Get Mystery Box with random crypto!

❤ የፍቅር ግጥም🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ selafeker — ❤ የፍቅር ግጥም🌹
የሰርጥ አድራሻ: @selafeker
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.61K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 💔 ❤
💊🔮 ከፍቶሀል?🙍‍♂
ከፍቶሻል? 🙍‍♀
🚬 አስደስታችኋል ብዬ ቃል አልገባም😥 ስሜታችሁን ግን እጋራለው💔 እናም ማንም ሰው እንዲያፅናናኝ አልፈልግም 🙅‍♂
ለአድናቆት @Addisu32
Join 👇requests የሚለውን ይጫኑ 👇

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-10 19:16:32
1.3K viewsAddisu, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 21:27:06    #መልስህን ንገረኝ 

ድሮስ የወደደውን መች ሰው ይፈልጋል
የማይፈልገውን ሄዶ ይለምናል።

    እኔም ከነዛ ውስጥ አንዷ ነሽ ብለዋል
    አንተ የኔ እንደሆንክ ማን በቅጡ ያቃል።

እኔ ስፈልግህ አንተስ እርቀሀል
እንዴት የኔ ላርግህ ሌላ ሰው ይዘሀል።

      የኔን ልብ ስሰጥህ መች አንተ ይገባሀል
       ለኔ ያለህን ስሜት ማወቅ ተስኖኛል።

እኔ አንተን ስፈልግ አንተ ስትል ሌላ
የኔ ልብ በስቃይ በሀዘን ተሞላ።

       አሁን የማሳይህ ላይገባህ ይችላል
       ስታቀው ሲገባህ እግርህ ይመልስሀል።

ተስፋ እንዳትቆርጥ ልቤ ይቀበልሀል
ጥላቻንም ገፍቶ ፍቅርን ያለብስሀል።

        በርግጥ አልዋሽህም ልቤ ይፈልግሀል
        በአፍ ባልነግርህም አይኔ አሳይቶሀል።

አልገባኝም ማለት አውቃለው እንደምችል
ግን ጥቅም የለውም አይገባኝም ብትል።

         አውቃለው እንደሌለህ የኔ እምትላት
         እኔ እኮ የለኝም የቅናት ስሜት።

ለኔ ያለህን ስሜት ንገረኝ እባክህ
ልሂድልህ በቃ ሙሉ ከሆነ ልብህ።

         ልቤ መውደድ ይበቃሀል
         ለእሱ እኔ አለሁ ለኔ ማን ያስብልብኛል።

የሰማዩ ጌታ የኔ ሁን ካላለው
ለኔ የፃፈውን እስኪ ልፈልገው።

         ካንተ ጋር መሆኑን ልቤ ይመኘዋል
          ያላንተ መኖሩን እንዴት ይችለዋል።

አንድ ቀን አስበህው ይገባህ ይሆናል
የሰው ልብ እንዲ ነው በተራው ይመጣል።

          ፈላጊ ነኝ እንጂ ማን ይፈልገኛል
          የሚፈልገኝስ መቼ ፍቅር ያውቃል
          እስኪጠግበኝ ብቻ ከጎኔ ይቆያል።

@Addisu32
@selafeker

https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
2.2K viewsAddisu, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 20:16:05 አንዱ በር ስዘጋ ሌላ በር ይከፈታል!

አንዱ የደስታ በር ስዘጋ ሌላው በር ይከፈታል ግን ሁላችንም በተዘጋው በር ላይ ረጅም ጊዜ ስናፈጥ አለመታደል ሆኖ ክፊቱን በር አናየውም ትለናለች ሄለን ከለር ይህንን ንግግር ማንም ቢናገረው አይገርመኝም ሄለን ከለር ግን ማየትም ሆነ መሰማት አትችልም

አስገራሚው ነገረ ግን ራሱን መናገረንና መጻፉን አስተምራ ትልቅ ደራሲና የመፍትሄ ተሟጋች ሆነች የዐይኑና የጆሮ በር ስዘጋ የአንደበቱን በር ተጠቅማ ታርክ ሠራች።አንተን ምን ደረሶብህ ነው ምን መኋት ወረዶብ ነው ጭንቅ ጥብብ ያለህ ወዳጄ በምድራዊ ችግር ተሰፋ መቁረጥ የለብህም ምክንያቱም አንዱ በር ስዘጋ ሌላ በር ይከፈታል።

ያማረ ምሽት ተመኘንላችሁ
@selafeker join
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ

አስተያየት ካላቹህ @Addisu32

https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
2.1K viewsAddisu, 17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 19:09:14 ከአንተ የሚጠበቀው!

