Get Mystery Box with random crypto!

Tona Media | ቶና ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ psychaddis — Tona Media | ቶና ሚዲያ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ psychaddis — Tona Media | ቶና ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @psychaddis
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.60K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ገጽ የሥነ-ልቦና ሳይንስን ለሕይወታችን እንዲመች አድርገን እንድንጠቀም የሚያስችል መረጃ የምናገኝበት ነው:: ሰብስክራይብ በማድረግ አባል ይሁኑ!

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 15:59:13 ተጠቀሙበት!


476 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:15:38
ዓለም..... ደስታችን፣ ኀዘናችን፣ ወረታችን፣ ብርቃችን፣ ህልማችን እና ቅዠታችን በሚወሰንባት፣ በታጨቀባት... በእጅ ስልካችን ትጠፋለች። ልጆችም በወላጆቻቸው ቅጥ ያጣ ደግነት ይጠፋሉ። ብዙዎች በቀቢጸ ተስፋ በመቅበዝበዝ ሲያልፉ፣ በጣም ጥቂቶች በእግዚአብሔር እርዳታ በቀናው መንገድ ይውላሉ። ትንቢት አይደለም። ሟርትም አይደለም። ካየሁት ከተረዳሁት ነው።

ልጆችን ከወደድን፣ በጋውን ብቻ ሳይሆን ክረምቱንም በቤታችን ውስጥ እናሳያቸው። "እሺ" ከማለት ጎን ለጎን፣ መከልከልንም ይሰልጥኑ። አፈር አይንካችሁ ከመባል ጎን ለጎን፣ ትህትናን እና ጨዋነትን፣ የሌላውን ሰው ልጅ መውደድና ማክበርንም ይልመዱ። ሲያድጉ ያጡትን ነገር በሙሉ እንደ ጠቃሚ ነገር ቆጥሮ፣ ለልጅ ማሟላት ብቻውን መልካም ወላጅ አያስብልም። ያጣነው የማይጠቅመን ብዙ ነገር ነበረ። ለልጆቻችን የምናሟላው ብዙ መጥፎ ነገርም አለ።
"ልጄ ታብሌቱን ካገኘ ጥግ ነው።" "ስልክ ከያዘ አይነሳም።" "ላፕቶፑን ይዞ ክፍሉ ከገባ፣ በቃ ትኩረቱ እሱ ላይ ነው።" የምንልላቸው ልጆች ከስክሪኖቹ ጀርባ ምን ዓይነት ዓለም ውስጥ እንዳሉ ካላወቅን፣ እንደው ምናልባት ምናልባት ሰይጣኖቻችንን ይኾናል እየቀለብን ያለነው።

ለልጆቻችን የምናሟላላቸው ቁሳቁስ ስለሚያስፈልጋቸው ነው? ስለጠየቁ ነው? ሰው ስላደረገ ነው? ትናንታችንን ለመበቀል ነው? እንዳይረብሹ ሰላም ለማግኘት ነው?

እኔ ባልወለደ አንጀቴ፣ ባየሁት መጠን ይኽን ብያለሁ። የወለዳችሁ ጨምሩበት። አጠፋህ ልክ አይደለህምም በሉኝ።
(Yohannes Molla)
___
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑና ጠቃሚ ትምህርቶችን ያግኙ!
ዩቲዩብ፡


