Get Mystery Box with random crypto!

ሽፈራው የሶማው

የቴሌግራም ቻናል አርማ rasmeried — ሽፈራው የሶማው
የቴሌግራም ቻናል አርማ rasmeried — ሽፈራው የሶማው
የሰርጥ አድራሻ: @rasmeried
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.22K
የሰርጥ መግለጫ

የአማራ ሕዝብ የሕልውና የፍትህ እና ርትዕ ትግል ትክክልና ድል መጎናፀፍ ያለበት ነው።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-30 10:34:13 ጃርት ወይስ ቀበሮ?
------------//---------

የፓለቲካ ጥያቄዎች እና መብቶችን በሰላማዊ መንገድና ትግል ማሸነፍ የሚገባና ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ ስለሆነ የሚመረጥ ነው!!!

የዜግነት መብቶች (Civic Rights) የሰላም በርን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ የጦርነት መንገድን ብቸኛ አማራጭ እስካላደረገ ድረስና በአንድ ሀገር ላይ እንደ ፍርድ ቤት መከላከያ እና ሌሎች የፀጥታ ተቋማት ገለልተኛ ነፃና ከአገዛዝ ነፃ ሆነው እስካሉ ድረስ በሰላማዊ ትግል ምላሽ ለማግኘት መታገል ላቂ መፍትሄ የማምጣት እድል ስላለው የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል::

ነገር ግን ሰብዐዊ መብቶች (Human Rights) ከህልውና ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚገናኝና የሚያስከትለው ጉዳት የማይቀለበስ የማይካስ ሊሆን ስለሚችል የሚመረጠው የትግል ስልት እናደ አደጋው መጠን እና አይነት የሚበየን ነው የሚሆነው::

ለምሳሌ:- በነፃነት እና በንብረት ላይ የሚቃጣን ጥቃት ጊዜ ሰጥቶ በሰላማዊ መንገድ መታገል ይቻላል::

በህይወት ላይ የሚቃጣን ማንኛውም ጥቃት ውጤቱ የማይቀለበስ ጥፋትን ያም ህይወትን እስከወዲያኛው ማጣት ስለሚሆን የሞተው ሞቶ በሰላማዊ ትግል እንፀናለን ማለት ከተፈጥሮም ከሰውም ህግ የተፋታ ወደ ድንቁርና በሚያመዝን የዋህነት ነው!!!

የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነውን እራስን የማዳንና ዘርን የማስቀጠል ተፈጥሯዊ ህግን የሚፃረር መሆኑን ማወቅ ተስኗቸው በሕዝባዊ እምቢተኝነት. በሰላማዊ ሰልፍ...በምርጫ ሰላማዊ ትግል ታገሉ ብለው ያልገባቸውን አምነው ያመኑት የሚሰብኩ "አዋቂም" ታዋቂም ማየት ሰዎች የሚሞቱባትና ሰቆቃ የበዛባት ሀገር ላይ ባይሆን ኖሮ አስቂኝ ትዕይንት በሆነልኝ ነበር!!!

ጃርት ወይስ ቀበሮ በሚለው ፅሁፏ ላይ አይዛያ በርሊን የተባለ የፓለቲካ ፈላስፏ "ጃርት አንድ እውነት ታውቃለች::

ያም ነጠላ እውቀት አለምን ሁሉ የምታይበት መነፅር ነው!!! ለዛም ነጠላ እውነት ሁሉን ነገር ከርክማ ታስገብርለታለች!!! በጥቅሉ ያ ነጠላ እውቀት አለም ቢጠፋ እንኳን ይኑር! ያብብ!! ይለምልም የምትል ጥልቀት የሌላትና የተለያየ ሁኔታ የተለያየ የመፍትሄ አማራጭ እንዳለው የማትገነዘብ እንደ ጭንጫ መሬት ጥልቀት የሌላት ናት ይላል አይዛያ በርሊን::

ቀበሮ ግን የአለምን ውስብስብነት በአግባቡ ተረድቶ ለተለያዩ ችግሮች የተለያየና ሁኔታውን የሚመጥን ምላሽ የሚሰጥ ነውና ከጭንጫዋ ጃርት የቀበሮ ብልሀት ይመረጣል ባይ ነው::

ጃርት ሰላም በራሱ መዳረሻ ሳይሆን ለህይወት ለንብረትና ለነፃነት ጠቃሚ ስለሆነ እንደሆነ የሚመረጠው መረዳት አትችልም!!! አንዴ "ሰላም" ካለች ህይወት እየጠፋም ቢሆን ሰላም የሚል መፈክር ይዛ ትቀጥላለች ወይም ትጠፋለች!!

