2023-04-15 17:30:37
የኦሮሙማ የጥቃት አድማስ እና የአማራው ምርጫዎች፤
የኦሮሙማ ፕሮጀክት አስፈፃሚዎች አማራውን አስጨፍጭፈውትም፣ አፈናቅለውትም፣ በአገሩ ስደተኛና ተፈናቃይ አድርገው በየድንኳኑ አስፈርውትም አልረኩም።
ጭፍጭፈውና አፈናቅለው በየጎዳናው ለማኝና ተመፅዋች አድርገውትም ፣ በሰሜኑ ጦርነት ውድመቶች ተጨፍጭፎ እና ወድሞላቸውም አልረኩም።
አማራውን በማፈን ፣ የመንቀሳቀስ እና ሠርቶ የማደር መብቶቹን ሁሉ ነፍገውትም ፣ የኢትዮጵያን እሥርቤቶች በአማራ ልጆች ሞልተውትም አልረኩም።
ዛሬም በወለጋ እያስጨፈጨፉት ነው፣ በዚህ ወቅት በምስራቅ አማራ እያስገደሉት ነው፣ ልክ በዚህ ወቅት በአዲስአበባ ዙሪያ ቤቱን እያፈረሱ እያፈናቀሉት ነው።
በዚህ ወቅት አገረ- መንግስቱን ከውድቀት የታደገውን የአማራ ልዩ ኃይል እያሳደዱት ነው፣ እየገደሉት ነው። በዚህ ወቅት በአዲስአበባ እንዳይመቸውና እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ የጥቃት መስኮች ከመንገድ ላይ ትራፊክ እስከ ቢሮክራሲ እያሰቃዩት ነው።
ይሔ ሁሉ ግን ሊያደርጉት ከሚፈልጉት አንፃር ፣ ገና እረፍት የሠጣቸው አይደለም። ኦሮሚያ ላይ ትርጉም በሌለው መልኩ ሀብትና ንብረቱን ጥሎ እስከሚወጣ ፣ የኦሮሞ ከተሞችን ከአማራ እስከሚያፀዱ ፣ አዲስአበባን የኦሮሞ ንብረት የማድረግ ሕልምን ለማሳካት እና ኦሮሞ የሚዘውራትን አገር እውን ለማድረግ አማራን ቋሚ ተሸናፊ ለማድረግ የሚያስችሉ ቋሚ ቀውሶች እና ጥቃቶች ገና ይቀጥላሉ !!
▸ ትግራይን ቀጥቅጠን ወያኔ የፈለግነውን ስምምነት እንዲፈፅም፣ የምንለውን እሺ ብሎ የሚቀበል ፣ የሾምንለትን አሜን የሚል እንዳደረግነው ፤ አማራም አሜን ብሎ እንዲገዛ በሚያደርግ መልኩ እንደቁሰዋለን ብለው ተነስተዋል። ወያኔ 27 ዓመት በገዛበት አገር ፣ አማራው የኦሮሞን በ5 አመት የስልጣን ተቀናቃኝ በመሆኑ መስበር አለብን ብሎ ተነስቷል።
▸ ወያኔን ከአማራና ኤርትራ ጋር ሆነን እንደሰበርነው ፣ አማራን ከትግራይና ከሱዳን ጋር ሆነን እንሰብረዋለን የሚል ስሌት ይዞ ፡ ነገሮችን እያስተባበረ ይገኛል።
▸ የአማራን ወታደራዊ አቅሞች ሁሉ አሟጦ የማጥፋት ጥረት ልዩ ኃይልን በመቀተን ፣ ፋኖን በማጥፋት ፣ መሣሪያ በመንጠቅ አያበቃም። በጦርነቱ ሰበብ በከፍተኛ መጠን ወደመከላከያ የገባውን አማራ በፅንፈኛነት ፣ ከብዛት ይልቅ ጥራት በሚሉ ሰበቦች ፣ በጡረታ እና በልዩ ልዩ ሰበቦች ጠርጎ ያስወጣዋል። ለኦሮሙማ ፍላጎት ያደረ ታዛዥ ከመሆን ያለፈ ሚና አይሰጥም።
▸ በአገሪቱ ብቻ ሳይሆን በቀጠናውም ከአማራው ጎን የሚቆሙ አካላት እንዳይኖሩ ለማድረግ ሁሉንም ክልል ስጋትና ፍርሃት ውስጥ መክተት ላይ እየተሠራ ነው። ከአማራው ጋር አብረው የሚቆሙ እንዳይኖሩ ብቻ ሳይሆን አማራውም በራሱ አብሮ እንዳይቆም ለማድረግ የሚያስችሉ ከፋፎሎ የመቆጣጠር (Divide and conquer) ፣ ከፋፍሎ የመግዛት (devide and rule) እና መርጦ የማስተናገድ (selective accomodation) ስልቶችን በመከተል መከፋፈል ላይ በስፋት ተሠማርተዋል።
▸ በቀጣይ የሚመጣውን የቤትና ሕዝብና ቤት ቆጠራ የእነሱን ታላቅነት የአማራን ትንሽነት አረጋግጦ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የሚያስችለው ሥራ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ መሥሪያቤትን የያዘው የበከር ሻሌ ቡድን እጅግ ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ ነው። በኦሮሚያ ያለ አማራ ፡ ማንነቱን ክዶ በእነሱ ማንነት የመቆጠር አሊያም የመባረር አማራጭ ይደርሰዋል። እነሱን ነኝ ብሎ ባይቆጠርም ስሌቱ ከወዲሁ እያለቀ ነው። እነሱን ነኝ ማለትም በቀጣይ ምዕራፍ ዘሩ ተቆጥሮ ከመባረር አይድንም። ቋንቋ መናገር እንኳ እንደማያስጥል በተደጋጋሚ ታይቷል።
