Get Mystery Box with random crypto!

ጃርት ወይስ ቀበሮ? ------------//--------- የፓለቲካ ጥያቄዎች | ሽፈራው የሶማው

ጃርት ወይስ ቀበሮ?
------------//---------

የፓለቲካ ጥያቄዎች እና መብቶችን በሰላማዊ መንገድና ትግል ማሸነፍ የሚገባና ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ ስለሆነ የሚመረጥ ነው!!!

የዜግነት መብቶች (Civic Rights) የሰላም በርን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ የጦርነት መንገድን ብቸኛ አማራጭ እስካላደረገ ድረስና በአንድ ሀገር ላይ እንደ ፍርድ ቤት መከላከያ እና ሌሎች የፀጥታ ተቋማት ገለልተኛ ነፃና ከአገዛዝ ነፃ ሆነው እስካሉ ድረስ በሰላማዊ ትግል ምላሽ ለማግኘት መታገል ላቂ መፍትሄ የማምጣት እድል ስላለው የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል::

ነገር ግን ሰብዐዊ መብቶች (Human Rights) ከህልውና ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚገናኝና የሚያስከትለው ጉዳት የማይቀለበስ የማይካስ ሊሆን ስለሚችል የሚመረጠው የትግል ስልት እናደ አደጋው መጠን እና አይነት የሚበየን ነው የሚሆነው::

ለምሳሌ:- በነፃነት እና በንብረት ላይ የሚቃጣን ጥቃት ጊዜ ሰጥቶ በሰላማዊ መንገድ መታገል ይቻላል::

በህይወት ላይ የሚቃጣን ማንኛውም ጥቃት ውጤቱ የማይቀለበስ ጥፋትን ያም ህይወትን እስከወዲያኛው ማጣት ስለሚሆን የሞተው ሞቶ በሰላማዊ ትግል እንፀናለን ማለት ከተፈጥሮም ከሰውም ህግ የተፋታ ወደ ድንቁርና በሚያመዝን የዋህነት ነው!!!

የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነውን እራስን የማዳንና ዘርን የማስቀጠል ተፈጥሯዊ ህግን የሚፃረር መሆኑን ማወቅ ተስኗቸው በሕዝባዊ እምቢተኝነት. በሰላማዊ ሰልፍ...በምርጫ ሰላማዊ ትግል ታገሉ ብለው ያልገባቸውን አምነው ያመኑት የሚሰብኩ "አዋቂም" ታዋቂም ማየት ሰዎች የሚሞቱባትና ሰቆቃ የበዛባት ሀገር ላይ ባይሆን ኖሮ አስቂኝ ትዕይንት በሆነልኝ ነበር!!!

ጃርት ወይስ ቀበሮ በሚለው ፅሁፏ ላይ አይዛያ በርሊን የተባለ የፓለቲካ ፈላስፏ "ጃርት አንድ እውነት ታውቃለች::

ያም ነጠላ እውቀት አለምን ሁሉ የምታይበት መነፅር ነው!!! ለዛም ነጠላ እውነት ሁሉን ነገር ከርክማ ታስገብርለታለች!!! በጥቅሉ ያ ነጠላ እውቀት አለም ቢጠፋ እንኳን ይኑር! ያብብ!! ይለምልም የምትል ጥልቀት የሌላትና የተለያየ ሁኔታ የተለያየ የመፍትሄ አማራጭ እንዳለው የማትገነዘብ እንደ ጭንጫ መሬት ጥልቀት የሌላት ናት ይላል አይዛያ በርሊን::

ቀበሮ ግን የአለምን ውስብስብነት በአግባቡ ተረድቶ ለተለያዩ ችግሮች የተለያየና ሁኔታውን የሚመጥን ምላሽ የሚሰጥ ነውና ከጭንጫዋ ጃርት የቀበሮ ብልሀት ይመረጣል ባይ ነው::

ጃርት ሰላም በራሱ መዳረሻ ሳይሆን ለህይወት ለንብረትና ለነፃነት ጠቃሚ ስለሆነ እንደሆነ የሚመረጠው መረዳት አትችልም!!! አንዴ "ሰላም" ካለች ህይወት እየጠፋም ቢሆን ሰላም የሚል መፈክር ይዛ ትቀጥላለች ወይም ትጠፋለች!!

