Get Mystery Box with random crypto!

❤ የፍቅር ግጥም🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የሰርጥ አድራሻ: @selafeker
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.61K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 💔 ❤
💊🔮 ከፍቶሀል?🙍‍♂
ከፍቶሻል? 🙍‍♀
🚬 አስደስታችኋል ብዬ ቃል አልገባም😥 ስሜታችሁን ግን እጋራለው💔 እናም ማንም ሰው እንዲያፅናናኝ አልፈልግም 🙅‍♂
ለአድናቆት @Addisu32
Join 👇requests የሚለውን ይጫኑ 👇

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-29 09:57:44
@Addisu32
3.3K viewsAddisu, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 20:43:22
ከስሞች ሁሉ ምርጥ ስም  ከሰው ልጅ ከናፍራት ከወጡ ውብ ቃላት አንዱ " እናት" ነው ።

የጥሪዎች ሁሉ ምርጡ  ጥሪ " እማ" ቃላቱ በፍቅር , እና ተስፍ የተሞላ ነው ፣የምትጣፍጥ ቃል ከሰው ልጅ ጥልቅ ልብ የወጣች ናት።እናት ሁሉ ነገር ናት  ፣ በችግር ሰአት አማካሪያችን ናት በጭንቀት ሰአት ተስፍችን ናት በድክመት ሰአት ጥንካሪያችን ናት  እሷ እኮ የፍቅር , የእዝነት , የርህራሄ, ምንጭ ናት።

እናት እንደ መሬት ሁሉን ቻይ ናት። ብትረገጥ ታግሳ ለወግ ማረግ ታበቃለች። ብትነቀፍና ብትተችም ፈገግታዋ አይከስምም። የዘሩባትን መልካም አድርጋ እንደምታበቅል እርሻ ልበ ንፁሁ እንዲሁም መልካም ፍሬ እንደምታፈራ ዛፍ አብራኳ ለምለም የሆነ የውበት የምጨረሻዋ ምእራፍና የመጨረሻዋ እውነተኛ ዓረፍተ ነገር ነች እናት። ልቧ ከፍቅር ድርና ማግ የተሸመነ ነውና ምን ቢያስቀይሟት የጥላቻ ጥርስ አትነክስም። ፊት ቢነሷት ፊት አትነሳም ።

ሰው የመሆን የመጨረሻው ደረጃ ነው። ቅድስና በእናትነት መንገድ የሚደረሰበት የህሊና ንቃት ነው።  እናት  የፍጥረት ሁሉ የመጅመሪያ ምሳሌ ናት ሙሉ የሆነ ውበት እና ፍቅር ተምሳሌት ናት  ከሁሉም በላይ እናት የሚተመንላት ዋጋ የላትም፡፡ ከዋጋ በላይ ናትና።

የእናት ፍቅር የመጨረሻዋ የፅድቅ ፅዋ ነች።

    ውብ ምሽትን ተመኘሁ
                  
@Addisu32

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
3.8K viewsAddisu, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 18:21:48 ከራስህ ጋር ብቻ!!!

በህይወት ሩጫ ውስጥ የሚያሸንፈው ቀድሞ የደረሰ ብቻ አይደለም ውድድሩን የጨረሰም ነው። የግድ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ቀድመን ወይም እኩል መድረስ አለብኝ ብለን ራሳችንን ማስጨነቅ የለብንም።

ራሳችንን ካወዳደርን አይቀር ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከትላንቱ ማንነታችን ጋር መሆን አለበት። ስኬት የሚለካው በራስ መነፅር እንጂ ከሌሎች ጋር ባለን ንፅፅር አይደለም።



https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
5.2K viewsAddisu, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 17:52:02
ወዳጄ ሆይ መቆም ከፈለክ ሌሎችን አትጣል

