Get Mystery Box with random crypto!

ሽፈራው የሶማው

የቴሌግራም ቻናል አርማ rasmeried — ሽፈራው የሶማው
የቴሌግራም ቻናል አርማ rasmeried — ሽፈራው የሶማው
የሰርጥ አድራሻ: @rasmeried
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.22K
የሰርጥ መግለጫ

የአማራ ሕዝብ የሕልውና የፍትህ እና ርትዕ ትግል ትክክልና ድል መጎናፀፍ ያለበት ነው።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-01 08:50:09 ኦህዴድ መራሹ የዐቢይ አህመድ መንግሥት "የአማራ ሕዝብን እንደ ሕዝብ የምናደርስበትን መከራ ለምን ድምፅ ሆናችሁት" በሚል በርካቶችን እያሳደደ እና እያሰረ ይገኛል።

በዛሬው ዕለትም እኔን እና ወንድሞቼን "ሕገ - መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ" በሚል በሽብር ወንጀል እፈልጋቸዋለሁ እያለ ነው።

ወንድማችን ግርማ የሺጥላን የገደለው ኃይል ከያዛቸው ከወራት በላይ የሆናቸውን እንዲሁም ፍርድ ቤት የዋስ መብት የሰጣቸውን ግለሰቦች የዋስ መብታቸውን ነፈጎ በአዲስ ክስ ለመመሥረት አመቺ መንገድ መፍጠሩ ነው። የዐቢይ አህመድ 'መንግሥት' የጡት አባታቸውን ሕውሓትን ከምኒልክ ቤተ መንግሥት ከመባረር እንዳላዳናቸው ማወቅ ተሥኗቸዋል።

በወንድሜ ሻለቃ ምሬ ወዳጆ እና በፋኖ በለጠ ጋሻው የተቀነባበረው የድምፅ ልውውጥም በማን እንደተቀነባበረ እንኳን እንደ እኔ አይነቱ ጋዜጠኛ እና የሳይበር ደህንነት ስልጠና ለወሰደ ሰው ለተራ ግለሰብም ሀሰተኛ የድምፅ ቅንብር መሆኑ የሚሰወር አይደለም።

እኔ አንድ አማራ ነኝ፤ በአማራነቴ የመጣብኝን መከራ እቀበለዋለሁ። ነገር ግን ስንቱን ገድሎ እና አፈናቅሎ እንደሚጨርሰው አብረን የምናየው ይሆናል። እኔና ሌሎች ጓዶቼ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከፈጣሪ የተሰጠውን የመኖር መብት ቀምተን ከባሪያ ያነሰ አኗኗር እናኑራችሁ ለሚለን አካል እሺ እንደማንል ያደግንበት ሥሪትም ሆነ ሥነ - ልቦናዊ ውቅር እንደሌለ ልታውቁት ይገባል። ስለዚህ እንኳን የእስር ማደኛ አግኝታችሁ ብትሰቅሉኝም ከባሪያ ያነሰ ሕይወት ከምገፋ ለነጻነቴ እየታገልሁ ብሰቀል አይቆጨኝም።

የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ሁሉም ፋኖ መሆኑ እየታወቀ "ኢ - መደበኛ" ማቃለያ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ፈርጆ ለማጥፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ መላው የአማራ ሕዝብም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊያን ብሎም ለሰብዓዊ መብት መከበር የቆሙ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጉዳዩን በልዩ ትኩረት እንዲከታተሉት እና እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ እና የዘር ማጽዳት እንዲያስቆሙ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ።

በመጨረሻም፦
አማራ ግን የታወጀብትን የዘር ጭፍጨፋ እና የዘር ማጽዳት ግን ቀልብሶ እንደሚወጣ እርግጠኛ ነኝ!
136 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:49:40 ወንጀላቸው/ወንጀላችን አማራነት ነው፤
ነጻ መውጫቸውም አማራነትን መታደግ ነው
--
ዶር አምሀን፣ ልደቱንም ሆነ ቴዎድሮስን ሆነህ ይህን ጸረ አማራ ፋሽስት ስርአት አታመልጠውም።
የፈጸመከው ወንጀል ባይኖር እንኳ አማራነትህ ተጣርቶ ያስወነጅልሀል።