ቀበሮ ግን ሰላም ለህይወት ለአካላዊ ደህንነትና ሌሎች የህልውና አደጋዎችን ለመቅረፍ እናም ለማስቀረት እንደሚጠቅም በአግባቡ ተረድቶ ሰላምን አጥብቆ ይወዳል::

በዛውም ልክ አሁናዊና ተጨባጭ አደጋ ሲመጣበት አልሞት ባይ ተጋዳይ በመሆን ታግሎ ሊሰርቅ ሊገድል ሊያጠፋ የመጣውን ማንኛውንም ኃይል ይታገላል ይፋለማል እንጂ እስቲ ገዳዮቼ ሆይ የመጣቹበትን ከማሳካታችሁ በፊት አንዴ ስለ ሰላም እና ለሰላም እንፀልይ አይልም!!!

እጅና እግሩንም አጣጥፎ እኔ በሰላማዊ ትግል ብቻ ነውና የማምነው አልሞት ባይ ተጋዳይ አልሆንም የሚል ሞኝ አይደለም!!! እንዲህ አይነቱ ሞኝነት ጃርትን እንጂ ቀበሮን አያጠቃም:: (ለነገሩስ የሊሂቃንን የአስተሳሰብ ዝንባሌ ለማሳየት ጃርት ወይስ ቀበሮ በሚል አገልግሎት ላይ ዋለ እንጂ በተፈጥሯዊ ማንነቷ ጃርትም የእሾህ ክምር ይዛ የምትዞረው ገዳዮቿን ልታስውብበት አይደለም!!! ለሰላማዊ ትግል አይደለም እያልኩህ ነው!!!እኛስ ዘንድሮስ ብሶብን ጃርትና ሸረሪት የሚያውቁት እራስን የመከላከል መብት የተፈጥሮ ህግ ለሊሂቃን ስይቀር ግድ ሆኗል!!!)

ለማንኛውም ምን አይነት የችግር አፈታ? መቼ? እንዴት? ወደሚለው ምልሰት ላድርግ::

ለዚህም ነው ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ፍቱ እያልኩ ስሰብክ የነበርኩት እኔ ጎዳና ከባዳ የሻቢያ ሰራዊት ጋር ተጣምሮ ሊጠብቃቸው የሚገባቸውን የትግራይ ልጃገረዶችን ሲያስደፍር እና አብሮ ሲደፍር የነበረውን ሰራዊት የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ "ሰላም" እያለ ሳይሆን ነፍጥ አንግቦ "የአሉላ አባ ነጋ ዘመቻ" ብሎ በመራራ ትግሉ ሲያስወጣ ለትግራይ እናቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በአደባባይ ያስተላለፍኩት::

ይዤው የምዞረው ሁለት መስፈሪያ የለኝምና ዛሬም አሁናዊና ተጨባጭ የህልውና አደጋ ውስጥ ላለው የአማራ ሕዝብ የዘምባባ ዝንጣፊ ይዘህ "ሰላም" እያልክ እየዘመርክ ውጣ ሳይሆን የምለው በመራራ ትግልህ ህልውናህን አስጠብቅ...! አስከብር...! ነው የምለው መርሄም አንድ መስፈሪያዬም አንድ ነውና!!!

ለማንኛውም ከአሁናዊ ጥቃት ለመጠበቅ ተፈጥሮም ህግም ተሞክሮም ምን ያዛል...ፋታ የሚሰጡ ሌሎች ችግሮችስ ምን አይነት የግጭት አፈታት አማራጮች ይኖሩታል ብሎ ማየት ያስፈልጋል:: ሰላማዊ ትግል የአለመግባባት የተቃርኖና የግጭት አፈታት አማራጭ እንጂ የሚሞትለት ኃይማኖት አይደለም::

አቋም እና ሀሳብም ለየቅል ናቸውና ከአቋም ክምር ትንሽ ሀሳብ ወደ መግባባት ባያደርስ እንኳን ቢያንስ ለመደማመጥ ይረዳል ባይ ነኝ!!!


በ Godana Yakob



ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide