2022-07-05 19:26:59
#መስዋዕትነት
ክፍል
"ማለት? በምን ምክንያት ማለቴ እንዴት?...."
"ሌላውን ቀስ ብዬ እነግርሻለው ምክንያት ላልሺው መልሱ አንቺ ነሽ..."
" ማለት ምን እያልከኝ ነዉ ያለኸዉ" አልትኩት ግራ ገብቶኝ አይን አይኑን እያየሁት
ሊያዬ በሽታሽ ላንቺ እንደተነገረሽ ቀላል አልነበረም፡፡ የሆነ ጊዜ ትምህርት ቤት ራስሽን ስተሸ ከደረጃ ላይ እንደወደቅሽ ታስታዉሻለሽ አይደል፡፡ አንገቴን በአወንታ ነቀነኩለት፣ (እንዴት አላስታዉሰዉም ለሁላችንም ከባድ የሰቆቃ ጊዜ ነበረ፡፡ ፡፡ በወደኩ ሰዓት እጄ ወልቆ ያልሄድኩበት ውጌሻ አልነበረም እትዬ ዘይነባ ከሄዱበት ሀገር እስኪመለሱ። እትዬ ዘይነባ የታውቁ የሰፈራችን ወጌሻ ናቸው ውልቃት ይሁን ስብር ዘይነባ ጋር መፍትሄ አለው... ከሳምንት ጭንቅ በኋላ መጡልኝ እና ከነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ትግል ብኋላ ግጭ አድርገው ወደነበረበት መለሱት.... )
"በዛን ሰዓት ልብሽ ከፍተኛ የሚባለዉ ደረጃ ላይ ደርሶ ስለነበር በሶስት ወር ዉስጥ ሄደሽ ካልታከምሽ እንደምትሞቺ ለቤተሰቦቺሽ ተነገራቸዉ፡፡ መሲም የተፈጠረዉን ሁሉ መጥታ ነገረችን፣ ያላደረግነዉ ነገር አልነበረም መሲ ሻርፕ አንጥፋ እስከመለመን ደርሳ ነበር፤ ግን ተለምኖ እስከሚሰባሰብ አንቺ ልትሞቺ ሆነ፡፡ ሁላችንም ተጨንቀን ባለበት ሰዓት መሲን አባትሽ ደዉሎ ጠራትና አዲስ አበባ ሄደች…"
"ቆይ አንዴ እናንተ ይሄን ያክል ከለፋችሁ እስከማዉቀዉ እነ አባቢም ዝም ብለዉ አልተቀመጡም… እንዴት አምስት መቶ ሺህ ብር ሳይሞላ ቀረ"
"ለህክምና የሚያስፈልግሽ አንቺ የምታዉቂዉ አምስት መቶ ሺህ ብር ሳይሆን 1.2 ሚሊዮን ብር ነበር… "
"ምምምምን... እንዴት ሳይነግሩኝ ማለቴ እኔኮ የማዉቀዉ…"
"ያልነገሩሽ አንቺ እንዳትጨነቂና ተስፋ እንዳትቆርጪባቸዉ ነበር… ብዙ ለፉ የየሰዉን ደጅ አንኳኩ አባትሽ አለኝ የሚሉት ጓደኛቸው አቶ ደምሴ ጋር ሄዱ፤ 'ከዚህ ቀደም እንደነገርኩህ ነው ልጅህን መሰረትን ዳርልኝና ሙሉ ወጪዋን ችዬ አሳክምልሀለሁ' አሏቸው ። ነገሩ ሁሉ ከአቀማቸዉ በላይ ነበር፡፡ እያዩሽ ወደሞት ልትሄጂባቸዉ ሆነ" በረጂሙ ተነፈሰና ከአልጋዉ ተነሳ
"እስኪ የሆነ የሚቀመስ ነገር ካለ ታች እንዉረድ" አለኝ እጄን እየያዘ
"ይሄንን ጉዴን ነግረኸኝ ሳትጨርስ የምን ምግብ በዛ ላይ በዉድቅት ሌሊት..."
"ልክ ነሽ ሊያዬ ግን ራትም አልበላዉም በዛ ላይ አንቺም …" ንግግሩን ሳይጨርስ አቋረጥኩት
"በቃ እሺ እንደዛ ከሆነ ሂድና በልተህ ና እኔ እዚሁ እጠብቅሀለሁ" ምንም ሳይለኝ ወደታች ወረደና ትንሽ ቆይቶ ሁለት የታሸገ ምግብ ይዞ መጣ፡፡ አንዱን ለኔ አቀበለኝና "መጀመሪያ እንብላ ካለዛ አልነግርሺም" አለኝ ፈገግ እያለ በፈገግታዉ ዉስጥ ለኔ ምን ያክል እንደሚያስብልኝ ተረዳዉ፡፡ ፍላጎቱ ባይኖረኝም የሰጠኝን ምግብ ትንሽ በላሁና እሱ እስከሚጨርስ ጠበኩት፡፡
" እሺ ከዛስ" አልኩት እንደጨረሰ
"አማራጭ ሲያጡ የመጨረሻዉን አማራጭ ለመጠቀም ተገደዱ እሱም መሲን ከአባትሽ ጓደኛ ከአቶ ደምሰዉ ጋር ማጋባት እና ብሩን መቀበል"
"እና! መቼም አደርገዉት ነበር አትለኝም…"
" እሱን ልነግርሽ አይደል … ለሁሉም የቀረዉ የመጨረሻ ምርጫ ይህ ነበር፡፡ መሲ ህመምሽ ሳይብስ በፊት ነገሩን ሰምታ ነበር እናም እንደሰማች ከአባትሽ ጋር ከፍተኛ ጥል ዉስጥ ገብተዉ ነበር..(አስታወስኩ የደበቁኝ ሚስጥር ሁሉም ነገር አንድ በአንድ እየተገለፀልኝ መጣ) ለነባም ነግራዉ ነበር፡፡ ምናልባትም ነባ በህይወቷ ዉስጥ ባይኖር ብታጣ ትምህርቷን ማቆም እና የአንድ ሽማግሌ ሰዉዬ ሚስት መሆን ወይም እንደ ሁኔታዉ የማትወደዉን ሽማግሌ አግብታ መማርን ትመርጥ ይሆናል፡፡ የነባ መኖር ግን ህይወቷን ከባድ አደረገባት...
አባትሺም የጠሯት ለዚሁ ጉዳይ ነበር፤ አወሩ እና ዉሳኔያቸዉን ወሰኑ እሱንም አሳወቋት፡፡ 'ከአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ደምሰዉን ታገቢዋለሽ የሰርጋችሁ እለት ብሩን ሊሰጠን ተስማምቷል ከዛ በኋላ ያለዉ ያንቺ ዉሳኔ ነዉ ብቻ እህትሺን አድኛት ይሄ አይሆንም የምትዪና ለሰርጉ ከጎንደር የማትመጪ ከሆነ የኔና ያንቺ አባትና ልጅነት ያበቃለታል፡፡ እህትሺን የቀበርኩ እለት ባትሞቺም በሀሳቤ እቀብርሻለሁ' ቃል በቃል እንደዚህ አሏት መሲ አማራጭ አልነበራትምና ተስማምታ ወደኛ ተመለሰች ግን በድኗ ነበር የተመለሰዉ ወር ሙሉ ጠጣች… ጠጣች… ጠጣች… ብዙ ሰከረች ነባም ተባባሪዋ ሆነ ይጠጣሉ የሆነ ቦታ አልጋ ይዘዉ ያድራሉ፡፡ ታዲያ በዚህ መሀል ያለጥንቃቄ ወሲብ እንደሚያደርጉ እኳን ማስተዋል አቅቷቸዉ ነበር፡፡
የሆነ ቀን አብረን ምሳ እየበላን መሲ ልትጎርሰዉ ያለቺዉን ምግብ እንዳንከረፈፈች በሀሳብ ሄደች እያየኋት ነበር፤ እጇ ላይ ያለዉን ምግብ ጣለቺዉና ወደ ነባ አፈጠጠች አሱም ግራ ተጋብቶ አያት… ተነስታ እጁን እየጎተተች ይዛዉ ወጣች ትንሽ ቆይተዉ ተያየዘዉ ተመለሱ 'ምን ተፈጥሮ ነዉ መሲ ሰላም አይደለም' አልኳቸዉ፡፡ 'ባክህ መሲ ሳታረግዝ አትቀር…'
ተናግሮ ሳይጨርስ አቋረጠችዉ 'አንተ ባልተረጋገጠ ነገር እንደዚህ አትበል ገና መች አወቅን' እንደዛ ከሆነ ተነሱ ሀኪም ቤት እንሂድ ብዬ ተያይዘን ወጣን… ምርመራ ተደረገላት እዉነት ነበር መሲ የሶስት ሳምንት ነብሰ ጡር ናት...
ይቀጥላል....
አሪፍ አሪፍ ግጥም እና ታሪክ ለማግኘት
@Addisu32
@selafeker
@selafeker
4.3K viewsAddisu, 16:26