Get Mystery Box with random crypto!

❤ የፍቅር ግጥም🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የሰርጥ አድራሻ: @selafeker
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.61K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 💔 ❤
💊🔮 ከፍቶሀል?🙍‍♂
ከፍቶሻል? 🙍‍♀
🚬 አስደስታችኋል ብዬ ቃል አልገባም😥 ስሜታችሁን ግን እጋራለው💔 እናም ማንም ሰው እንዲያፅናናኝ አልፈልግም 🙅‍♂
ለአድናቆት @Addisu32
Join 👇requests የሚለውን ይጫኑ 👇

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-12 18:37:58 መስጠት

የፈጣሪ የሒሳብ ቀመር ደስ የሚለው አንተ ስታካፍል እሱ አየደመረ እያባዛ መስጠቱ ነው። የተሰጠህን ስጦታ ለራስህ ብቻ ባስቀረኸው ቁጥር እንዳይጨምር እያረከው መሆኑን ሁሌም አስታውስ።

ወዳጄ የምትሰጠው ገንዘብ ብቻ አይደለም፤ ለምትወዳቸው ጊዜህን ስጣቸው! ለተጨነቁ ጆሮህን ስጥና አድምጣቸው! ግራ ለገባቸው ሀሳብህን አካፍላቸው! ያኔ ባለህ ገንዘብ፣ ዕውቀትና ጥበብ ላይ ብዙ እጥፍ ሲጨመርልህ ታይና በግርምት እጅህን አፍህ ላይ ትጭናለህ።

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ
https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0 join
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

ለአስተያየት @Addisu32
1.4K viewsAddisu, 15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 00:02:06 ውዴ..!

መልክሽ ይገርጣልሽ ፤ ውበትሽ ይጠንዛ
አንቺነትሽ ይርገፍ ፤ ብጉር ፊትሽ ይብዛ
ጥፍርሽ ዱምዱም ይሁን ፤

ፀጉርሽም ይጠር
ሰላም ሚልሽ አይቶ ፤ ደንግጦ ይሰበር 
አይንሽ ፈጦ ይውጣ ፤
አፍንጫሽም ይርዘም
መልከ #ጥፉ ሁኚ ፤ የሚያይሽም የለም።

ከዛ...

አንቺን መሳይ ፉንጋ ፤ ሁሉ #ስለሚሸሽ
እንዲ ያርግሽና ፤ #ብቻዬን ላፍቅርሽ!

እወድሻለሁ

ሼር 
https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
163 viewsAddisu, 21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 23:57:19
ጥርሳቹ እስኪረግፍ መሳቅ ከፈለጋቹ ከስር ባለው ሊንክ ገባ ገባ በሉ


https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
178 viewsAddisu, edited  20:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 23:25:51 ጥርሳቹ እስኪረግፍ መሳቅ ከፈለጋቹ ከስር ባለው ሊንክ ገባ ገባ በሉ
https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
232 viewsAddisu, 20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 21:27:04 ዕድሌ ነው...
(መላኩ አላምረው )
.
ዕድሌነው...
በሚስትልወሰን፣ እኔ ትዳር ሲያምረኝ፤
ሳታገባ 'ምትቆይ፣ አንድም ሴት አትገኝ
.
ዕድሌነው...
እኔዲግሪ ስይዝ፣ ዲግሪ ዋጋ ያጣል፤
ገንዘብ ያለው ሁሉ፣ ዶክትሬት ያመጣል
.
ዕድሌነው...
እኔመድረክ ስይዝ፣ ይፈታል ጉባኤ፤
እኔ መጾም ሲያምረኝ፣ ይሆናል ትንሣኤ።
.
ዕድሌነው...
በቁርባንለመኖር፣ ንሰሐ ስገባ፤
አቁራቢው ፖትልኮ፣ ቤተመንግሥት ገባ።
.
ዕድሌነው...
እኔኳስ ስገዛ፣ ሜዳው ይታረሳል፤
እኔ ቤት ሲኖረኝ፣ ሰፈሬ ይፈርሳል።
.
ዕድሌነው...
ለተሾመሁሉ፣ እንዳልኖርሁ ስለፋ፤
እኔ አለቃ ስሆን፣ የሚታዘዝ ጠፋ።
.
ዕድሌነውና...
ከዕለታትአንድ ቀን፣ መንገሤ ባይቀርም፤
እኔ ንጉሥ ስሆን፣ ሀገሪቱ አትኖርም። 


𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 በ ፍቅር
@Addisu32

@selafeker2

@selafeker
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
661 viewsAddisu, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 21:16:13

➥ፍቅር የራሱ የሆነ ውበትና ዜማ አለው
ያፈቀረ እንጂ ማንም የማይሰማውღ
............. ..............

