2022-12-26 15:50:30
እንዲቀልሽ 20
**የኖርሻቸውን አመታት ሰርዞ ህይወትን ሀ ብሎ የሚያስጀምርሽን ሰው ስታልሚ ውለሽ ስለምታድሪው አንቺ ብናወራስ
**አንዲት እርምጃን ልብሽ አልደፍር ብሎ ተራምዶም ይሁን ሮጦ ከጎንሽ እንዲገኝ የምትከጅይው ሰውዬሽ ነገርስ እንዴት እየሄደልሽ ነው??
**ባሳለፍሽው ህይወት ምክንያት ልብሽን ዝግ አድርገሽ ለቤተሰቦችሽ እና በዙሪያሽ ለሚወተውቱሽ ሰዎች ብቻ ብለሽ ትዳርን ያለፍቅርም ቢሆን ለማግኘት የምትጋጋጪው ምስኪኗ እህቴስ እንደምን ከርመሻል??
**ባህልና እሴት ነው ወጉም አይፈቅድም ትዳር ከሱ ይምጣ ብለውሽ ሲያበቁ በገባሽ በወጣሽ ቁጥር ....."ኸረ አንቺ ልጅ አረጀሽ አግቢ እንጂ".... እያሉ መግቢያ መውጫ ላሳጡሽ.... አግባኝ ለማለት አቅሙን ያጣሽ.. መናቅ ይደርስብኛል የሚል ፍርሀት የናጠሽ እህቴ እንደምን ነሽ??
**ህይወት በሁሉም አቅጣጫ የጠመመችብሽ የተመኘሽው የከጀልሽው ቀርቶ ያሰብሽው የማይሳካልሽ የሚመስልሽ ......እድለቢስነት አብሮሽ የተፈጠረ ይመስል ፈተናዎች የተደራረቡብሽ .......ችግርሽን የሚረዳሽ ቀርቶ "እህ" ብሎ የሚሰማሽ ያጣሽ .....ኑሮሽ ከመውጣት መግባት ያልዘለለ ኢምንት የማይጨምር ትላንትም ዛሬም ያው የሆነብሽ እንስት ሆይ ዛሬን እንዴት አለሽ???
እኔ ምልሽ!!!
"""ነገሮችን በራስሽ ለማስተካከል ደፋ ቀና እያልሽ ስትደክሚ ፈጣሪሽን ስለምን ዘነጋሽው አለሜ??
ፈጥሮ የረሳሽ የሚመስልሽ ለምን ነው? ጥንካሬሽን የሚፈትነው በነገሮች አለመሳካት ትእግስትሽን የሚፈታተንሽ ቢመርጥሽ እንጂ ለምን ይመስልሻል???
እጅሽን አንሺ ፣ ግንባርሽን ድፊ ፣ እውነተኛ እና ትክክለኛ የልብ መቅረብን ቅረቢ፣ ተናነሺና ከፍታን ጠይቂ እሱ ዘንድ የተዘረጋ እጅ በባዶ አይመለስም እመኚኝ!!!
#ስላንተም_እንቀጥላለን!!!
ማኪ
✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
49 viewsGlamor, 12:50