የምትሔድበት የስኬት መንገድ ሺህ ጊዜ ይርዘም እንጂ ቶሎ ለመድረስ ብለህ አቋራጭ መንገድ አትጠቀም። ልብህ በእውነት ላይ ተረማምደው በሰዎች ትከሻ ላይ ተንጠልጥለው ፣ በአቋራጭ ባደጉ ሰዎች እንዳይቀና! የግፍንም እንጀራ እንዳትበላ ተጠንቀቅ ፣ትግስትን ገንዘብህ አድርጋት አምላክ ለአንተ ያዘጋጀዉ ነገር አለውና። በዕውነት ፣ በሃቅና በራስ አገዝ አዋጭ መንገድ ከተራማድክ እመነኝ በያንዳንዱ እርምጃህ ስኬትህን እየገነባህ ነው።

ሀሴትህ በቀናነትህ መጨምር ይበዛል፣ ከክፋት ትርፍ አይሰበሰብም፡፡ የምትሆነው ብታጣ እንኳ ጨካኝነትን ብቸኛው ምርጫህ አታድርግ፡፡ የሚመረጥ ስላጣህም የማይመረጥ አትምረጥ ፣ የምትመርጠው ከሌለ አለመምረጥም ጥሩ ምርጫ ነው፡፡ ማስተዋልህን ባለማስተዋል አትጠቀምበት፡፡

ወዳጄ ሆይ

ከብረህ ሳለም ቀለህ መኖርን አትውደድ፡፡ በከፍታ እንጂ በዝቅታ እያሰቡ መኖር አይመጥንህም ጭካኔ የሕሊና ሰላምህን ያቀነጭራል፡፡ የውስጥህንም ሰላም ያመክናል፡፡ጊዜአዊ እንጂ ዘላለማዊ የዚህች ምድር ነዋሪ አይደለህምና በደጉ ጊዜህ መሰልህን አትበድል፡፡

ነገ የአንተ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን በውል አታውቅምና ነግ በእኔ ማለትን እወቅ፡፡ በቁንጮነት ዘመንህ የፍጡራንን መብት አትግፈፍ፡፡ የሌላው ውድቀት የአንተን መቆም አያረጋግጥምና ፣ መከራ በታጨቀባት በዚህች ጠፊ ዓለም መልካምነትን የመሰለ ሰላም ሰጪ ተግባር የለም፡፡ በመሆኑም ዛሬህ ላይ ነገ የማትፀፀትበትን ምግባር አብዛ፡፡

ነፃ የሆነ ነፃነት እንዲሰማህ ፤ በጭንቀት የታጨቀ ኑሮህን በቅንነት ቀይር፡፡ ከሁካታ እርካታ አይመነጭም እፎይታ ለሚሰጡህ ተግባሮች ራስህን ስጥ፡፡

         ውብ ምሽት

@Addisu32


https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
5.4K viewsAddisu, 14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 00:39:25 አንድ ቤት እያለን ከሰማይ ደመና
ደርሰን የምንታይ ስማችን ገናና
ታሪክ አደረገን የሚለያይ መንፈስ
ቤታችን ገባና
ምን ችግር ነበረው ለየብቻ መቆም
ምን ችግር ነበረው ለየብቻ መኖር
እኛን ቢጠቅመን
እርዳታ ጠባቂ ሁነን ባልቀረን
የሁላችን ችግር ለየብቻ ሁነን
ከሌላው ለማትረፍ ለየብቻ መክረን
ከፊት የነበርነው
በጥላቻ ሰክረን ከሰው ኋላ ቀረን
በጥላቻ ሰክረን በጥላቻ ታስረን
መቆም ከብዶን
ትናንሽ ቤት ሰርተን ለመኖር አቅቶን
አሁንም ጥላቻ
መጥፎ እያስታወስክ ቁስልን መነካካት
ሌላውን ወንጅለህ እራስህን ማፅዳት
አሁንም ጥላቻ
ክፋት እያነሳህ መጥፎ መጥፎ ብቻ
ወንድምን ለመግደል ፉከራና ዛቻ
ወገን ይበቃናል ይብቃ መገዳደል
ወንድም ወንድም ገድሎ ዳሱ የት ይተከል
ቆም ብለን እናስብ
እንዲው ስንናከስ እንዳንገባ ገደል
ያተረፈ ካለ አንደኛው ሲበደል
መጣላት አደለም አይበጀንም ድንበር
ከዓለም ፊት የሚቆም የሰሩትን አገር
በአባቶቻችን ወግ እስቲ እንነጋገር