ቀበሮ ግን ሰላም ለህይወት ለአካላዊ ደህንነትና ሌሎች የህልውና አደጋዎችን ለመቅረፍ እናም ለማስቀረት እንደሚጠቅም በአግባቡ ተረድቶ ሰላምን አጥብቆ ይወዳል::

በዛውም ልክ አሁናዊና ተጨባጭ አደጋ ሲመጣበት አልሞት ባይ ተጋዳይ በመሆን ታግሎ ሊሰርቅ ሊገድል ሊያጠፋ የመጣውን ማንኛውንም ኃይል ይታገላል ይፋለማል እንጂ እስቲ ገዳዮቼ ሆይ የመጣቹበትን ከማሳካታችሁ በፊት አንዴ ስለ ሰላም እና ለሰላም እንፀልይ አይልም!!!

እጅና እግሩንም አጣጥፎ እኔ በሰላማዊ ትግል ብቻ ነውና የማምነው አልሞት ባይ ተጋዳይ አልሆንም የሚል ሞኝ አይደለም!!! እንዲህ አይነቱ ሞኝነት ጃርትን እንጂ ቀበሮን አያጠቃም:: (ለነገሩስ የሊሂቃንን የአስተሳሰብ ዝንባሌ ለማሳየት ጃርት ወይስ ቀበሮ በሚል አገልግሎት ላይ ዋለ እንጂ በተፈጥሯዊ ማንነቷ ጃርትም የእሾህ ክምር ይዛ የምትዞረው ገዳዮቿን ልታስውብበት አይደለም!!! ለሰላማዊ ትግል አይደለም እያልኩህ ነው!!!እኛስ ዘንድሮስ ብሶብን ጃርትና ሸረሪት የሚያውቁት እራስን የመከላከል መብት የተፈጥሮ ህግ ለሊሂቃን ስይቀር ግድ ሆኗል!!!)

ለማንኛውም ምን አይነት የችግር አፈታ? መቼ? እንዴት? ወደሚለው ምልሰት ላድርግ::

ለዚህም ነው ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ፍቱ እያልኩ ስሰብክ የነበርኩት እኔ ጎዳና ከባዳ የሻቢያ ሰራዊት ጋር ተጣምሮ ሊጠብቃቸው የሚገባቸውን የትግራይ ልጃገረዶችን ሲያስደፍር እና አብሮ ሲደፍር የነበረውን ሰራዊት የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ "ሰላም" እያለ ሳይሆን ነፍጥ አንግቦ "የአሉላ አባ ነጋ ዘመቻ" ብሎ በመራራ ትግሉ ሲያስወጣ ለትግራይ እናቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በአደባባይ ያስተላለፍኩት::

ይዤው የምዞረው ሁለት መስፈሪያ የለኝምና ዛሬም አሁናዊና ተጨባጭ የህልውና አደጋ ውስጥ ላለው የአማራ ሕዝብ የዘምባባ ዝንጣፊ ይዘህ "ሰላም" እያልክ እየዘመርክ ውጣ ሳይሆን የምለው በመራራ ትግልህ ህልውናህን አስጠብቅ...! አስከብር...! ነው የምለው መርሄም አንድ መስፈሪያዬም አንድ ነውና!!!

ለማንኛውም ከአሁናዊ ጥቃት ለመጠበቅ ተፈጥሮም ህግም ተሞክሮም ምን ያዛል...ፋታ የሚሰጡ ሌሎች ችግሮችስ ምን አይነት የግጭት አፈታት አማራጮች ይኖሩታል ብሎ ማየት ያስፈልጋል:: ሰላማዊ ትግል የአለመግባባት የተቃርኖና የግጭት አፈታት አማራጭ እንጂ የሚሞትለት ኃይማኖት አይደለም::

አቋም እና ሀሳብም ለየቅል ናቸውና ከአቋም ክምር ትንሽ ሀሳብ ወደ መግባባት ባያደርስ እንኳን ቢያንስ ለመደማመጥ ይረዳል ባይ ነኝ!!!