የአማራ ብሄርተኝነት ተቃዋሚም ሆነህ አማራነትህ ወንጀል ሆኖ ትታሰርበታለህ፣ ትሳደድበታለህ፣ ትገደልበታለህ።
አየህ ክሱም-ወንጀሉም አማራነት ነው። ርዕዮቱም ጸረ አማራነት ነው። ፋሽዝም የምንለው ይህን ነው።

የትኛችንም እንደ ሰው እና እንደ ዜጋ ያሉንን መብቶች የተቀማነው የፈጸመነው የተለዬ ጥፋት ኖሮ ሳይሆን አማራነታችን የወንጀል ክስ ሆኖ ተቆጥሮብን ነው።
ይህን እንደ አማራ በጋራ የቀረበብንን ክስ፣ የታወጀብንን የሞት ፍርድ እና ያለንበት የህልውና አደጋ እንደ አማራ ከመመከት ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።

የአማራ ህዝብ የገጠመው አደጋ ህዝባዊ ማለትም ብሄራዊ ነው። ይህ አደጋ ሁሉም አማራ በመሆኑ በሁሉም ቦታ የገጠመው እና የሚገጥመው መሆኑ የፖለቲካ ዲስኩር ሳይሆን ነባራዊ ሀቅ ነው። የአደጋው ክሱትነት እየበለጠ እየጨመረ የሚሄድ፣ ሁሉም ላይ የደረሰ ነው። የመንግስታዊ ስርአቱ ፍሬ ነገር ውስጥ ያለው አማራ ጠልነት እና የአገዛዙ ፋሽስታዊነት እስካልተሸነፈ ድረስ ከህልውና አደጋ ማምለጫ ሌላ መንገድ የለም።

አደጋው መገለጫዎቹ ዘርፍ ብዙ ከመሆናቸው ውጪ ሁሉም አማራ አደጋው ገጥሞታል፣ ይገጥመዋልም። አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጥቃቶችን በተለያየ መጠን ከገጠመን ውጪ የሆኑት አማራ በመሆናቸው ብቻ የጠላትነት ክስ ተፈራጅ በመሆናቸው ብቻ ስጋቱን ይጋራሉ። ይህም የህልውና አደጋውን ብሄራዊነት በግልጽ ያሳያል።
እናም በመሸሽም ሆነ በመደበቅ የሚመጣ ትድግና የለም። ይህን አደጋ በሙያ ልህቀት፣ በሀብት መጠን አለያም በመዋለድ አናመልጠውም።

ይህን አደጋ ለመቀልበስ ደግሞ ልምምጥም ሆነ ተሸናፊነት መፍትሄ አለመሆኑን ከዚህ ቀድሞ ከሞከሩት መረዳት ይቻላል። በተለይ ቀደምት ብአዴኖች በሀሰት ተረክ ላይ የተመሠረተውን ክስ ላይ ያመቻመቹ እና የተቀበሉ [Offender appologizers] እንዲሁም ተጠቂን አጥፊ አድርገው የሚቆጥሩ ነበሩ። ይህ መንገድም ጠላት ብርታት እና ድፍረት አግኝቶ ጥቃቱን እንዲጨምር አድርጓል። ስለዚህም መታገል ብቸኛ የህልውና ማረጋገጫ መንገድ መሆኑ ሀቅ ነው። የትግሉ መንገድም ብሄርተኛ አደረጃጀት ነው።
|
በጋራ የተቃጣ ጥቃት በግል አለያም በንዑስ ቡድን ተከፋፍሎ ሊመከት እና ሊቀለበስ አይችልም። እናም አንደ አማራ መደራጀት ልከኛው [normative] የአደረጃጀት መንገድ ነው። ከልከኛነቱ በተጨማሪ በንዑስ ቡድን ተከፋፍሎ የሚደረግ ትግል ውስን አቅምን በመከፋፈል የጋራ ትግሉን የሚያዳክም እንዲሁም ለጠላት የከፋፍሎ መግዛት ስትራቴጂ የሚያጋልጥ ነው። ካለፈው ሂደት እንዳየነው በጥቂቱም ቢሆን በጋራ የተሰለፍንባቸው የትግል አውደ ውጊያዎች አንጻራዊ ድል አግኝተንባቸው ነበር። ከዚህ ትይዩ በንዑስ ቡድን ተከፋፍለን በሄድንባቸው ጊዜያት ለጠላት ጥቃት የበለጠ ተጋላጭ ከመሆን ባሻገር፣ ጠላት በምርጠታዊ አስቀምጦ [Selective accommodation] ከመካከላችን ልዩ አጋር እና ልዩ ጠላት በሚል ብያኔ በሚፈጥረው መከፋፈል የጋራ አጀንዳዎችን ተትተው፣ የጎንዮሽ ሽኩቻዎች ጨምረው፣ የተናጠል ጥቃቶች በርትተው ፣ በጥቅሉ ደግሞ የጋራ ብሄራዊ አደጋው ከመቼውም በላይ ከፍቶ አግኝተነዋል።

