Get Mystery Box with random crypto!

ሽፈራው የሶማው

የቴሌግራም ቻናል አርማ rasmeried — ሽፈራው የሶማው
የቴሌግራም ቻናል አርማ rasmeried — ሽፈራው የሶማው
የሰርጥ አድራሻ: @rasmeried
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.22K
የሰርጥ መግለጫ

የአማራ ሕዝብ የሕልውና የፍትህ እና ርትዕ ትግል ትክክልና ድል መጎናፀፍ ያለበት ነው።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-17 13:11:09 ይህ "የአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ" የቴሌግራም ገጽ ነው። የአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴዎች የሚያወጣቸውን መረጃዎች በዚህ ያገኛሉ።
https://t.me/AmharaPeoplesCommitie
1.5K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 12:16:12 2. አማራው በወልቃይትና ራያ በከፈለው መስዋዕትነት ያስመለሰው ማንነትና ያስመለሳቸው አፅመ ርስቶቹ ህጋዊ እውቅና በአስቸኳይ ተሰጥቷቸው በአማራ ክልል ስር እንዲተዳደሩ እና የሁለት አመት ውዝፍ በጀት እንዲያገኙ እንዲደረግ፣

3. ወደ ክልሉ የገባው የመከላከያና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በአስቸኳይ እንዲወጣ፣
4. በህግ ማስከበር ሰበብ በአማራ ክልል የታሰሩ ፋኖዎች ከነ መሪያቸው አርበኛ ዘመነ ካሴ እንዲሁም ልዩ ኃይሎች በሙሉ እንዲፈቱ፣

5. በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በአማራው ላይ ያነጣጠረ የቤት ማፍረስ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የፈረሰባቸውም ካሳ አግኝተው በቦታቸው ላይ እንዲሰሩ እንዲፈቀድ፣

6. በአዲስ አበባ በሺወች የሚቆጠሩ ታፍሰው የታሰሩ አማራወች እንዲሁም ምሁራን ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ
አውግቸው፣ መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኞች አባይ ዘውዱ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው፣ ቴዎድሮስ አስፋው፣ ፓለቲከኞች፣ አንቂወች እንዲሁም ባለሃብቶች በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንዲሁም የፍትህ ታጋዩ አቶ ታዲዮስ ታንቱ እንዲፈቱ፣

7. በወለጋ አማራወች ላይ እየተካሄደ ያለው መንግሥት መር የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በአስቸኳይ እንዲቆምና ወራሪው የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም ከቦታው እንዲወጣ፣

8. እድሜውን በሙሉ ለአገሩ ሲታገል የኖረው ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ውጭ ወጥቶ ህክምና እንዳያገኝ መከልከሉ ፍፁም ነውር እና ሰባዓዊነት የጎደለው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲፈቀድለት እንጠይቃለን።


ለመከላከያ ሰራዊት፤

መከላከያ ሰራዊት ዋናኛ አላማህ ኢትዮጵያን ከጠላት ለመጠበቅ ስለሆነ ከዚህ በወጣ መልኩ በህዝብ ላይ ወረራ ፈፅም የሚል ትእዛዝ ውድቅ ማድረግ ይኖብሃል። ደግሞስ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ በችግርህ ወቅት የደረሱልህ በአንድነት በጦር ሜዳወች ተዋድቃችሁ ለድል አልበቃችሁምን? ስለዚህ መከላከያ ከህዝብ ጎን እንድትቆም እንጠይቃለን።

ለፓለቲካ ፓርቲዎች፤

ለፍትህ ዕኩልነትና ዲሞክራሲ የምትታገሉ የፓለቲካ ፓርቲወች በሙሉ ይህ የኦነግ መንግሥት ኢትዮጵያን ለከፍተኛ የህልውና አደጋ ላይ ስለጣላት በጋራ ሆናችሁ እንድታወግዙትና ከያዘው የእብደት ጉዞ እንዲገታ ጫና እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