▸ የአማራ ባለሀብቶች በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ገንዘብ እንዲያወጡ ማድረግ ፣ የኦሮሞ ባለሀብቶችን ግን ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማ በመስጠት ኢኮኖሚውን እንዲቆጣጠሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ለእነሱ አመቺ የሕግና የአሠራር ማሻሻያ ማድረግ፣ እንደኮንስትራክሽን ያሉ ዘርፎችን እንዲቆጣጠሩ ማስቻል ፣ የአገሪቱን ግዢዎች ወይ ከኦሮሞዎች ወይ በኦሮሞዎች እንዲፈፀሙ ማስቻል የመሠሉ ሥራዎች እየተሠሩ ነው።
▸ በዚህ ሒደት ውስጥ በሚድያ የሚተቹትን ፣ የሚያጋልጡትን እና ሕዝቡን የሚቀሰቅሱትን አክቲቪስቶች ፣ የሚድያ ሙያተኞች ፣ ፖለቲካዊ አስተያየት ሰጪዎች ሁሉ እያደኑና እያዋረዱ ማገት እና ማሠር የማስፈፀሚያ ስልት ተደርጓል። ከአማራው ወግኖ የሚናገር የሌላ ብሔር ተወላጅ ደግሞ አፉን እንዲዘጋ የሚያደርግ እርምጃ እንዲወሰድበት በተወሰነው መሠረት ሲደበደቡና ሲታፈኑ ቆይተዋል፣ ይቀጥላል። ይሔንን አላማ ለማሳካት ደግሞ ልክ እንደ ኢ-መደበኛ ታጣቂው ፣ በኢ-መደበኛነት የሚያፍን፣ የሚደበድብ እና የሚዘርፍ ቡድን ተደራጅቷል።
▸ በፌደራል እና የአዲስአበባ ተቋማት ያለውን አማራ መቀነስና ማባረር፣ ቀኑን የሚጠብቅ የማይቀር አላማ ነው። አዲስአበባን አላስፈላጊ ማድረግ የሚለውም በኑሮ ውድነት ጠብሶ ማስወጣትን ጨምሮ፣ ድሆች የሚሠማሩባቸውን የንግድ ሥራዎች ከማወሳሰብና ከማገድ ጋር ተያይዞ የሚቀጥል ነው። በአድር-ባይነት የወገኑን ጥቃት የካደ የአማራ ሲቪል ሠርቫንት፡ ወገኑን መካዱ አያስቀረውም።
▸ በኦሮሚያ ከተሞች እና ዞኖች የሚኖረው አማራ፣ እስከዚያው የሚፈፀምበት ጥቃትና ማሸማቀቅ እንዳለ ሆኖ፡ የአዲስአበባ ጉዳይ ሲጠናቀቅ የሚመለሱበት አጀንዳ ነው። በአዲስአበባ ዙሪያ እንዳደረጉት፣ "ፌስታልህን ይዘህ እንደመጣህ፡ ከእነፌስታልህ ባዶ እጅህን ነፍስህን ይዘህ ከተመለስክ ይበቃሃል" ተብሎ ፣ ያፈራው ሀብትና ንብረት የሚወረስበት ወይም የሚገደልበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። የኦሮሙማ ፕሮጀክት ያስገድዳልና ።
▸ በወገናቸው ላይ ሊመጣ የሚችልን አደጋ ለመተንበይና ለመከላከል ይቅርና እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት እና ጥፋት ለመቀነስም ለማስቀረትም ያልፈቀዱ እና የማይችሉ፣ ይልቁንም የቀደሙትን ሁሉ በሚያስመሰግን ግፍ እና ክሕደት ወገናቸውን በማጥቃት ላይ የተሠማሩ አድር-ባይ የአማራ ወኪል አመራሮች እንደትናንትናዎቹ የለውጥ አወዳሽ ተባራሪዎች፣ አሁን ያሉትም ቀንበሩ እንደከበዳቸው ምልክት ያሳዩ ቀን በሌሎች መሠል አድርባዮች ይተካሉ። በሕዝባቸው ውርደት ለማጌጥ የተሰለፉ እና አማራን የሚያሳድዱ ሁሉ እንደአገዳ ተላምጠው የሚሸኙበት ቀን ይመጣል።
▸ እነዚህ ሁሉ ሒደቶች ፡ ጠላት ድልን ከተጎናፀፈ አማራ የሚባለውን ግዛት እንኳ ጠብቆ መቀጠል ወደማይችልበት መቀመቅ ማውረድ የጠላት አላማ ነው።
አልደበቁንም!!
አማራ የሚባል ሕዝብም ክልልም የለም ብለዋል!!
የዛሬ 500 ዓመት የረገጥነውን ሁሉ በዚህ ዘመን እንጠቀልላለን ብለዋል።
የአማራ አማራጮቹ ሁለት ብቻ ናቸው!!
1) በቋሚ ተሸናፊነት ጠላት የሚወስንልህን እየተቀበሉ የባርነትና ተንበርካኪነት ኑሮ መኖር፤
2) አማራዊ ሕልውናን ለመታደግ በሚያስችል ሁሉንአቀፍ ትግል ተሠማርቶ ታሪኩን እና ማንነቱን የሚመጥን ልዕልናውን ማረጋገጥ!!
ድል ለአማራ !
#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
563 views14:30