¶ እናም እንደ አማራ መደራጀት ከልከኛነቱ በተጨማሪ ገቢራዊነቱ የግድ አስፈላጊ ያደርገዋል።
ያለ መደራጀት በተለይም እንደ አማራ ያለመደራጀት ያስከተለብንን ኪሳራ በተጨባጭ እየኖርንበት ነው።
ሌላው ይቅርና የአማራ ክልል አማራር ውስጥ ያለው ጉራማይሌ እና አመንታችነት [ማመናታት] አደረጃጀቱ ያስከተለው ችግር ነው።

እናም በአማራነት ተደራጅቶ ከመታገል በስተቀር ሌላ መፍትሔ የለም።

ድል ለአማራ !

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
212 views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:49:12 "የአማራ ንቅናቄ የማይታወቅ መሪ ሊፈጥር ይችላል" አሉ። ስለዚህም የማይታወቅ መሪ እንዳይመጣ አለ የሚሉትን አማራ ሁሉ በያለበት እያደኑ ያስራሉ። ከታጠቀው ወጣት የሚመጣ መሪም እንዳይመጣ እያደኑ ይገድላሉ።
እየሆነ ያለው ይህ ነው። የብዐዴን ደነዞች ፣ እንደነአበባው ታደሰ እና ተመስገን ጥሪነህ ያሉ የትምሕርት ፆመኞች ደግሞ በዚህ የጠላት አላማ አስፈፃሚነት ተሰልፈዋል።

ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
254 views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 14:11:58
በኦሮሚያ ክልል ከህግ ውጪ ነጻነታችንን ተነፍገናል ያሉ ሰዎችን አቤቱታ መቀበሉን ኢሰመኮ ገለጸ።

April 30, 2023

በመድረኩ ላይ ግለሰቦችና ባለግዴታዎች ተገኝተው አቤቱታ እና ክርክር ማድረጋቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ሰብዓዊ መብታችን ተነካ ያሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ባለግዴታዎች በአንድ መድረክ የተገኙበት የግልጽ መድረክ ማካሄዱን አስታውቋል፡፡
የግልጽ የምርመራ መድረኩ ተጎጂዎች፣ ባለግዴታዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እልባት ለማስገኘት እና አስቀድሞ ለመከላከል የመፍትሔ ሐሳቦችን ያመላከተ እንደሆነ ኮሚሽኑ ለአል ዐይን በላከው መግለጫ ገልጿል፡፡
ኮሚሽኑ ከሰሞኑ በአዳማ ከተማ አራተኛውን ግልጽ የምርመራ መድረክ ማካሄዱን የገለጸ ሲሆን በመድረኩ ላይ የዘፈቀደ እስር፣ የተራዘመ የቅድመ ክስ እስር እና በእስር ወቅት ተከስተዋል ስለተባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የተጎጂዎችን እና ምስክሮችን አቤቱታዎች አድምጫለሁ ብሏል፡፡
 
942 views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:49:55
870 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:48:51 ምንም ነኝ ግን አማራ ! ለዚያውም ደሜ አረንጓዴ
(ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ!)
==============
ምንም ነኝ ግን አማራ ...
ሰዋሰው ... የሰው እኩል ...
በወለባ ... የማልኩል
በስሜት የማልኮለኩል
ምንም ነኝ ... ግን አማራ ... የሰው አቻ ...
የማልንጠረበብ እንደ ቅምብቻ
ምንም ነኝ ... ግን አማራ ...
የፈጠረኝን አምኜ ...
በጎቼን ከተኩላ ጋር የማሰማራ ...
አማራ ነኝ የጠራሁ ...
ኩራት እንጂ ሞት ያልፈራሁ
አማራ ነኝ መቃ አንገት ...
ራሴ ከብዶኝ የማልንገታገት ...
የሰው ጣባ ሥር የማልለገት ...
ዙርያ ገባውን ቃኝቼ ...
ትሻልን ከትብስ አገናኝቼ
አይበጆን ከነመናጆው ባሕር ዙልማ ሸኝቼ ...
የቀኑን እያንቀራጨሁ ...
ደሞ ሌሊቱን እየፈጨሁ ...
ለጎጆዬ የታጨሁ ...
ባሰኝ ብዬ ያልጫጨሁ ...
በወለምታ ያልተቀጨሁ ...
ልጄ ለሰማእትነት ተመርጦ ባንዳ ባረር ቢቀነጥሰው
ሞተ ብዬ ... ደረት ጥዬ ፊት ያልነጨሁ ...
ባለፈው ያልተቆጨሁ ...
አማራ ነኝ ዓይኔን ብከድንም ... እንቅልፍ አላውቅም
ማማ ላይ ነው አዳሬ ...
ገና አባርራለሁ ዋኔ እኔ አለቅም።
ዓይኔ ደጀን ...
ልቤ ግሸን ...
ደሜ አረንጓዴ ...
ጓንዴዬ ጓዴ ...
ቃሌ ደም ... ምግባሬ ደም ...
እንኳን ለቃጣኝ ... ላሰበኝ የማልቀደም ...
ለትንሳዔ የምታደም ... የትም የማልጋደም ...
የትም የማልስደመደም
ማንም እንዳስመለከተው ... ያሻውን ስም ቢያወጣልኝ
እድሜ ለዓባይ ጣና ልጅ ...
ያኔ የማስቆርሰው ድፎ ዳቦ አያጣልኝ ...
ሰምና ወርቅ ቅኔ ...
ጠኔ ያጥን መጥኔ ...
ይኸው ነው ሥርወ ውልደቴ
አማርኛ ነው ውጥኔ ...
አማራ ነው ምጥኔ ...
እንኳን ሰው ወፍ አልምጄ ...
እንኳን ሌላ ጥላ አጥምጄ ...

በፍቅር ተገድጄ ...
ውሌን ሳልስት ...
ጉልበቴን ሳልሰስት ...
የልቤን በልቤ ቅስት ሳልሰድር ...
ተኝቼ የማላድር ...
ቼ በወሎ ፈረስ ካይኔ ልቤ ድረስ እያልኩ ...
አዘቦት አልቦዘንኩ ባል አላበልኩ
የቀላወጠው ወጥሮት ... ክንዱን በኔ ሊፈትን
ገና ሲያስተነትን ...
ከነገር ቀደም ሳይመክር በፊት ...
ባባቴ ጋሻ በናቴ ወንፊት
ወደፊት እንጂ ... ምን አለ ሌላ ...
እንኳን መብላት ማብላት ቀርቶበት ...
ለታጠረ በእምነቱ ኬላ
ነፍሴ አውጪኝንማ ማን አስቦት
ዘር ከልጓም ስቦት ...
እንደ ቅዱስ ላሊበላ ንጉስ
ሹመት አይጠናኝ ... አይጠፋኝ ጉግስ
ግብር ጥዬ እንኳ ባልደግስ ...
እንኳን ለጠላቴ
ለወዳጄስ ቢሆን ደም እንጂ ሌላ አለግስ!
ድኃ ነን ብለን ስንል እኮ ... በሰው ልጅ ፍቅር ተጠልፈን ...
እህል ተጠይፈን ...
ለሞት ተሰልፈን ነው እንጂ ...
የምንበላው ቢገደን ... መለኮት ባሕሪም አላነሰን
ክፉ ጥፉ ብሎ እንደ ጨው ዘር የትም አልነሰነሰን ...
ሳይንትና ተንታ ... ዋ ክምበል ያድርገኝ
ምን አገር ቢሰፋ እንዳማራ አይገኝ ...
ቢሆንም አይደል ወይ ጨዋታው ...
አገሩን ... ልብ ውልቅ ድምብልቅ
እስክስታ እሚያስመታው
እና አማራ ነኝ ... መከራ የመከረኝ
መስእዋትነት ያጠነከረኝ ... ፍቅር የተዘከረኝ ...
ብፈራ እንኳ ፍቅርን ነው እንጂ ... በሌላ አልጠረጠርም
ማንም እንዳሻው ለክቶ ... እንዳሻው ሊቆርጠኝ ቢያልም ...
ከልክ አልፌ አላጥርም
ጉራም ቢሆን ልቀናጣ ...
ስሞ ባያሳድገኝ... ነክሶ እሚያነቃኝ አላጣ ...
ያው ወንድሞቼ ይመስክሩ ...
በናት ጡት ወተት ባይሰክሩ
የዛሬ ሃያ አመት ተክራርዋ ወርደውም ባልመከሩ ...
ግቻ ነክሰው ... ጦር ባይሰብቁ
ለዛሬዋለትም ባልበቁ ...
ለዚያውም ውለታ ሳይጠይቁ ...
ትሁት ነኝ እንኳ ባልል እንደ ጠሎተ ሐሙስ ...
ሸቀንና ሰቀቀን ላራግፍ ...
ጦም ሽሬ የማልገድፍ ...
ግን አማራ ነኝ...
እኔው ገምቼ ...
እኔው ዘምቼ ...
እኔው ሞቼ
ክፉ መሻቴን እና ምኞቴን ተጠይፌ ስጋዬን ልሰቅል
ድፍት የምል እንደ ብቅል ...
ጣብያ ሳላቀላቅል!
ኮርማ ሳላዳቅል!
በአ ቅ ል!

እና አማራ ...

የፈጠረውን አምኖ በጉን ተኩላ ጋር ካሰማራ ...
እስቲ ደሞ በልብ እንደመሙላታችን ... ለደራ ሳይሆን
ካይንህ ይፍሰስ ይልቅ ...
እንደው ላይን ላይደምቅ
ፈፋው እምቅ ...
በጠመቅ ...
አምባውን እንደሹሩባ ... በክትር ሰርቶ ...
ለሽማግሌ ጥላ ... ለእንቦሳ መገሌ ...
ለልጅ ሰተቶ ...
መውጫው ጠፍቶን እንዳንንገዳገድ
ደሞ ጨዋታ ... አንድ ለመንገድ ...
እሰጠው ባጣስ ... ለምን ጦም ልደር
እሳትና ጢስ ጠፍቶ ... ከመንደር ...
ንሳማ ጎበዝ ... ንሳ ተነስነስ ...
ከስፍርህ ጎለህ ከሰው አትነስ!

ንሳማ ጎበዝ ... ንሳ አታደግድግ ...
ወገብን ጠበቅ ... ባንጀት ድርብ ድግ ...
እንኳን እቁቡ ... እድሩ ፈርሶ ...
የወላድ ማህፀን ... በዋይታ ታርሶ ...

አማንስ ቢሆን ... ለተቀመጠ ...
እያላመጠ ... እየገላመጠ ...
እየተርመጠመጠ ... እየተዳመጠ
እድሜውን ይፈጃል እንጂ በከንቱ ...
ማን ይለዋል አንቱ ...
ንሳማ ጎበዝ ... ንሳ ተነስነስ ...
ከስፍርህ ጎለህ ከሰው አትነስ!!
793 views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:48:04
ከአበባው ታደሰ ፣ ብርሃኑ ጁላ እና አብይ አሕመድ የተሻለ እና የበለጠ ግንዛቤ እና መፍትሔ ነው ስዩም ያቀረበው !!

ስዩም ያልገባው ሆን ተብሎ በትኖ በመግደል የአማራን ኃይል አቅም የመንሳት አላማ ስለመኖሩ ነው የዘነጋው። ሆን ብለው እንደሚሠሩ ነው የሳተው።



ድል ለአማራ !!
1.8K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:03:35 የትግላችን አካል ያልሆነ ከእኛ ወገን አይደለም!!

አማራ እየተጠቃ ፣ አማራ እየታረደ ፣ የአማራ ሕልውና አደጋ ላይ በወደቀበት በዚህ ወቅት ከትግል ውጭ መሆን አይቻልም!!
የአማራ ምሁር ፣ ነጋዴውና ባለሀብቱ ፣ ሲቪል ሰርቫንቱ ፣ ወጣቱ ፣ የኃይማኖት ሰው፣ አርሶአደሩ የትም ያለው ፣ በምንም ሥራ ላይ የተሠማራው አማራ በሚችለው ሁሉ ጠላትን የሚታገልበት ፣ ትግሉን የሚያግዝበት፡ የመጨረሻው ዘመን ላይ ነው !!