በ Godana Yakob



ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
875 views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 10:33:07 በወያኔ እና በኦነግ ሸኔ የከሸፈ የአገር መከላከያ ሠራዊት በአማራ ወጣቶች ላይ አይሳካለትም።

የአማራ አርሶአደር እና የአማራ ሕዝብ ስለሕልውናህ የተነሱ ልጆችህን ጠብቅ!!
የአማራ ልጆች ስንቃቸው ምሽጋቸው ሕዝብ ነው !!


ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
607 views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 09:34:17 በአማራ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የሚከተሉትን የቴሌግራም ገፆች ይቀላቀሉ።

ገፆቹን  #share በማድረግ ያጋሩቸው !!

1) ANF
https://t.me/Anfyes

2) Amhara Espionage
https://t.me/Amespionage

3) ራስ ስዕለክርስቶስ
https://t.me/D_free1

4) ራስ መርዕድ
https://t.me/RasMeried

5) ኢትዮ 251 media
https://t.me/ethio251media

6)  Inform Amhara
https://t.me/informamhara

7) ቆቂት
https://t.me/kokit2121

8) የአማራ ድምፅ
https://t.me/VOAamhara

9) ሙሉጌታ አንበርብር
https://t.me/Mulugetaanberberr

10) ቃል-አለን
https://t.me/Qal_Alen

11) ሞረሽ አማራ
https://t.me/moresh143yo

12) Horn African news
https://t.me/Horn_African_News

13) Ethio daily monitor
https://t.me/ethiodailymonitor

14) king makers
https://t.me/Akingmakers

15) Amhara international
https://t.me/amharainternational

16) Inform Amhara
https://t.me/informamhara

17) Assaye Derbie
https://t.me/etegieassaye

18) Amhara Today
https://t.me/+sf6vdfXU5Tk1MzQ0

19) AgarsAmhara
https://t.me/AgarsAmhara


ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
667 views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 09:25:23
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አማራ ምንም አያመጣም፣ ወሬ እና ጉራ ብቻ ነው ሲል የነበረ መንጋ፤ ሰሞኑን ደግሞ ከውጭ ቢያድር እንኳን ቀበሮ የማትነካው የሰው ገልቱ ሁሉ  "ይገሉኛል" ሆኖል ዘፈኑ ሁሉ።

የዚህን ህዝብ ህመም እሱን ሆናችሁ ተረዱት፤ በደሉን ጩኸቱን ስሙት፤ ከቻላችሁ እንባውን አብሱለት። የአማራ ሕዝብ ሌላ አልጠየቀም፤ እንደ ሰው የመኖር መብቴ ይከበር ነው ያለው፤ ሌላው ቢቀር ሰውነቴ እውቅና ይሰጠው ነው ጥያቄው፡፡

በነገራችን ላይ ይህ ህዝብ ተቆጥቷል !!
ቁጣውን መረዳት ካልቻልህ ቢያንስ ዝም በማለት አግዝ።
ከዚህ በተረፈ በፓለቲካ correctness ስም በየሚዲያው እየወጣህ የህዝባችንን ቁስል በነገር በመሸቅሸቅ መልሰህ እያደማህ  ፥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ በመሆን እያገለገልህ ነው።

እንቅልፍ እምቢ ባለህ ቁጥር የአማራ ብሄርተኞች ይገሉኛል ይሉት እለቅሶ ሰሚ የለውም። የአማራ ብሔርተኝነት ገዳይ ስኳድ አላቋቋመም፤ የለውምም። የአማራ ብሔርተኝነት ለምን እንደተፈጠረ የሚያውቅ ያውቀዋል

በመጨረሻ ቀኙን ስንመታችሁ ግራውን ፊታችሁን አምጡ ከሆነ ጥያቄችሁ እሱን የማድረግ ችሎታ ያለው የናዝሬቱ እየሱስ ብቻ ነው ።


በኤልሻዳይ የግዮን ልጅ

ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
1.4K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 09:13:53
የአማራ ትግል እጅግ ፍትሐዊ ትግል ነው!!



ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
919 viewsedited  06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 07:06:23
ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ!

በእንግሊዝ ለንዶን የሚገኙ የአማራ ዲያስፖራዎች የፊታችን አርብ 21st April from 2:30-6:30Pm ቦታ at 17 Princes Gate London SW7 1PZ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የአማራ ስብስብ ድርጅቶች በአማራ  ግብረሃይል ዋና  አስተባባሪነት ተዘጋጅቷል። ተጋብዛችኋል!