ለሌሎች ክልሎች መንግሥታትና ህዝብ፤

የኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠልና ለህዝብ ሰላም የምትጨነቁ የክልል መንግሥታትና ህዝብ መንግሥት እየሄደበት ያለውን የእብሪትና ጉዞ በመቃወም ከተገፋው የአማራ ህዝብ ጋር በመቆም የትግል አጋሩ እንድትሆኑ እንጠይቃለን። በትብብር ይህ እብሪተኛ መንግሥትና ስርዓቱ ካልተለወጡ አገር እየፈረሰ መሆኑ በግልፅ ሊታወቅ ይገባል።

ለአዲስ አበባ ህዝብ፤

የአዲስ አበባ ህዝብ በዚህ የኦነግ መንግሥት እንደደረሰብህ መከራና ግፍ እንዲሁም ውርደት መቸም ደርሶብህ አያውቅም። ነገር ግን ግፉን በሚመጥን መልኩ እየታገልኸው ባለመሆኑ ገና ከዚህ ለባሰ ስቃይ ስለሚዳርግህ በአስቸኳይ በአማራ ክልልና በጉራጌ ዞን የተጀመረውን ህዝባዊ ትግል እንድትቀላቀል ጥሪ እናቀርባለን።

ለኦሮሞ ህዝብ፤

ህወሓት ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት እየፈፀመ ለነበረው ሰቆቃና ግፍ የትግራይ ህዝብ ተቃውሞ ባለማሰማቱ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዴት የትግራይ ህዝብ እንደተቀያየመ የሚታወስ ጉዳይ ነው። አሁንም የኦሮሞ ብልፅግና ከኦነግ ጋር በመሆን የኦሮሞ መንግሥት ነኝ እያለ በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና ሰቆቃ እያየህ ነው። ስለዚህ ይህ በስምህ የሚፈፀመውን ግፍ ሳይውል ሳያድር እንድትቃወም ጥሪ እናደርጋለን።

ለአማራው ህዝብ፤

ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በተለያዩ የአማራ ጠል መንግሥታት እየደረሰብህ ያለው ሰቆቃ ተነግሮ እንደማያልቅ ለቀባሪው እንደ ማርዳት ነው። ህወሓትና ኦነግ በትብብር ያደረሱብህ መከራ ተዘርዝሮ አያልቅም። በተለይ ግን በዚህ አምስት አመት ውስጥ በአብይ አህመድ የሚመራው የኦነግ መንግሥት እያደረሰብህ ያለው ግፍና ሰቆቃ ግን ፍፁም የተለየ ነው።
የወለጋውና መተከል የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፣ የአጣየ ተደጋጋሚ ውድመት፣ የደራ ሰቆቃ፣፣በአዲስ አብባ ዙሪያ ጅምላ ቤት ፈረሳና መፈናቀል፣ በእምነትህ የደረሰብህ ግፍ፣ ወደ መሰረትሃት ከተማ አዲስ አበባ አትገባም መባል፣ አዲስ አበባ ውስጥ ስራ እንዳትሰራ መከልከል፣ በህወሓት በሴራ እንድትወረርና እንድትወድም መደረግ፣ በድል ጦርነቱን እንዳትደመድም በማድረግ ወደ ድብቅ ስምምነት መድረስ፣ ይህን ተከትሎ በታላቅ መስዋእትነት ያስመለስሃቸውን ወልቃይትንና ራያን ዳግም ለህወሓት ለመስጠት መወሰን፣ እረ ስንቱ ይዘረዘራል አሁን ደግሞ ክልል ብለው በወሰኑልህ ሰፈር የጦር ኃይል በማሰማራት እየወጉህ ይገኛሉ።

ለዚህ ወረራ እየሰጠህ ያለኸው ምላሽ የሚያኮራ ነው። በዚሁ አጠናክረህ እንደምትቀጥል እናምናለን። ያለ ስርዓት ለውጥ ከህገ መንግሥት ለውጥ ጀምሮ ሌሎች ያሉህ መሰረታዊ ጥያቄዎችህ መልስ ሊያገኙ ስለማይችሉ ለስርዓት ለውጥ፣ ፍትህና እኩልነት ተግተህ እንድትታገል ጥሪ እያደረግን እኛም ከጎንህ መሆናችንን እናሳውቃለን።
አብዛኛው ኢትዮጵያዊም አገርን ከመፍረስ ለማዳን ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ለምታደርገው ትግል ከጎንህ እንድሚቆም እናምናለን።

ፍትህ ለግፉዓን!