ከጠላት ጋር የተሠለፈ የአማራ ጠላት ነው!!
አማራ ሆኖ ከመካከላችን ተመልካች እና ዋዘኛ ከተገኘ የጠላት አካል ነው !!


ድል ለአማራ!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
620 views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 12:20:35
446 views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 12:20:35 ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሰሩት ሁሉ ቀይ ምንጣፍ ተዘርግቶላቸዋል!

ረሽድ አብዲ ኬንያ በሚገኝ የአንድ እንግሊዛዊ የግል የደህንነት ተቋም በኩል ኢትዮጵያን በቅጥረኝነት በሀሰት መረጃ ሲወጋ የከረመ ሰው ነው። ሰሞኑን እንድትበተን ሲሰራባት ወደነበረችው ኢትዮጵያ ተጋብዞ መጥቷል።

ይህ ሰው በጦርነቱ ለአገራቸው የተዋደቁ የፀጥታ ኃይሎችን ስም በሀሰት ሲያጎድፍ ነው የከረመው። በአንፃሩ ከውጭ አገር ሳይቀር መጥተው የፀጥታ ኃይሉ መለዮ ለብሰው ጠላትን የተፋለሙት፣ አገር ቤት ሆነው ከአገር ህልውና ጎን የቆሙት ጠላት ተደርገው ተፈርጀው፣ ለእስር ተዳርገዋል።

መልዕክቱ ግልፅም አደገኛም ነው። አገር አፍራሽ እንዲህ በገዥዎቹ ተፈላጊና ወዳጅ ሆኗል። በዚህ ወቅት የገዥዎቹ መመዘኛ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ነው። በአንፃሩ ለአገር የቆመ ፅንፈኛ ወዘተ እየተባለ እየተፈረጀ እየተጠቃ ነው።

ይህን የስርዓቱን ባህሪ መጀመርያ ማስረዳት ያለብን ለአገር ህልውና ለተዋደቀው የፀጥታ ኃይል ነው። በሀሰት ደፋሪ፣ ጨፍጫፊ ብለው በዓለም ያስወገዙት፣ ድል ሲያደርግ የተሸፈነ አስመስለው ያቀረቡት ሁሉ ክብር ተሰጥቷቸዋል። ከእሱ ጋር ምሽግ ውስጥ የከረሙ፣ ሲቆስል ያሳከሙት፣ ደም የለገሱለት፣ እንዳይራብ ስንቅ፣ እንዲድን መድሃኒት ያቀረቡለት፣ ስሙ እንዳይጠፋ የተከላከሉለት ጠላት ተደርገዋል።

በዚህ ወቅት ስርዓቱ የደም ዋጋ የከፈለውን የፀጥታ ኃይል የከዳውን ያህል ማንንም አልከዳም። የፀጥታ ኃይሉ በገዥዎቹ እንዝላልነት በተደጋጋሚ ከመመታቱ ባሻገር ከጎኑ የወደቁት፣ አካላቸውን ያጡት፣ በርካታ መስዋዕትነት የከፈሉትን ዋጋ ለማሳጣት የሰሩትን አክብሮ አብረውት የተዋደቁትን እያሳደደ ያለው የፀጥታ ኃይሉ ከከፈለው ዋጋ በተቃራኒ ስለቆመ ነው።

የፀጥታ ኃይሉ አገር ለማዳን ህይወት እንዳልሰጠ፣ አገር አፍራሾቹ የገዥዎቹ ወዳጅ ተደርገዋል። ይህን ለእያንዳንዱ የፀጥታ ኃይል ማሳየትና ማስረዳት አለብን። የከፈለውን ዋጋ፣ በጀግንነት የወደቁትን ወንድምህ እህቶቹን መስዋዕትነት እንዴት እንዳረከሱት ማስታወስ አለብን። ከእሱ ጋር አገር ለማዳን የወጡ የወረዱት በጠላትነት ተፈርጀው አገር ለማፍረስ የሰሩት፣ ነገም አገር ለማፍረስ የሚሰሩት የተሰጣቸውን ክብር እንዲያየው በተደራጀ መልኩ ማስታወስ አለብን። ክብርና ዋጋውን ያወረዱ በፀረ ኢትዮጵያ አቋማቸው በገዥዎቹ የተሰጣቸውን ሞገስ እንዲያውቀው ማድረግ ያስፈልጋል።
447 views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