Get Mystery Box with random crypto!

'ከናዚ የማጎሪያ ካምፕ የተረፍኩ ነኝ። ማንም ታዛቢ ያልነበረበትን ትዕይንት ዓይኖቼ አይተዋል፤ የመ | Tona Media | ቶና ሚዲያ

"ከናዚ የማጎሪያ ካምፕ የተረፍኩ ነኝ። ማንም ታዛቢ ያልነበረበትን ትዕይንት ዓይኖቼ አይተዋል፤ የመርዝ ጋዝ ማስተላለፊያዎች በተማሩ ኢንጅነሮች ሲገነቡ፣ ልጆች ብቃት ባላቸው ሐኪሞች ሲመረዙና ጨቅላ ሕፃናት በሰለጠኑ ነርሶች ሲገደሉ። ስለሆነም ትምህርትን እጠራጠራለሁ። "

"የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር፤ ልጆቻችሁን ከምንም በላይ 'ሰው' እንዲሆኑ አግዟቸው። ልፋታችሁ የተማሩ አረመኔዎችን ወይም የተማሩ ጭራቆችን ለማፍራት መሆን የለበትም። ማንበብ፣ መጻፍና ሒሳብ ማስላት ጠቃሚ የሚሆኑት ልጆቻችንን ይበልጥ 'ሰው' እንዲሆኑ ከረዷቸው ብቻ ነው።"

-ዶ/ር ሐይም ጂኖ
የሕጻናት ሳይኮሎጂስትና ከናዚ እልቂት የተረፈ