Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም..... ደስታችን፣ ኀዘናችን፣ ወረታችን፣ ብርቃችን፣ ህልማችን እና ቅዠታችን በሚወሰንባት፣ በ | Tona Media | ቶና ሚዲያ

ዓለም..... ደስታችን፣ ኀዘናችን፣ ወረታችን፣ ብርቃችን፣ ህልማችን እና ቅዠታችን በሚወሰንባት፣ በታጨቀባት... በእጅ ስልካችን ትጠፋለች። ልጆችም በወላጆቻቸው ቅጥ ያጣ ደግነት ይጠፋሉ። ብዙዎች በቀቢጸ ተስፋ በመቅበዝበዝ ሲያልፉ፣ በጣም ጥቂቶች በእግዚአብሔር እርዳታ በቀናው መንገድ ይውላሉ። ትንቢት አይደለም። ሟርትም አይደለም። ካየሁት ከተረዳሁት ነው።

ልጆችን ከወደድን፣ በጋውን ብቻ ሳይሆን ክረምቱንም በቤታችን ውስጥ እናሳያቸው። "እሺ" ከማለት ጎን ለጎን፣ መከልከልንም ይሰልጥኑ። አፈር አይንካችሁ ከመባል ጎን ለጎን፣ ትህትናን እና ጨዋነትን፣ የሌላውን ሰው ልጅ መውደድና ማክበርንም ይልመዱ። ሲያድጉ ያጡትን ነገር በሙሉ እንደ ጠቃሚ ነገር ቆጥሮ፣ ለልጅ ማሟላት ብቻውን መልካም ወላጅ አያስብልም። ያጣነው የማይጠቅመን ብዙ ነገር ነበረ። ለልጆቻችን የምናሟላው ብዙ መጥፎ ነገርም አለ።
"ልጄ ታብሌቱን ካገኘ ጥግ ነው።" "ስልክ ከያዘ አይነሳም።" "ላፕቶፑን ይዞ ክፍሉ ከገባ፣ በቃ ትኩረቱ እሱ ላይ ነው።" የምንልላቸው ልጆች ከስክሪኖቹ ጀርባ ምን ዓይነት ዓለም ውስጥ እንዳሉ ካላወቅን፣ እንደው ምናልባት ምናልባት ሰይጣኖቻችንን ይኾናል እየቀለብን ያለነው።

ለልጆቻችን የምናሟላላቸው ቁሳቁስ ስለሚያስፈልጋቸው ነው? ስለጠየቁ ነው? ሰው ስላደረገ ነው? ትናንታችንን ለመበቀል ነው? እንዳይረብሹ ሰላም ለማግኘት ነው?

እኔ ባልወለደ አንጀቴ፣ ባየሁት መጠን ይኽን ብያለሁ። የወለዳችሁ ጨምሩበት። አጠፋህ ልክ አይደለህምም በሉኝ።
(Yohannes Molla)
___
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑና ጠቃሚ ትምህርቶችን ያግኙ!
ዩቲዩብ፡


ቴሌግራም፡ https://t.me/psychaddis