በተግባር የምትገልጠው ማንነት ያስፈልግሀል፤ ከ 5 ዓመት ወይ ከ 10 ዓመት በኋላ መሆን የምትፈልገውን ሰው አሁን መሆን መጀመር አለብህ!

በቃ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ አድርግ! በየቀኑ በጥረትህ የሚገነባ እንጂ ከሰማይ የሚወርድ ማንነት የለም!

የተለየ ምሽት ተመኘንላችሁ
@selafeker join
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

የመወያያችን @Addisu32
2.1K viewsAddisu, 16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 19:01:45 ሀይል ውስጥህ ይፈሳል!

"በልቡ ቂም ይዞ ይቅርታ የማያደርግ ሰው ጠላቱን ለመጉዳት ብሎ መርዝ የሚጠጣ ነው" ይለናል ታላቁ የሀይማኖት መስራች ቡድሀ። የያዘህን የንዴት የቁጭት ስሜት ከውስጥ አውጣና ፈተህ ልቀቀው! ካንተ ይራቅ! 

ሰው የሌለውን አይሰጥም፤ አንተ ውስጥ ያለው ይቅርታ ነው እንጂ ቂም አይደለም፤ ሰዎች ብዙ ነገር አርገውህ ይሆናል፤ የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው! ራስህንም መውቀስ አቁም! ለራስህ ይቅርታ ስታደርግ የሆነ ሀይል ውስጥህ ይፈሳል፤ ወዳጄ ከዛ ምንም ነገር አያቆምህም!

የይቅርታ ምሽት ተመኘንላችሁ
@ https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0 join
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

የመወያያችን @Addisu32
2.1K viewsAddisu, 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 18:45:52 ጨረቃ ስትወጣ ከጎኔ ቁጭ ብለሽ
በዓይኔ አይሻለው……
ከዋክብት ሲጓዙ ከነሱ መካከል
አንቺን ፈልጋለው……
ከፀሃይ ጋር ብትወጪ ብዬ
ሁል ጊዜ ጠዋት እጠብቅሻለው
አንዳንዴም በህልሜ አቅፌሽ አድራለው።
ዝም ብለሽ በሀሳቤ ሁሌ ትመጪያለሽ
ምክንያቱን ባላቅም ትናፍቂኛለሽ
ያነጫንጨኛል ላገኝሽ እሻለው…
በሰበብ አስባቡ ስላንቺ አወራለው
የፅድቄ ሽልማት የኔ ገነት ውዴ
ኧረ ጉዴ ፈላ…ፍቅር ያዘኝ እንዴ

#Like ና #አደራ_ሼር_አድርጉ

@Addisu32
@selafeker
━━━━━━✦ ✦━━━━━━

https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
2.2K viewsAddisu, 15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 21:28:14 ​​እርስዎስ ቢሆኑ ምን ያረጋሉ?