የአማራው የህልውና ትግል ኢትዮጵያን ከመፍረስ ይታደጋል!
ዓለም አቀፍ አማራ ህብረት
ዋሽንግተን፣ ዲሲ
743 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 12:16:12 በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ግፍ አስመልክቶ ከዓለም አቀፍ አማራ ህብረት የተሰጠ መግለጫ

ዓለም አቀፍ አማራ ህብረት በአብይ አህመድ፣ ሺመልስ አብዲሳና አዳነች አቤቤ የሚመራው የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ በአማራ ህዝብ ላይ ያወጀውን ፋሺስታዊ ወረራ፣ ግድያ፣ አፈና፣ መጠነ ሰፊ ቤቶች ማፍረስና እና ማፈናቀል እንዲሁም የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታትና ለማፍረስ ያሳለፈውን ዕብሪት የተጠናወተው አገር አፍራሺ የሆነ የሴራ እርምጃ አጥብቆ ያወግዛል።

የአማራ ህዝብ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከሚደርስበት የማያባራ ግፍ እንዲሁም ከጦርነት እንኳን ገና ሳያገግም በኦሮሞ ብልፅግና የሚዘወረው የብልፅግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአማራን ህዝብ ደህንነት እና ህልውና ሲያስጠብቅ የቆየውን ኃይል ለማፍረስ እና ትጥቅ ለማስፈታት መወሰኑ እና ይህንንም ለማስፈጸም በግልጽ ጦርነት ከህዝቡ ጋር መግባቱ ከአንድ መንግሥት ነኝ ከሚል አካል የሚጠበቅ አይደለም።

የአማራ ልዩ ኃይል የተቋቋመው በክልሉ ምክር ቤት ሲሆን በጀት የሚያገኘውም ከክልሉ ነው። የተቋቋመበት ዋነኛ ምክንያትም የውስጥና የውጭ ታጣቂ ኃይሎች በክልሉ ህዝብ ላይ እያደረሱበት የነበረውን የፀጥታ ችግር በመደበኛ ፓሊስ ሊወጣው ባለመቻሉ መሆኑ ይታወቃል።

ይህ የአማራ ልዩ ኃይል እስካሁን ድረስ በአጣየ እና ሸዋ ሮቢት ከኦነግ ጦር ጋር በመዋጋት፣ በጎንደር ከቅማንት ታጣቂወች ጋር በመፋለም እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉምዝ ከክልል መንግሥት በተደረገለት ጥሪ መሰረት ወደ ክልሉ በመግባት የጉምዝና የኦነግ ታጣቂዎች እያደረሱ ከነበረው ጭፍጨፋ ህዝብን ከከፋ እልቂት ታድጓል።
ከዚህም አልፎ ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከአገር መከላከያ፣ ከፋኖ ሚሊሻ እና የአፋር ልዩ ኃይል ጋር በመሆን አኩሪ የውጊያ ድሎችን በማስመዝገብ አገርን ከውርደት መንግሥትን ከመፍረስ የታደገ የሃገር ባለዉለታ ነው።
ነገር ግን ለዚህ ላደረገው አስተዋጽዖ እና ለከፈለው መስዋእትነት ምላሹ ትጥቅህን ፍታ የሚል መሆኑ ከማስገረምም አልፎ አደገኛ አካሄድ መሆኑን ተገንዝበናል።
ለመሆኑ የኦሮሞ ብልፅግና ለምን በአሁኑ ወቅት የአማራ ልዩ ኃይል ትጥቅ እንዲፈታ ወሰነ? በእኛ እምነት በአምስት መሰረታዊ ምክንያቶች ነው ብለን እናምናለን፦