⇘ፍቅር እንደ ጦርነት ነው፤ ለመጀመር
ቀላል ነው፤ ግን ለመጨረስ በጣም
አስቸጋሪ ነው።

    ❝ዓይኖቼን ጨፍኜ አንቺን አስባለሁ፤
      ዓይኖቼን ገልጨ አንቺን አስባለሁ፤    
         አንቺም እያሰብሽኝ እንደሆነ
             ማወቅ እፈልጋለሁ።❞

     ➦አምነህ ልብህን ለሰጠኸው ከዛም
     በከዳህ ሰው ላይ ፈፅሞ እንዳታዝን፤
     ምክንያቱም ሰውየው አንተን ሳይሆን
     እራሱን ነውና የከዳው፡:

⇘ፍቅር ምን እንደሆነ ስታውቅ ነው
ለዋጋው መስዋዕት የምትከፍለው።
          
            
𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 በ ፍቅር

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
704 viewsAddisu, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 20:21:40 ደግ ሁን

የምትችል ከሆነ ከማንም የበለጠ ደግ ሁን ቢሆንም ደግነትህን አትናገር

ስለተረፈህ ሳይሆን ሰብአዊነት ኖሮህ ላንተ ከሚያስፈልግህ ላይ ሳትሰስት ለሌሎች አካፍለህ ኑር

መስጠት የማያውቁ ሰዎች ሌሎች ሲሰጡ ይታመማሉ



@Addisu32

Share በፍቅር

https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
1.6K viewsAddisu, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 20:13:43 ጨረቃ ስትወጣ ከጎኔ ቁጭ ብለሽ
በዓይኔ አይሻለው……
ከዋክብት ሲጓዙ ከነሱ መካከል
አንቺን ፈልጋለው……
ከፀሃይ ጋር ብትወጪ ብዬ
ሁል ጊዜ ጠዋት እጠብቅሻለው
አንዳንዴም በህልሜ አቅፌሽ አድራለው።
ዝም ብለሽ በሀሳቤ ሁሌ ትመጪያለሽ
ምክንያቱን ባላቅም ትናፍቂኛለሽ
ያነጫንጨኛል ላገኝሽ እሻለው…
በሰበብ አስባቡ ስላንቺ አወራለው
የፅድቄ ሽልማት የኔ ገነት ውዴ
ኧረ ጉዴ ፈላ…ፍቅር ያዘኝ እንዴ


𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 በ ፍቅር

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
1.5K viewsAddisu, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 20:10:23 አንዳንዴ
አያድርስ ነውና የጓደኛ ምክር
በፍቅርህ እንድትወድቅ
ቀልድላት አሉኝ በቀልድ አንድትሰክር
ቀለድኩልሽ ቀልዴን
ጨረስኩልሽ ቀልዴን
ምን የቀረኝ አለ
ጥርስሽን ሳይ ገና ልቤ ኮበለለ

ልገዛሽ ያልኩትን መልሰሽ ገዛሽኝ
       በጥርስሽ ለከፍሽኝ
ምትይኝ አይገባኝ ይህንን አውቃለው
ስትስቂ ካየሁሽ አብሬ እስቃለው
.
.
.
ቀፋቀርን
ብዙ ጊዜ አለፍን
.
.
.
አብረን ባለን ጊዜ
ቀልደኛ ነህ ብለሽ በፍቅር ዘፍቀሽኝ
ምነው ታድያ ዛሬ
ቀልዴን ሳወራልሽ ቁምነገር የለህም ብለሽ የገፋሽኝ

ቁምነገሬን ሁሉ በቀልድ ሳወራልሽ
           ከት ብለሽ ስቀሻል
አይንሽ እስኪቀላ
ፊትሽ እስኪቀላ
           በሳቅ እረክተሻል

የሳቅሽበትን ቀልድ ቁምነገር መሆኑ
         ደርሶ አንቺን አይገባሽ
ይብላኝ እንጂ ለኔ ለምብሰለሰለው
         አንቺን ለማነባሽ

#ሊቀጥል_ይችላል

ለኔ ቁም ነገሩ
በሳቅሽ መስከሩ
1.3K viewsAddisu, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 19:17:18 ሕይወት በሚታይና በማይታይ ማዕበል የተከበበች ናት!