ለበለጠ መረጃ :- 07417589269 / 07429 363249


ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
251 views04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 21:24:48 At least 8 journalists detained amid renewed unrest in Ethiopia


https://cpj.org/2023/04/at-least-8-journalists-detained-amid-renewed-unrest-in-ethiopia/?s=09
533 viewsedited  18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 21:22:27 "በየከተማው የሚተኮሰው ጥይት ወደ ከፋ የገዥዎች ሴራ ተቀይሯል።

1) ቤተ እሞነትና ቤት ግቢ ውስጥ ያሉ ሰዎች በተባራሪ ጥይት ተመትተዋል። ሆኖም ከአጥሩና ከሌላው አንፃር ሲታይ ህንፃዎች ላይ ሆነው በተጠና መልኩ የሚተኩሱ አካላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ነው። እነዚህ አካላት የፀጥታ ኃይሉን ስም ከማጥፋት አልፈው በህዝብም ለማስጠላት ያሰቡ እንደሆኑ ተገምቷል። ግጭት ለመበስቀስም እየተሰራ እንደሆነ ማሳያ ናቸው።

2) የፌደራል ፀጥታ አካላት ጭምር ባሉባቸው ከተሞች ጥይት የሚተኩሱት አካላት አይጠየቁም። ጥይት ተኩሱ እንዲቀጥል የተፈለገ ብቻ ሳይሆን አካባቢ ለማተራመስ፣ ከዛም በሰበብ ፋኖ እና የልዩ ኃይል አባላትን ለማጥቃት የታሰበበት ሴራ ነው።

3) የፌደራል ፀጥታ አካላት የሚኖሩባቸው ካምፖችን ጨምሮ ጥይት ተኩስ የሚጀመርባቸው የመንግስት አካላት የሚቆጣጠሯቸው ቦታዎች ናቸው። እነዚህ አካባቢዎች ላይ ጥይት ከተተኮሰ በኋላ በተናበበ መልኩ በሌሎቹም ይተኮሳል።

በአጠቃላይ በከተሞቹ ጥይት መተኮሱን ገዥዎች የሚፈልጉት፣ ለዚህ አላማ ጥይት የሚተኩስ ተባባሪዎችን ያሰማሩበት ነው። ይህን በመገንዘብ በየከተማው ጥይት የሚተኩሱ አካላት የገዥዎቹ አላማ ማስፈፀሚያ መሆናቸው መታወቅ አለበት። እነሱን ተከትሎ ጥይት የሚተኩስ ካለ ገዥዎቹ በአካባቢው ሊፈጥሩት ላሰቡት ሴራ መጠቀሚያ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።

ስለሆነም ሁሉም በሚችለው መልኩ በየከተማው የሚተኮሰው ጥይት ገዥዎቹ ህዝባችን ለማጥቃት እያለማመዱት ያለው የከፋ ሴራ ምልክት መሆኑን እንዲያውቅ በሚችለው መንገድ ሁሉ ማድረስ አለበት።"
(በጌታቸው ሽፈራው)


ድል ለአማራ !

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
552 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 21:14:56
ጋዜጠኞች ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶባቸው እንዲታሰሩ መደረጉ፤ “በምንም መለኪያ ተቀባይነት የሌለው ነው” ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ተቸ

ከስራቸው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በዋሉ ጋዜጠኞች ላይ የቀረቡ ክሶችን፤ የፍትህ ስርዓቱ “በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ብቻ” በመመራት እንዲመለከታቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ጠየቀ። በቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች “እንደማንኛውም ተከሳሽ” ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶባቸው እንዲታሰሩ መደረጉንም፤ ምክር ቤቱ “በምንም መለኪያ ተቀባይነት የሌለው” ሲል ተችቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ይህን ያለው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋዜጠኞች ላይ የተፈጸሙ እስሮችን እና የፍርድ ቤት ሂደቶቻቸውን አስመልክቶ ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 9፤ 2015 ባወጣው መግለጫ ነው። ምክር ቤቱ በዚሁ መግለጫው፤ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞች በተደጋጋሚ “ከሕግ አግባብ ውጪ መያዝ እና መታፈናቸውን” እንዲሁም በሚሰሩባቸው ተቋማት ላይ “ያለፍርድ ቤት ማዘዣ ወረቀት ብርበራ” መፈጸሙን እንደተገነዘበ አስታውቋል።