1. በፕሪቶሪያ ድብቅ ስምምነት መሰረት አብይ አህመድ ወልቃይትና ራያን ለትግራይ ለማስረከብ ስለተስማማ እንዲሁም ለአሜሪካኖች ቃል ስለገባ ይህንን ለማስፈፀም ልዩ ኃይሉ እንቅፋት ይሆናል ብሎ በማሰብ ለማፈራረስ ማሰቡ፣ ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆነወ የአማራ ልዩ ኃይል ከመከላከያ ጋር በተፈጠረው ግጭት ቦታዎችን መልቀቁን ተከትሎ የህወሓት ጦር ወደ ጠለምትና ራያ እየገባ መሆኑ እየተዘገበ መሆኑ ነው።

2. ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት ያደረገው ሙከራ ስላልተሳካ በቅድሚያ ልዩ ኃይሉን ትጥቅ አስፈትቶ በቀጣይ የፋኖንን፣ የሚሊሻውን እና የህዝቡን የግል ትጥቅ በቀላሉ ለማስፈታት እንዲችል በማቀድ፣

3. በወለጋ በአማራው ላይ የኦነግ ጦር ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጋር በመጣመር እያካሄዱ ያሉትን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ መጠነ ሰፊ የቤት ማፍረስና አማራውን የማፈናቀል ዘመቻ እንዲሁም አማራወች ወደ አዲስ አበባ አትገቡም የሚለው ክልከላና እንግልት አማራውን እንዲያመር ስላደረገው ለትግል መነሳቱ የማይቀር መሆኑን በመረዳት መሳሪያ አልባ ለማድረግ፣

4. የአማራ ብልፅግና አንዳንድ የበላይ አመራሮች በተለይም የዞንና የወረዳ አመራሮች የህዝቡን ብሶት ማንፀባረቅ በመጀመራቸው ክልሉ በራሱ የመወሰን አቅም ሊያመጣ ስለሚችል ለመቅጨትና የስልጣናቸው ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ እንዳይወጣ ለማድረግ፣

5. የኦሮሞ ብልፅግና የኦነግን የዘመናት ጥያቄ በማንገብ ኢትዮጵያን በማፍረስ አዲስ አገር ለመፍጠር ወይም የኦሮሞን የበላይነት የምትቀበልና ኦሮማዊት የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ካለው እቅድ አንፃር ግዛት ማስፋቱ ዋናው አጀንዳ በመሆኑ አዲስ አበባን ከመሰልቀጥ፣ ቤንሻንጉልን ጋምቤላን ከመዋጥ ብሎም በሶማሊያ፣ በሲዳማ በደቡብ ክልል ዙሪያ ያለውን የመስፋፋት እቅዱን ተግባራዊ ከማድረግ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ይገዳደረኛል ብሎ ከማሰብ የተነሳ ነው።

በመንግሥት ባለስልጣናት በኩል የሚናገረውና ልዩ ኃይሎችን ወደ መከላከያ ለማዞር የበለጠ አገራዊ ኃይል አቅም ለመፍጠር ነው እንጂ ለማፍረስ አይደለም የሚለው አባባል ፍፁም ውሸት ነው። የታሰበው የአማራ ልዩ ኃይልን ለማፍረስ ነው። ለምን የአማራ ክልል ብቻ የሚል ጥያቄ ሲነሳ ሌሎችንም ያጠቃልላል በሚል ህዝብን ለማሞኘት እየጣሩ ይገኛሉ። ነገር ግን ህዝቡ ስለነቃ ሰሚ አላገኙም። ዋናው እቅዳቸውን በአምባሰደር ተሾመ ቶጋ በኩልና ከአማራ ክልል የፓሊስ ኮሚሺነር በኩል ትጥቅ ፍቱ የሚለው ትዕዛዝ በግልፅ እንዲታወቅ ሆኗል።

ለመሆኑ የአማራ ክልል በአሁኑ ሰዓት የህልውና ስጋት የለበትም? በትክክል ከህወሓት፣ ከኦነግና ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል እንዲሁም ከሱዳን ወራሪ ጦር ከፍተኛ የህልውና ስጋት አለበት። በአሁኑ ሰዓት ኦነግ በአጣየና አካባቢው ጦርነት በአማራው ላይ ከፍቷል።