ቴሌግራም፡ https://t.me/psychaddis
611 views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:24:20 ህፃናት ለምን ሀይለኛ ይሆናሉ?
=================
(በዶ/ር ዮናስ ላቀው)
አቡቲ 3 አመቱ ነው። እናቱ እንግዶች እያስተናገደች እሱ ኳስ ይጫወታል። ምሳ ካቀረበች በኃላ "ኳስ በቃ!" ብላ ኳሱን ወሰደችበት። እሪ ብሎ አለቀሰ ከዛም እናቱን መምታት ጀመረ። ስትይዘው ራሱን ከሷ ጋር ያጋጫል። ከእንግዶቹ አንዱ "ስጪው ይጫወት" ሲል በእድሜ ከፍ ያሉት "ፊት አትስጪው አልቅሶ ሲበቃው ዝም ይላል።" አሉ። ......
አብዛኞቹ ህፃናት ከ2-5 አመታቸው ላይ አልፎአልፎ ሀይለኝነት ሊያሳዩ ይችላሉ። የሚፈልጉትን ነገር ሲከለከሉ፣ በቂ ትኩረት ሳይሰጣቸው ሲቀር መሻታቸውን ለመግለፅ ቃላት ገና አላዳበሩም። በተጨማሪም ንዴትን መቆጣጠር እና በተገቢው መንገድ መግለፅ ስለሚያቅታቸው አልፎአልፎ ሀይለኛ ሊሆኑ ይችላሉ። የሶስት አመት ልጅ ተረጋግቶ "በኳስ እየተዝናናሁ ያለሁበት ሁኔታ ነው ያለው። የመጡትን እንግዶች አላውቃቸውም። ስለዚህ መጫወቴን ለምን ማቆም እንዳለብኝ አልገባኝም።" ሊል አይችልም።
ልጆች ሀይለኛ እንዳይሆኑና ከሆኑም ወላጆች ማድረግ የሚገባቸው ነጥቦች፦
1) መረጋጋት:
ወላጆች ተረጋግተው ለልጆቻቸው ምላሽ ሲሰጡ ለልጆቻቸው ንዴትን መቆጣጠርን በተግባር ያሳዩአቸዋል። ከዛ ልጆች ፍላጎታቸውን እንዲናገሩ ማድረግ። ቃላት ካነሳቸው ማገዝ ቋንቋቸውን ስለሚያሳድግ በቀጣይ የሚፈልጉትን በንግግር መጠየቅ እንዲችሉ ያስችላቸዋል።
2) ትኩረት መስጠት:
ለሚናገሩትና ለሚያደርጉት ነገር ትኩረት የሚሰጣቸው ልጆች የሚፈልጉትን በሀይለኝነት መግለፅ አያስፈልጋቸውም።
3) ፕሮግራሞችን ማሳወቅ:
ነገሮችን ድንገት መከልከል ንዴት ይፈጥራል። ፕሮግራሞችን ማሳወቅ ግን የሚካሄደውን እንዲረዱና ምክኒያታዊ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። "ምሳ እስኪቀርብ መጫወት ትችላለህ።" ከዛ የተወሰነ ቆይቶ "ምሳ ሊቀርብ ስለሆነ ትንሽ የመጫወቻ ጊዜ ነው የቀረህ።"....
4) ምርጫ መስጠት:
ልጆች እነሱን የሚመለከት ጉዳይ ላይ አማራጮች ሲሰጣቸው ሀላፊነት ይሰማቸዋል። በመጨረሻም የሚከለከሉት ነገሮች ላይ ምክኒያቱን መንገር ናቸው።
መልካም ጊዜ!
---
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑና ጠቃሚ ትምህርቶችን ያግኙ!
ዩቲዩብ፡


ቴሌግራም፡ https://t.me/psychaddis
1.0K views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:27:17 ሕይወትን እንደ ንሥር አሞራ ኑር!
====================

ንስር አሞራ ፀሐይን ቀጥ ብሎ ማየት የሚችል ወደ ፀሐይ አቅጣጫ ጨረሩን እያየ መብረር የሚችል ብቸኛው ፍጡር ነው። ሌሎች ቁራዎችና ጭልፊቶች 100 ወይም 200 ሆነው ከበው ሲጮሁበት ወደ ፀሐይ እያየ ከፍ ብሎ ይበራል። ሌሎቹ ፍጥረቶች ወደ ፀሐይ እያዩ መብረር ስለማይችሉ ይጠፋባቸዋል!!

- ንስር ከሰው አይን 8 እጥፍ የተሻለ ማየት ይችላል፣
- ንስር ከ 2.30-3 ሜ ይረዝማል፣
- ንስር ከ5-7 ኪሎሜትር ያለን ለማደን የሚፈልገውን ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ይችላል፣
- ንስር ለአደን እስከ 120 ኪሎሜትር አካሎ ይበራል፣
- ንስር መጠለያ ከሌለበት አካባቢ ሆኖ ኃይለኛ ዝናብ ቢመጣ ወደላይ በመምጠቅ ከደመና በላይ በሮ ዝናብና ወጀቡን ከስር ያደርጋል እንጂ በዝናብ አይቀጠቀጥም፣
- ንስር አድኖ እንጂ ጭራሽ የሞተ አይበላም፣
- ንስር ሲታመም ፀሐይን አተኩሮ በማየት ነው ህክምና የሚያገኘው፣
- ንስር 340° ማየት ይችላል። ከ360° በአንድ እይታ 340° ማየት ይችላል። ሰው 180° አካባቢ ነው ማየት የሚችለው፣
- ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ። ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል።

የመጀመሪያው ፤
ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል፣

ሁለተኛው ፤
አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ (መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል፣

ሶስተኛው፤
ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።

እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?

2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?
የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።

ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።

፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።

፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።

፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡

፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።

፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡

ወዳጄ ሆይ:

ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ...ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡ... አትበል ፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን የተሻለ ነገር ለመስራት ጣርና ሕይወትህን ቀይር!

ዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!


Se
1.1K views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:27:15
988 views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 15:50:53
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑና ጠቃሚ ትምህርቶችን ያግኙ!
ዩቲዩብ፡


ቴሌግራም፡ https://t.me/psychaddis
1.2K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 15:02:51 https://youtube.com/shorts/d-Bg9fEbOMM?feature=share
1.7K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 06:44:58
ጥቁር ነጥብ፤
========

የአንድ ትንሽ ከተማ የንግድ ምክር ቤት ዓመታዊ የእራት ግብዣ ላይ አንዲትን አነቃቂ ተናጋሪ ጋበዘ። ምክንያቱም የማህበረቡ ኢኮኖሚ አሽቆልቁሎ፣ ሰዎቹም ተስፋ ቆርጠው ነበርና እንዲበረታቱና እንዲነቃቁ ለማስቻል ነበር።

ተናጋሪዋም ንግግሯን ስትጀምር በአንድ ትልቅ ነጭ ወረቀት መሀል ላይ ትንሽ ጥቁር ነጥብ በመሳል ነበር። ከዚያም በተሰበሰቡት ሰዎች ፊት ለፊት ከፍ አድርጋ በመያዝ ምን እንደታያቸው መጠየቅ ጀመረች።

አንዱ ሰው ፈጠን ብሎ "ጥቁር ነጥብ" አለ።

"እሺ ሌላስ" አለች ተናጋሪዋ።

ሁሉም በአንድ ላይ : "ጥቁር ነጥብ" አሉ።

"ከጥቁሩ ነጥብ ሌላ ምንም ነገር አልታያችሁም?" ብላ ደግማ ጠየቀቻቸው።

ተሰብሳቢዎቹም በአንድ ድምጽ : "ምንም" በማለት መለሱ።

"ትልቁ ነጭ ወረቀትስ?" በማለት ጠየቀች ተናጋሪዋ። "እርግጠኛ ነኝ ሁላችሁም አይታችሁታል" አለች። "ነገር ግን እሱን ትታችሁ ላዩ ላይ ያለውን ነገር ማየትን መረጣችሁ።"

"በሕይወታችንም ያሉንን እና በአካባቢያችን የሚከሰቱ አስገራሚ ነገሮችን በመተው ጥቃቅንና ነጥብ የሚመስሉ እንዲሁም የማይረቡ ነገሮች ላይ በማተኮር ጊዚያችንን እናባክናለን። 'ችግሮች' ብለን የምንጠራቸው ነገሮች በአብዛኛው ልክ ነጩ ወረቀት ላይ እንዳለው ጥቁር ነጥብ ናቸው። እይታችንን ካሰፋን እና ሙሉ ሥዕሉን ማየት ከቻልን ትናንሽና የማይረቡ ሆነው እናገኛቸዋለን።" በማለት ንግግሯን አጠቃለለች።

እርስዎስ ጉልበትዎንና ትኩረትዎን ነጥብ መሰል ችግሮች ላይ ከሚያደርጉ ሰዎች ተርታ የሚሰለፉ ነዎት? ወይስ ትልቁን ወረቀት በማየት ችግሮችን አሳንሰው አሸናፊ የሚሆኑ ነዎት?

ሳይክ አዲስ
1.8K views03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:28:38 https://youtube.com/shorts/UFWtdIZFq7E?feature=share
1.4K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:27:55 "ከናዚ የማጎሪያ ካምፕ የተረፍኩ ነኝ። ማንም ታዛቢ ያልነበረበትን ትዕይንት ዓይኖቼ አይተዋል፤ የመርዝ ጋዝ ማስተላለፊያዎች በተማሩ ኢንጅነሮች ሲገነቡ፣ ልጆች ብቃት ባላቸው ሐኪሞች ሲመረዙና ጨቅላ ሕፃናት በሰለጠኑ ነርሶች ሲገደሉ። ስለሆነም ትምህርትን እጠራጠራለሁ። "

"የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር፤ ልጆቻችሁን ከምንም በላይ 'ሰው' እንዲሆኑ አግዟቸው። ልፋታችሁ የተማሩ አረመኔዎችን ወይም የተማሩ ጭራቆችን ለማፍራት መሆን የለበትም። ማንበብ፣ መጻፍና ሒሳብ ማስላት ጠቃሚ የሚሆኑት ልጆቻችንን ይበልጥ 'ሰው' እንዲሆኑ ከረዷቸው ብቻ ነው።"

-ዶ/ር ሐይም ጂኖ
የሕጻናት ሳይኮሎጂስትና ከናዚ እልቂት የተረፈ
1.4K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