ሰው ሃሳቡ በግንባሩ ላይ ቢጻፍ ማን ማንን ቀና ብሎ ያያል? ደግነቱ በውስጣችን ያለውን ማንም አያውቅብንም። የምናስበውን አስበን፤ የፈለግነውን አሳውቀን የምንደብቀውን ደብቀን የመኖር ጥበቡ ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ ጥበብ ነው። ልብ በሃዘን ደምቶ ፊት በፈገግታ ሲፈካ ፤ ግንባር ኮስተር ብሎ ልብ በሃሴት ሲሞላ ፤ ጉልበት ተንበርክኮ ልብ በትዕቢት ሲቆም ፤ አፍ እንደ ማር ጣፍጦ ልብ እንደ እሬት ሲመር ፤ ማን ማንን ያውቃል ያሰኛል?!

የሰው ልጅ በሚታየውና እና በማይታየው ማዕበል ውስጥ ያልፋል፤ የሚታየው ማዕበል ሌሎች የሚረዱት እና የሚያዩት ችግራችን ሲሆን፤ የማይታየው ማዕበል ደግሞ ከሌሎች ደብቀን ለብቻችን የምንጋፈጠው ችግር ነው”።

ሌሎች የማውቁት ምን አይነት ጭንቀት ይሆን እያንዳንዳችን በውስጣችን ያለው? ምን አይነት የማይታይ ማዕበል እየተጋፈጥን ይሆን?

አዎ በሰው ፊት እንስቃለን ለብቻችን ግን እንባችንን በገዛ መዳፋችን ያለማቋረጥ እናብሳለን። ከሰው መሃል ደምቀን ለብቻችን ስንሆን መግቢያ እናጣለን። ከህዝብ ፊት ከብረን በቤታችን ግን የሰው ያህል የሚቆጥረን የለም። ጠንካራ መስለን፤ ልባችንን ግን በክህደት ስብርብሩ ወጥቷል። ከላይ ሰላም የሰፈነብን እንመስላለን፤ ውስጣችን ግን በተስፋ መቁረጥ ማዕበል ይተራመሳል። ከውጪ ሲታይ ቤታችን የደመቀ ቢመስልም ውስጡ ግን እንደ ዋሻ ቀዝቅዟል። ተለቀም አነሰም ሁላችንም ለሌሎች የማይታይ ለብቻችን የምንጋፈጠው ማዕበል አለን።

እናም በየመንገዳችን ስንተላለፍ ልብ እንበል፤ ሌላው ከኛ ያነሰ ትግል የሚታገል እየመሰለን ፊት አንንሳው፤ እየረገጥን አንለፈው። የኔ ችግር እና ጭንቀት ከሌላው ይበልጣል የሚል አስተሳሰብ ሲኖረን ለሌሎች የምንዘረጋው እጅ ያጥረናል። ትኩረታችን ሁሉ የራሳችን ችግር ላይ ሲሆን ይበልጥ እናማርራለን፤ ሌሎች ለብቻቸው የሚገፈጡትን ማዕበል ስለማናይ “ምነው እኔን ብቻ” እያለን የሃዘናችንን ጉድጓድ ይበልጥ ወደታች እንቆፍረዋለን።

ከትዳር አጋራችን ጋር ክንድ ተንተርሰን እያደርን፤ እርስ በርሳችን የምንፋለመውን ትግል አናውቅም። ለዚህ ነው ጭቅጭቅ ሲነሳ መሸናነፍ እና እርቅ ማውረድ የሚከብደን፤ ማን የማንን ማዕበል ያያልና? እናም በየመንገዳችን የሚያጋጥሙን ሰዎች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ታሪክ አላቸው፤ በጫማቸው ሳንቆም አንፍረድ። በደቂቃ ውስጥ ያየነውን ምግባራቸውን ተንተርሰን አንፍረድ።

ሌላውም እንደኔ ስሜት አለው የሚል አስተሳስብ መያዝ ስንጀምር፤ የሌላው ህመም ይሰማናል እናም ብዙ ስህተቶችን ከመፈጸም እንድናለን። ምናልባት ለብቻሽ/ ለብቻህ የምትጋፈጠው ማዕበል ካለህ በርታ… አጋዥ የለኝም ብለህ አትስጋ ፈጣሪ የማትችለውን ችግር አይሰጥህም። አንተ/አንቺ ብቻ ከሰው የተለየ መከራ አልተሰጠሽም/አልተሰጠህም እንደየአቅማችን ለሁላችንም የታደለን ነው እንጂ……ከምንም በላይ ግን እርስ በርሳችን እንተጋገዝ፤ እየተገፈታተርን መተላለፉን እናቆም ምክንያቱም ሁላችንም ለየብቻችን በምንጋፈጠው ማዕበል ደክመናልና።

                      

            ውብ አሁን


@Addisu32
@selafeker

https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
1.5K viewsAddisu, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