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በብዙ የአማራ ከተሞች በመከላከያ ስም በመግባት በህዝቡ ላይ ግልፅ ጦርነት እያካሄደ ንፁሀንን እየጨፈጨፈ ይገኛል። ህወሓት በፌደራል መንግስት በመታገዝ ወልቃይትና ራያን በጦርነት አሸንፎ ለመያዝ ሰራዊቱን እያስጠጋ ይገኛል።
መንግሥትም ታስረው የነበሩ የትግራይ የጦር መኮንኖችን በመፍታት ወደ ትግራይ እየሸኛቸው ይገኛል። ሱዳን የአማራ ልዩ ኃይል ይዞት የንበረውን ካምፕ መልቀቅ ተከትሎ ጦሯን አስገብታ የኢትዮጵያን መሬት በስፋት እየተቆጣጠረች ትገኛለች። እንግዲህ ይህ ከሁሉም አቅጣጫወች የጦርነት ስጋት ባለበት ሁኔታ ነው አማራው ትጥቁን እንዲፈታ የተወሰነበት። ለምንድን ነው ይህ የሚሆነው ቢባል የተፈለገው አማራው ያሉትን ጥያቄዎች ሁሉ ትቶ በባርነት ታዛዥ ሆኖ እንዲኖር ብሎም የኦነጉ መንግሥት አዲስ አገር የመፍጠሩን ወይም የኦሮሞን የበላይነት ለማረጋገጥ የወጠነውን ፕሮጀክት እውን ለማድረግ እንቅፋት እንዳይፈጥርበት ለማድረግ ነው። ይህን በመረዳት ልዩ ኃይሉም ሆነ ህዝቡ ውሳኔውን እንቃወማለን ብሎ ለሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ጨፍጫፊ ኃይል ተልኮበታል። በብዙ ሚዲያወች እንደተዘገበው አብዛኛው ወደ አማራ ክልል ለወረራ የገባው የመከላከያ ልብስ የለበሰ የኦሮሞ ልዩ ኃይል መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ ወራሪ ኃይል በፍፁም ጭካኔ ህዝቡን በከባድ መሳሪያ እየጨረሰው ይገኛል። ብዙወች ተገድለዋል እንዲሁም ቆስለዋል። ህዝቡ ግን ለህልውናው በመዋደቅ ላይ ይገኛል። መሆንም ያለበት ይኸው ነው። የዓለም አቀፍ የአማራ ሕብረት ከተገፋው የአማራ ህዝብ ጎን መቆሙን ያሳውቃል።

የአማራ ክልል መንግሥት በዚህ ወሳኝ የትግል ምዕራፍ ወቅት ህዝቡን ክዶ ከወራሪው ኃይል ጋር ወግኖ መቆሙ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር ነው። አሁንም የበለጠ ደም መፋሰስ ሳይፈጠር ከህዝቡ ጎን በመሆን የትግሉ አካል እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን።

ኢትዮጵያ አገራችን ከዚህ የበለጠ ትርምስ ውስጥ እንዳትገባ ለመንግሥትና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የሚከተሉትን ጥያቄዎች እናቀርባለን፦

1. በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው የህልውና ስጋት እስኪቀረፍና አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ ልዩ ኃይሉ በፊት በነበረው ሁኔታ እንዲቀጥል፣
600 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 11:56:14
የኦነጋውያን ፀብ ከትውልድ ጋር ነው !!

ጠላትነታቸው ካለፈው ዘመን ጋር ብቻ ሳይሆን ከዛሬ እና ከነገ ዘመን ጋር ጭምር ነው።

ትውልድን ጠልተዋል ፣ ትውልድን አጥቅተዋል ፣ ትውልድን በደል አውርሰዋል።

እየለመነች እህትና ወንድሟን እየረዳች የነበረችው የ9 አመት ልጅ ታዳጊ ፤ አሊያም እነዚህ ተማሪዎች ሁሉ ነገ የሚመሰክሩት የትውልድ ግፍ አለ። በአገራቸው ማን ተሳዳጅ እና ተፈናቃይ እንዳደረጋቸው ያውቃሉ !!


ስርዓቱ ጠላትነቱ ከትውልድ ጋር ነው !!


ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
550 views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 11:35:29
አዳነች እና ኦነጋውያን መልዕክት ተልዕኮላችኋል!!

የነገው ትውልድ የማፋረዳችሁ ወንጀለኞች መሆናችሁን ተቀበሉ !!


ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
609 viewsedited  08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 11:28:56
ጀግናዋ እህታችን ጋዜጠኛ ገነት አስማማው በ10ሺ ብር ዋስትና እንድትለቀቅ ፍ/ቤቱ ወስኗል።


ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
622 viewsedited  08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 10:08:36 ከአማራ ህዝብዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አሻራ ሰሜን አሜሪካ
ሚያዝያ 9 ቀን 2015 ዓ. ም.

የአማራ የውርደት ዘመን የሚያበቃበት ጊዜ አሁን ነው!

በጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ እና በኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ላይ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ጥሪ
ሚያዚያ 9, 2015

የተከበርከው የአማራ ሕዝብ:-
ባሳለፍነው ሳምንት የአማራ ሕዝብ በአብይ አህመድ፣ በኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ እና በባህር ዳር በሚገኙ በኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ የአማራ ተላላኪዎች የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም የአማራ ክልል ልዩ ሃይልን ለመከላከል፣መዲናችን አዲስ አበባ እንዳንገባ የተደረገው እገዳ እንዲቆም፣የፖለቲካ እስረኞችን እና ጀግኖቻችንን እንዲፈቱ በሚሊዮኖች ተነስተን ድምፅ አሰምተናል። ቁጣህን ለአለም አሳይተሃል፥ ገዥው ቡድን ምን ያክል አንደተርበሸም አይተሃል፥፥

የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ክልሉን ከትህነግ፣ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል እና ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ) ሲጠብቅ ከርሟል። የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ለአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ወሳኝ ሆኖ ቆይቷል። አብይ አህመድ ፣ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ እና በባህርዳር የሚገኙት አሻንጉሊቶቻቸው የህዝቡን የጸጥታ ምሰሶ ነቅለዋል።
የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በርካታ የአማራ አርበኞችን በሸዋ ሮቢት ከተማ ጨፍጭፈዋል።መከላከያ ሠራዊት እና አጋሮቻቸው በመንገድ ላይ የነበሩ በርካታ የአማራ ልዩ ሃይሎችን ገድለዋል።

የጀግኖቻችንን መስዋዕትነት እያከበርን ለቤተሰብ እና ወዳጆቻቸው ሀዘናችንን እንገልፃለን። ገዳዮቻቸው ፍትህ እስኪያገኙ ድረስ በፅናት አንታገላቸዋለን::
የአብይ መንግስት ይህንን የጸጥታ እጦት በመጠቀም የወልቃይት፣ የጠለምት እና የራያ ታሪካዊ መሬቶቻችንን ለትህነግ ሊሰጥ ዝግጅት ጨርሷል። በተጨማሪ የኦሮሙማ ገዥ ቡድን ታሪካዊ መሬቶቻችንን አጣዬ እና ሸዋ ሮቢት ለራሱ ሊወስድ እየሞከረ
ነው። የኦሮሙማ ገዥ ቡድን እና አጋሮቹ ሁላችንንም ሊያስጨርሱን እና እንደ ህዝብ ሊያስወግዱን ቆርጠው ተነስተዋል::

የአማራ የውርደት ዘመን የሚያበቃበት ጊዜው አሁን ነው። ይህ ወቅት ለፋኖ አርበኞቻችን እና በመላው አለም ለሚገኙ አማራዎች ታሪካዊ እና ወሳኝ ጊዜ ነው። ፋኖ ትጥቅ አትፍታ! የአማራን ህዝብ ጠብቅ! ጨቋኞችን ሁሉ ያሸነፈ ኩሩ የተከበረ ታሪክ አለን። ታሪካዊ ባህላችንን በማደስ ህዝባችንን፣ መሬታችንን፣ ባህላችንን፣ ታሪካችንን እና ማንነታችንን ከወራሪዎች ለመጠበቅ በአንድ ላይ የምንነሳበት ጊዜ አሁን ነው።