               



𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 በ ፍቅር

━━━━━━✦✗✦━━━━━━
https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
5.6K viewsAddisu, 21:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 16:48:47 https://www.tiktok.com/t/ZM2ewx8KP/
1.4K viewsAddisu, 13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 20:14:02 ክብሬ ሞገሴ ነሽ እምዬ እናቴ
የህይወቴ ፅላት የ9ወር ቤቴ
ክፉሽን አልሳማ እማ እስከለተሞቴ
ክፊሽን አልስማ እማ °° እምዬ እናቴ

      ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅
  ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌    #Share
       https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
2.0K viewsAddisu, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 20:05:35

እማ ዋሽተሺኛል

የኑሮ ሁኔታ ካቅምሽ በላይ ሆኖ
ህመሙ ጭንቀቱ ሲጽናብሽ ገኖ
በተሰበረ ልብ ካይንሽ ዕንባ ሲፈስ
ማይጠገብ ፊትሽ ባዘን ሲደፈርስ
     
                ምን ሆነሽ ነው ብዬ ያኔ ስጠይቅሽ
                 ጽጕሬን እየዳበሽ እንዲ ነበር መልስሽ
                 ፊቴን ታጥቤ ነው ለምን አለቅሳለው
                 አንተ ካለህልኝ ሁል ጊዜ ስቃለው
 
    ብለሽ ዋሽተሺኛል እኔ እንዳልከፋ እንደዛ በለቅሶ አይንሽ እየጠፋ

ውስጥሽ የተጎዳ ክፉኛ እያመመሽ
ደናነኝ አታስብ እርሳው ትዪኛለሽ
ግን ልጅነት ሆኖ አምንሻለው ቶሎ
ከቅፍሽ ስገባ እጅሽ እንኳን ዝሎ

                 ደግሞም አይቻለው ከሆድሽ አጉድለሽ   
                ጥራጊ ስትበዪ  እኔን ጥግብ አርገሽ
                 ለምንስ ዋሸሺኝ ለምንስ ደበቅሺኝ
                 እንደዛ እየክፋሽ ደስተኛ ነኝ አልሺኝ

እርቦሽ ሳትበዬ አንጀትሽም ታጥፎ
እኔን አብልተሻል ከጥጋብም አልፍ
ከህመምሽ በላይ ሚያሳስብሽ ነገር
ስለኔ ደስታ ነው ሳልከፋ እንድኖር

                     ባይኖርሽ እንኩዋን ከሰው ተበድረሽ
                    አንሼ እንዳልታይ ሁሉን ታደርጊያለሽ
                       እስካለሽ እስካለሁ
                   እምዬ ሁል ጊዜ ደምቄ እታያለሁ
  
               አንቺ እኮነሽ ወዜ

ባንቺ ፈገግታ ውስጥ እኔ እንድበራ
ስንት ጊዜ ስቀሻል ሆነሽ በመከራ
ቢከፋሽ ለብቻሽ ደብቀሽ ሸሽገሽ
እማዋሽተሺኛል እያነባሽ ስቀሽ

     #እናቱን የሚወድ ይሄንን ግጥም ያንብላት


𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 በ ፍቅር

https://t.me/+j5zljw1X4VpkNTNk
1.9K viewsAddisu, 17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 20:03:37
@Addisu32
@Addisu32
1.8K viewsAddisu, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 20:03:24
@selafeker
@Addisu32
1.7K viewsAddisu, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