂
ለአድናቆት @Addisu32
Join 👇requests የሚለውን ይጫኑ 👇

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-06 08:59:16      ወዳጄ ሆይ

ያለፈ ነገር አይቀዪርም ፣ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው ፣ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር ፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነትአይገልፅም ፣ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ፣ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና ለሁሉም ጊዜ አለው ።

በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው ።በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት አይደለም ። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋሁን ፣ አስተውል ።

ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውናየሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ አታመንታ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው ።

አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ። መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው ፣ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም ።

የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አስታውስ ፣
ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።

ወዳጄ ሆይ!

ለራስህ ስትል መልካም ሁን ፣ በጎውንም አስብ። ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም ። አትፍረድ ፣ የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም ። ፍርድ የፈጣሪ ነው፣ ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል ፣ ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት ። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል ።

ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣አበረታታው፣እንደማይጠቅም አትንገረው ፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን ። መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ ነው ። መልካም ጓደኛ ፣ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል ። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።

ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን ያስከትላል ።ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ ፣መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር ፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ። አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ ።

ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር ።ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው ፣ "ያስከፍላል"ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ። ደግ ሁኑ ፣ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸው ሰላማቸው ልክ የለውም።

ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ ፣ ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም
ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል ። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው ። በራስህ በአፈጣጠርህ ደስ ይበልህ ፣ውለህ በመግባትህ ደስ ይበልህ ። በአለህ ትንሽ ነገር ደስ ይበልህ ።

ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም።  እድሜህን በተመለከተ ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው ። ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳዪኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።

የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ።

              ሰላምና ጤና ፣
ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።
            ውብ ቀን

@selafeker
@selafeker

Addisu32
1.0K viewsAddisu, 05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 12:23:59
ማንኛውም ቦታ ላይ ላለ ለሚታይ አስተማማኝ የኪንታሮት መድሀኒት

ካለ ምንም ህመም እስከ መጨረሻው የሚያሶግድ
0901043589 በዚ ስልክ ይደውሉ

@Addisu32
@selafeker
803 viewsAddisu, 09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 13:08:50
እውነትን ፣ቅንነትን ፣ ገንዘብ ከማድረግ በላይ ኮተትን ብቻ  ገንዘብ አድርጎ ህይወቱን በክህደት፣ በውሸት ፣በጥቅመኝነት ፣በአስመሳይነት በብልጣብልጥነት እየኖረ ኑሮ የበራለት የሚመስለው ሰውነት እንዴት ያልታደለ ነው።

የህሊና ፣ የቤተሰብ ሰላምና ደስታ በብልጣብልጥነት አይመጣም። ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። የምናተርፈው ነገር ቢኖር የሆነ ጊዜ ላይ የሚመጣ መጥፎ ስቃይን ነው። ያውም ለልጅ የሚተርፍ የበደል ክፍያን ነው፣የቆምን መስሎን የዘነጋን…. ሰው የዘራውን ያጭዳልና እናስተውል።

መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው፣ ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ከአንተ የመነጨና ተንደርድሮ የተተኮሰ ኃይል በእኩል መጠን እና ልክ አጥፊ እንደሆነ ሁሉ ራስህንም ያጠፍል፤ ሀሳብህን አልሚ ከአደረከው ደግሞ ቅድሚያ አንተን እና የእኔ የምትለውን ሁሉ ባርኮ ለሌሎች ይተርፋል።

መጥፎ ነገራችንን ሁሉ በመልካም ይቀየርልን

                              

            ውብ  አሁን

@selafeker
@Addisu32
     
@Addisu32


https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
782 viewsAddisu, edited  10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 20:04:19
ረመዳን ከሪም

እንኳን ለ 1444ኛው ለተከበረው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ ያጀመዓ ።

ፆሙ የፍቅር ፣ የአንድነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን ።

ረመዳን ከሪም !

@Addisu32

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
586 viewsAddisu, 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 18:57:02
እኛ ሻማዎች ነን

<<...ባንድ ምሽት ሰውዬው በባሕር ዳርቻ ባለው የወደብ ከፍታ ቦታ ትንሽ ሻማ ይዞ መውጣት ይጀምራል። በዚህ ጊዜ 'ወዴት ነው እየሄድን ያለንው?' ሲል ሻማው ጥያቄ አቀረበለት።
"እየሄድን ያለነው ከቤቱ ባሻገር ከፍ ብሎ ወደሚታየው ቦታ ነው። በዚህም ለመርከቡ የወደቡን አቅጣጫ ማሳየት እንችላለን" አለው።
"እንደምታየው የእኔ ብርሃን በጣም ውስን ናት። እንዴትስ ከርቀት ያለ መርከብ በእኔ ብርሃን ተመርቶ ወደቡ ጋር መድረስ ይችላል?" አለ ሻማው።

"ምንም እንኳ ያንተ ብርሃን ትንሽ ብትሆንም የምትችለውን ያህል ማብራትህን አታቋርጥ፣ የቀረውን ነገር ለእኔ ተውው" አለው ሰውየው። በዚህ ንግግራቸው መሀል እያሉ ከከፍታ ቦታው ደረሱና ሰውዬው ትልቁን የፋኖስ ብርጭቆ እያሳየው ሻማውን በማስጠጋት ፋኖሱን ለኮሰው። ወዲያውኑም የተለኮሰው ፋኖስ የባሕሩን አካባቢ በብርሃን ጸዳል ሞላው።

እኛ ሻማዎች ነን። ከእኛ የሚጠበቀውም የሻማነታችንን ያህል ማብራት ነው። ቀሪው የሥራችን ስኬት ላይ ፈጣሪ ይታከልበታል። የአንዲት ትንሽ ሻማ መብራት ወይም ክብሪት ጫካ ሙሉ እሳት እንደምትፈጥር ሁሉ በእያንዳችን ያለች የብርሃን ምሳሌ ስናውቅም ሳናውቅም ለሌሎች ሕይወት መለወጥ ምክንያት ትሆናለችና ብርሃናችንን ሳንሳሳላት እንድትበራ እድል እንስጣት።

ዕድገትም ቅብብሎሽ ነው። እኛ ማድረግ የምንችለውን ሰርተን ለተገቢውና ለሚጠበቅብን ስናስረክበው እሱም በፈንታው ዳር ያደርሰዋል። ሻማዋ ለፋኖሱ እንዳቀበለችው ማለት ነው። ይህ ነው፣ ለዕድገት የድርሻን መወጣት ማለት፤ ሻማነታችንን ማበርከት የሚጠበቅብንን መወጣት። >>

       እርካብና መንበር [ 117-118 ]
                      ዲራአዝ

            ውብ  አዳር

@selafeker
@Addisu32
802 viewsAddisu, 15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 17:42:51
ሁሉን ነገር ካስተዋሉት ያስገርማል , የኑሮ ትንሽ የለውም,  እዛ የወደቀችው ሳር አስገራሚ ናት  ወፍ ለቅሞ ጎጆ ይሰራባታል ።  ይሄን ሳር አጭዶ ያመጣው ማጭዱ አስገራሚ ነው  ሰዎቹ ማጭድ ማሰባቸው ?!  የሚያስገርመው ጉዳይ እልፍ ነው  .  . 
ሳሩን አጭዶ ያመጣልኝ ሰውዬ ዘገየ ይባላል , ጨዋታ ያውቃል  እሱ ሲያወራኝ የሚገርም ነው ታሪኩ  :  'ለምን ?' ብትል እንዲያው ወንድ ሆነ እንጂ ታሪኩ ተኔ አንድ ነው።

የእኔ ታሪክ ምንም ብለፋ፣ ምንም ብቀባጥር የእኔ ብቻ አይሆን  'ለካ የእሱ የእኔን ይመስላል!' ብለህ መታዘብ አለ  ...  ያንተ የአንተ ከሆነ ፣ የእናትህ የእናትህ ከሆነ፣ የሰብለ የሰብለ ከሆነ፣ እንዴት እዚህ ደረስን ? እሱ እኮ ነው!

"ጠዋት እዚህ ፀሐይ ስሞቅ የቆረጥኩት የአውራ ጣቴ ጥፍር ለስንት ጉንዳን እራት ይሆናል   .  .   ? ባላርስም አበላሁ ማለት  ነው  ?!

ትሰማኛለህ  ?  .     ሰሚ ካገኘ የማንም ታሪክ ይገርማል  !

                      

              ውብ አሁን

@Addisu32
716 viewsAddisu, 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 17:10:03 መልካም እንሁን!!!

በተቻለህ አቅም ሁሉ ለሰዎች መልካም ሁን ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ አታውቅም እና አትክፋባቸው!
ክፋ ለመሆን የተፈጠረ ሰው የለም ሁኔታዎች ግን ሰዎችን ይቀያይሯቸዋል ! የእኛ ጥሩ መሆን ግን በእነዚያ ሰዎች ህይወት ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም !

ስለዚህ በተገኘህበት ቦታ ሁሉ የጥሩነት ምሳሌ ሁን ፤ ሁኔታዎች አይገድቡህ የበላያቸው ሆነህ አስደንግጣቸው !!!

አዲሱ የጎሀው
11/07/2015

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
754 viewsAddisu, 14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 15:13:23 እንዳትፈራ!!!

ለምንድነው የምትፈራው ? ምን ላለማጣትስ ብለህ ነው ከመንገድህ የቆምኸው? ማድረግ የምትፈልገውን ነገር ላለማድረግ ምን ገደበህ?

አለም ላይ የተሰጠህ እድሜ በሙሉ ያንተ ውድ ስጦታ ነው ! እያንዳንዷን ግዜህን በፈለግኸው መንገድ ልትጠቀምባት ተፈቅዶልኋል የምታደርገውን ማወቅ ያንተ ድርሻ ነው!
ብትከስር እንኳን መነሳት ትችላለህ ብትወድቅም ድጋሚ ከፍ ማለትህ አይቀርም ስለዚህ ወንድሜ ባታደርገውም የሚሆነው መሆኑ አይቀርምና ወደፊት መራመድን አትፍራ !

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
1.3K viewsAddisu, 12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 01:24:48 ቢላ ካልተሞረደ ዶልዱሞ እንደሚቀር ሁሉ የሰውም ልጅ ጠንካራና ብልህ እንዲሆን በተለያዩ ውጣውረድ ማለፍ ግድ ይለዋል።እኚ ውጣውረዶች በሕይወታችን ውስጥ መከሰታቸው ተፈጥሯዊ ነው፣ እኛኑ ለማጎበዝ እኛኑ ለማንቃት እኛኑ ለማጠንከር እኛኑ ለማጀገን ነው ፣የዶሎዶመ ቢላ ለመቁረጥ ከማስቸገርም አልፎ ድካም ነው የሚሆንብን እንጂ እንደተመኘነው አይቆርጥልንም።

ያልተፈተነ ማንነትም ከተራራው ጫፍ የሚያደርስ ጽናትን አያላብሰንም። እውነታው መሞረድ ነው እውነታው መሳል ነው፣እውነታው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ማለፍና ራስን ማጠንከር ነው። የሰው ልጅም ዛሬ በሁኔታዎች እራሱን እየፈተነ ማንነቱን ያጠነክራል። ዛሬ በሁኔታዎች ልቡን እያጠነከረ ለነገው ይዘጋጃል፣ዛሬ በሁኔታዎች መንፈሱን እያጠነከረ የወደፊቱን መንገድ በቀላሉ ያቅዳል።

ውስጣችንን አጠንክረን የገባንበትን ፈተና በድል እንወጣው። ቁስላችን ስብራታችን ውድቀታችን ሁሉ ያጠነክሩናል እንጂ አይገሉንም፡፡

          ውብ  አዳር

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
1.1K viewsAddisu, 22:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 01:19:39 ከሰው አትጠብቅ !!!

ለችግርህ ጊዜ የራቁህ ለስኬትህ ዙሪያህን ቢከቡህ አትደነቅ፤ በከባዱ ጊዜህ ትዝም ያላልከቸው በምርጡ ጊዜ ፍቅር በፍቅር ቢሆኑ እንዳይገርምህ።

የዛሬም ሺ አመት ሰዎች እንደዚህ ነበሩ፤ ዛሬም ነገም እንዲህ ናቸው። ስለዚህ ከሰው ምንም አጠብቅ! ከፈጣሪህ ቀጥሎ ራስህን እመነው! ራስን እንደመጠራጠር ህልም ገዳይ ነገር የለም!

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
1.1K viewsAddisu, 22:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