በመሆኑም መላው የአማራ ሕዝብ ከዚህ በታች ያሉትን እርምጃዎች በአስቸኳይ እና በቋሚነት እንዲወስድ እንጠይቃለን።

1. ገንዘብህን በሙሉ ከመንግስት ባንኮች ወደ ግል ባንኮች አስገባ።

2. ለአብይ መንግስት እና ለተላላኪዎቹ ግብር መክፈልህን አቁም።

3. የብአዴን፣ የብልፅግና ካቢኔ አባላት፣ የብአዴን ኮሚቴ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በመደወል የአብይ እና የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ አሻንጉሊት በመሆናቸው እራሳቸውን እና የአማራን ህዝብ ነግራችሁ ገስጿቸው። በአማራ ላይ የያዙትን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲቀጥሉ መፍቀድ የለብንም። ከማንኛውም ማህበራዊ እንቅስቀሴዎችና ግንኙነቶች አግልሏቸው።

4. በመንግስት ከተያዙ ንግዶች እና መንግስትን ከሚደግፉ የንግድ ድርጅቶች ምንም አይነት አግልግሎት አትጠቀሙ::

5. በመንግስት ባለቤትነት የተያዙ ሚዲያዎችን፣ ባለስልጣናትንና ደጋፊዎቻቸውን በማህበራዊ አውታር መደቦች መከተል አቁሙ።

6. ከማንኛውም የመንግስት ሚዲያዎች እና ለመንግስት ሚዲያ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ዝግጅቶች ላይ ከመሳተፍና ቃለመጠይቅ ከመስጠት ተቆጠቡ።

7. በአማራ እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የመንግስትን ፕሮፓጋንዳ የሚያራምዱ ፕሮግራሞችን እንዳያዘጋጁ የራሳቸውን ህዝብ በሚዲያ ከማዋረድ እንዲቆጠቡ ጥሪና ግፊት በማድረግ ገስጿቸው።

ዲያስፖራ አማራውዎች የአማራ ህዝብ ወዳጆች:-

8. በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ የአማራ ተላላኪዎች የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመቃዎም የአደባባይ ሰልፎችን በማድረግ ለህዝባችሁ ያለመታከት ድምፅ ሁኑ። በአብይ መንግስት ላይ ማእቀብ እንዲጥሉ ጠይቁ

9. ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ለመላክ የመንግስት ቻናል አይጠቀሙ። የአብይ መንግሥት ላይ ማእቀብ ጣሉ። ዶላታችሁ አብይ ከእናንተ አንድ የሚፈልገው ነገር ነወ።። በእርሱና በኦሮሙማ አገዛዙ አንድ ያለለችሁ ወሳኝ መሳሪያ ነው።

10. በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ማዕቀብ ጣሉ። በግልም ሆነ በመስሪያ ቤት ለሚደረጉ ጉዞውች የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከመጥቀም ታቀቡ።

አመራሩ ተጨማሪ የሚወሰዱ እርምጃዎችን የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በዓል ካከበሩ በኋላ ያሳውቃል::

የአብይ አህመድና ተላላኪዎቹ አገዛዝ መውደቁ የማይቀር ነው። በህብረታችንም ውድቅቱን በአጭር ጊዜ እውን እንዲሆን እንሰራለን።

የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ አመራር




ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
675 views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 20:26:15 የጥንቃቄ መልክት!

" የአማራ ልዩ ሀይል ዩኒፎርም በመልበስ የጥይት ተኩስን ጨምሮ ሌሎች ህዝባችን የማይፈልጋቸው ተግባራት በሴረኞች ተልዕኮ እየተፈፀሙ መሆኑን የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።በመሆኑም ይሄን ፖለቲካዊ ሴራ መሆኑን በመረዳት የታቀደልንን ሴራ እንድናከሽፍ እናሳስባለን።

በፋኖ ስም እና በልዩ ኃይል ስም በሚፈፀሙ ወንጀሎች ህብረተሰቡን የማማረር እና መንግስት ትክክል ነው ለማስባል የታሠቡ ሴራዎችን ሁሉም አማራ በትብብር ማክሸፍ አለበት።

የልዩ ኃይልና ፋኖ አባላት እነዚህን መሠል ወንጀሎች በሕዝባችን ላይ እንዳይፈፀሙ መከላከል እና አባሎቻቸውን ማረም አለባቸው።

በተጨማሪም በተለያየ መልኩ የጠላት መጠቀሚያ እየተደረጉ ያሉ ንግግሮችን ለማስቀረት ከየትኛውም የሚድያ መግለጫ እና አስተያየት ከመስጠት እንዲቆጠቡ ወንድማዊ እና እሕታዊ መልዕክታችንን ለማድረስ እንወዳለን። "



ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
830 viewsedited  17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 17:47:31
" Give 50 dollar for easter holiday"

ክብረ ነክ ነው።
ኢትዮጵያ ነች የተዋረደችው። የዘመኑ ቢሮክራሲ እንዲህ መላቅጡ ጠፍቶት የአገር ገመና እየተሸጠ ነው።

በአዲስአበባ መሬት እና የክፍለከተማ ዝርፊያ የሰለጠነው የብልፅግና ሌብነት ድንበር አልባ ነው። እናም የአደባባይ ዝርፊያ ድንበር ተሻገረ።
አሁን በኩራት፣ በአርበኝነት እና ሉዓላዊነት የሚያውቁን አፍሪካውያን በዝርፊያና ጉቦ በሚተነፍስ ቢሮክራሲ እየተዋወቁን ነው።

የሌማት ትሩፋት ነው መሰል




ድል ለአማራ!
#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
945 views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 16:24:01
እነ ብርሃኑ ጁላ በክፉ የማያነሱት አሸባሪ

በፎቶ የምትመለከቱት የከሚሴው "ሸኔ" ነው። የዚህ ቡድን መሪ ትህነግን ከሚሴ ላይ ተቀብሎ ሰራዊቱን የወጋ ነው። በድምፀ ወያነ ቲቪ ዜና የቀረበው የቡድኑ መሪ ከጦርነቱ ቀደም ብሎ በሰራው ወንጀል ደብረብርሃን ላይ ታስሮ ነበር። የኦሮሚያ ብልፅግና በክልሉ ፖሊስ መንገድ አዘግቶ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ እንዳያልፍ አድርጎ ነው ያስፈታው።

ከዚህ በኋላ የኦሮሚያ ብልፅግና አጀንዳ ሲፈልግ ይህ ቡድን አጣዬንና አካባቢውን እንዲያጠቃ ያደርገዋል። ሰሞኑን ልዩ ኃይሎችንና ንፁሃንን ከሚሴ ላይ ያጠቃው ይህ ቡድን ነው። ጥቃቱን የፈፀመው በመዋቅር መረጃ ተሰጥቶት ነው። የእነ ብርሃኑ ጁላን ጥላቻ ለተመለከተ መረጃ አይሰጡትም ማለት ይከብዳል።

ይህ ቡድን ትጥቅ አልፈታም። እንዲፈታም አይፈለግም። ህዝብና ሰራዊት ሲያጠቃም እነ ብርሃኑ ጁላ ስሙን አያነሱም። በሀሰት ፋኖ ልዩ ኃይልን የመታ አስመስለው ሲያቀርቡ ይህ ቡድን በቀደሞ ከሚሴ ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ጥቃት ግን አይናገሩም። ምክንያቱም አጀንዳ ማስፈፀሚያቸው ነው።

በነገራችን ላይ ባለፈው እነ ምሬ ጋር ሰላም የተፈጠረው በአካባቢ ሽማግሌዎችና በቀጠናው ባሉ የሰራዊት መሪዎች እንጅ እነ ብርሃኑ ጁላ ችግሩ እንዲፈታ አይፈልጉም። በቀጣይም ሰበብ እየፈለጉ ችግር ይፈጥራሉ። በአማራው ላይ ችግር ሲፈጥሩ ግን ከሚሴ ያለውን አሸባሪ በክፉ ስሙን ማንሳት አይፈልጉም።
/ጌታቸው ሽፈራው/
32 views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