በሚዲያ አማካኝነት ተፈጽሟል በተባለ ወንጀል የተጠረጠሩት እነዚህ ጋዜጠኞች፤ በፖሊስ በቁጥጥር ስር እየዋሉ እና ወደ ፍርድ ቤት እየቀረቡ ያሉት በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ መሰረት አለመሆኑንም ምክር ቤቱ ገልጿል። ይህ ድርጊትም “ባለሙያዎች ስራቸውን በነጻነት እንዳይሰሩ፤ እንዲሸማቀቁ እና የፕሬስ ምህዳሩ የበለጠ እንዲጠብ” እያደረገ መሆኑን በዛሬው መግለጫው መጥቀሱን ኢትዮጵያን ኢንሳይደር ዘግቧል።


ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
324 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 21:14:28 የአማራ ትግል ፤

የአማራ ትግል ረጂም እና ፈታኝ ነው።
ምክንያቱም፤
ጠላቶቻችን ብዙ እና የተለያየ ደረጃ እና መገለጫ ያላቸው ነው። ወዳጆቻችን ደግሞ ጥቂቶች እና በአብዛኛው ድብቅ ናቸው። ለብዙ አስርት አመታት የተዘራው ጸረ አማራ ትርክት እና ርዕዮት እንዲሁም ስርአታዊ እና መንግስታዊ ጠላትነት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ከዚህም በተጨማሪ የውስጥ ማህበራዊ እውነታዎች እና ነባር የፖለቲካ ልዩነቶች ላይ የጠላቶች ተንኮል ተጨምረውበት የተፈጠሩ የፖለቲካ ስንጥቃት ምልክቶች አሉ። ይህ ሁሉ ውስብስብ ሁነት ባለበት የተጋረጠው የህልውና አደጋ ካሉት የውስጥም ሆነ ችግሮች በላይ ህዝቡን የግድ እንዲነቃ አድርጎታል። ይህ አደጋ ያነቃው እና ያነቃቃው ማንነት ተኮር አደረጃጀት የበለጠ እንዲጠናከር ከውጭ ከመጣው ግፊት በተጨማሪ በራስ ተነሳሽነት ፣ በተጠና መልኩ የሚሰሩ ተግባራትን ይፈልጋል። ሆኖም ተግባራቱን ለመፈጸም ሰፊ ፈተና መግጠሙ አይቀርም።
እናም የምናደርገው ትግል የማገጥመውን ተደጋጋሚ ጎበስ ቀናዎች፣ የሚጨናገፉ ጅምሮች እና ፈተናዎች ለመሻገር ወሳኝ ስንቅ ይፈልጋል። ይህም ስንቅ አንድም ቀዳሚው የህዝቡ ጥያቄ ሲሆን ሌላው ደግሞ የትግሉ መዳረሻ ግብ ነው። የወቅቱ የአማራ ህዝብ ተጋድሎ መሠረታዊ ጥያቄ የህልውና አደጋው እና የፍትህ ጥያቄ ነው። በነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ውስጥ የማንነት፣ የስርአት፣ የመብት መከበር እና ሌሎች ጥያቄዎች ይገኙበታል። የትግሉ መዳረሻ ግብ ደግሞ እነዚህን ጥያቄዎች ባገናዘበ መልኩ የአማራ ህዝብ ለተፈጸሙበት ጥፋቶች ፍትህን በማስገኝት፣ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ህልውናው ተረጋግጦ የሚኖርበት ሀገራዊ ስርአተ ማህበር ማንበር ነው።
ይህን ለማሳካት ደግሞ በልከኛ የራስ ፍላጎት ልባዌ ላይ የተመሠረተ የአማራነት ብሄራዊ ንቃት እንዲጎለብት በማስቻል በሁሉም መስክ፣ እንደ ሁኔታዎች አመቺነት፣ አስፈላጊ የሆኑ አደረጃጀቶችን መፍጠር እና ማጠናከርን ይጠይቃል።
አሁን ያሉ እንቅስቃሴዎች ይህን ባገናዘበ መልኩ የሚደረጉ ሆነው፣ በዚህ መልኩ እየተሰሩ ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

ድል ለአማራ !

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
281 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