የእህቴን ባል አፈቀርኩት

አስቸገርኩት ወይስ አስቸገረኝ?
ለትምህርት ከድሬ ሸገር ከገባሁ አሁን ስድስተኛ አመቴን አስቆጥሪያለሁ። የመጣሁበትን አላማ አሳክቼ በቢዝነስ
ዲግሪ ተመርቄ የባንክ ሰራተኛ ሆኛለሁ። ዲግሪዬን እንድመረቅና ስራ እንድቀጠር የእህቴ ባለቤት እጅግ በጣም ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎልኛል። ከእህቴ ባል ጋር በጣም እየተላመድን ስንመጣ ባላሰብነው ሁኔታ ነገር ተገለባበጠ። ቢያንስ ለ5 ወራት ያክል እኔና እሱ ብቻችንን አንድ ቤት አድረናል። መላመድ ችግር ፈጠረብን። እጅግ መልካም ሰው ነው። ሳላስበው አፈቀርሁት። እሱም እጅግ በጣም ተቸግሯል። አፈቀረኝ። እኔ ግን ፍቅሬን አፍኜ እንደማላፈቅረው በአንደበቴ እነግረዋለሁ። እጅግ በጣም ብዙ ቀን ከእህቴ ቤት ለመውጣት አስቤ አውቃለሁ። ነገር ግን እንዴት ከሱ እንደምለይ ይከብደኛል። የሚሞትብኝ እስኪመስለኝ ድረስ ያሳዝነኛል። እንደማላፈቅረው በአንደበቴ የምነግረው ችግር ውስጥ እንዳይገባ ፈልጌ ነው። እንደሚያፈቅረኝ እንጅ እንደማፈቅረው እርሱ አያውቅም። የሱን ያህል የሚወደኝና የሚያፈቅረኝ እንደሌለ በጣም እርግጠኛ ነኝ። ሞት ቢመጣ እንኳን እንደሚሞትልኝ በተግባር አሳይቶኛል። አብረን ባደርንባቸው ቀናት ውስጥ ስሜት ውስጥ ገብተን ተሳስመናል። የወሲብ ፍላጎታችን ከፍተኛ ቢሆንም ጫፍ ደርሰን ወሲብ አርገን አናውቅም። sex እንድናደርግ ብዙ ቀን ፈልጌ አውቃለሁ። እርሱ ግን ከመሳሳም እንዳናልፍ ስሜቴን በመሳም እንዲያልፍ ያደርጋል። ከስሜት ስነቃ እህቴ እንጅ እሱ አያሳዝነኝም። ብዙ ቀን አስቀይሜው እራሱ ያባብለኛል። በአፌ ግን ደጋግሜ እንደማላፈቅረው እነግረዋለሁ። እንዲህ ስለው እጅግ በጣም ያዝናል። ያሳዘንኩት ቀን ሙሉውን ቀን ምን ሆኖብኝ ይሆን እያልሁ ስጨነቅ ሳስብና ሳለቅስ እውላለሁ።
አፈቅርሀለሁ እንዳልለው ከበደኝ እንዳልተወው አፈቅረዋለሁ።

ግን አስቸገርሁት ወይስ አስቸገረኝ?
አሰቃየኝ ወይስ አሰቃየሁት?



ታሪክ አለኝ ለሰዉ ሀሳቤን ባካፍለዉ ይቀለኛል የምትሉ,የጨነቀ የፍቅር ታሪክ ያላችሁ እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ ላይ እንዲቀርብ ሰወች ሀሳብ እንዲካፍሎችሁ
@Addisu32 ላይ አድርሱን




       ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
          •═••• •••
     @selafeker   
,,,,,, @Addisu32
━━━━━━━✦ ✿✦━━━━━━━

     https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
513 viewsAddisu, edited  18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 21:27:50
@Addisu32

@selafeker
490 viewsAddisu, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 20:21:06
Video ቪዲዮን እዩት እና አስተያየታቹሁን ለግሱኝ ።

@Addisu32
@selafeker

https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
696 viewsAddisu, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 20:14:32 #አታፍቅሪኝ


ተኝቸም ቁጭ ብየም በቁሜም ሳስብሽ፤
ለእኔ ሚሆን ቦታ ባይኖርም በልብሽ ፤
ወረተኛ ሁነሽ ለፍቅር ባትሞች፤
ባክሽ እኔ ላፍቅር አታፍቅሪኝ አንች፡፡
መለየት አቅቶኝ ቀን መሽቶ መንጋቱን፤
አንገቴን ደፍቸ ስገፋ ጊዜያቱን፤
በሳቅ በጨዋታ ሰፈሩ ሲቦርቅ፤
ፍቅርሽ ፍቅሬን ሰብሮት ከህል ውሃሽ ስርቅ፤
ሊያጽናናኝ የሚያስብ ባገር ቢሞላም ሰው፤
የፍቅርሽን ስቃይ ብቻየን ልቅመሰው፡፡
የሚያስተሳስረን ያ ቀን እስኪመጣ፤
አንች ሰላም ሁኝ እኔ ሰላም ልጣ፡፡
እስከማገኝ ድረስ ከእንግዲህ አቻየን፡
ባክሽ አታፍቅሪኝ ላፍቅርሽ ብቻየን፡፡


       ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                  •═••• •••═•
  
     @selafeker    ,,,,,, @Addisu32
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━

https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0
     
619 viewsAddisu, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