Get Mystery Box with random crypto!

ህፃናት ለምን ሀይለኛ ይሆናሉ? ================= (በዶ/ር ዮናስ ላቀው) አቡቲ 3 አመቱ | Tona Media | ቶና ሚዲያ

ህፃናት ለምን ሀይለኛ ይሆናሉ?
=================
(በዶ/ር ዮናስ ላቀው)
አቡቲ 3 አመቱ ነው። እናቱ እንግዶች እያስተናገደች እሱ ኳስ ይጫወታል። ምሳ ካቀረበች በኃላ "ኳስ በቃ!" ብላ ኳሱን ወሰደችበት። እሪ ብሎ አለቀሰ ከዛም እናቱን መምታት ጀመረ። ስትይዘው ራሱን ከሷ ጋር ያጋጫል። ከእንግዶቹ አንዱ "ስጪው ይጫወት" ሲል በእድሜ ከፍ ያሉት "ፊት አትስጪው አልቅሶ ሲበቃው ዝም ይላል።" አሉ። ......
አብዛኞቹ ህፃናት ከ2-5 አመታቸው ላይ አልፎአልፎ ሀይለኝነት ሊያሳዩ ይችላሉ። የሚፈልጉትን ነገር ሲከለከሉ፣ በቂ ትኩረት ሳይሰጣቸው ሲቀር መሻታቸውን ለመግለፅ ቃላት ገና አላዳበሩም። በተጨማሪም ንዴትን መቆጣጠር እና በተገቢው መንገድ መግለፅ ስለሚያቅታቸው አልፎአልፎ ሀይለኛ ሊሆኑ ይችላሉ። የሶስት አመት ልጅ ተረጋግቶ "በኳስ እየተዝናናሁ ያለሁበት ሁኔታ ነው ያለው። የመጡትን እንግዶች አላውቃቸውም። ስለዚህ መጫወቴን ለምን ማቆም እንዳለብኝ አልገባኝም።" ሊል አይችልም።
ልጆች ሀይለኛ እንዳይሆኑና ከሆኑም ወላጆች ማድረግ የሚገባቸው ነጥቦች፦
1) መረጋጋት:
ወላጆች ተረጋግተው ለልጆቻቸው ምላሽ ሲሰጡ ለልጆቻቸው ንዴትን መቆጣጠርን በተግባር ያሳዩአቸዋል። ከዛ ልጆች ፍላጎታቸውን እንዲናገሩ ማድረግ። ቃላት ካነሳቸው ማገዝ ቋንቋቸውን ስለሚያሳድግ በቀጣይ የሚፈልጉትን በንግግር መጠየቅ እንዲችሉ ያስችላቸዋል።
2) ትኩረት መስጠት:
ለሚናገሩትና ለሚያደርጉት ነገር ትኩረት የሚሰጣቸው ልጆች የሚፈልጉትን በሀይለኝነት መግለፅ አያስፈልጋቸውም።
3) ፕሮግራሞችን ማሳወቅ:
ነገሮችን ድንገት መከልከል ንዴት ይፈጥራል። ፕሮግራሞችን ማሳወቅ ግን የሚካሄደውን እንዲረዱና ምክኒያታዊ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። "ምሳ እስኪቀርብ መጫወት ትችላለህ።" ከዛ የተወሰነ ቆይቶ "ምሳ ሊቀርብ ስለሆነ ትንሽ የመጫወቻ ጊዜ ነው የቀረህ።"....
4) ምርጫ መስጠት:
ልጆች እነሱን የሚመለከት ጉዳይ ላይ አማራጮች ሲሰጣቸው ሀላፊነት ይሰማቸዋል። በመጨረሻም የሚከለከሉት ነገሮች ላይ ምክኒያቱን መንገር ናቸው።
መልካም ጊዜ!
---
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑና ጠቃሚ ትምህርቶችን ያግኙ!
ዩቲዩብ፡


ቴሌግራም፡ https://t.me/psychaddis