Get Mystery Box with random crypto!

Muslim Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimstudentsgroup — Muslim Students M
የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimstudentsgroup — Muslim Students
የሰርጥ አድራሻ: @muslimstudentsgroup
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.82K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን በደና መጡ!....አስተማሪ ታሪኮች፣ ለትምህርት ጥንካሬ ሊያግዙ የሚችሉ አስተምህሮቶችና መልዕክቶች የሚለቀቁበት ነው።ሀሳብ ወይም አስታየት እንዲሁም እዚህ ቻናል ላይ ምርታቹን መስታወዋቅ ለምትፈልጉ @Remdan333

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-03-20 15:37:18
ረመዳን ነክ ጉዳዩች

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿من لم يدَعْ قولَ الزُّورِ والعملَ بِهِ، فليسَ للَّهِ حاجةٌ بأن يدَعَ طعامَهُ وشرابَهُ﴾

“የሐሰት ንግግርን በሐሰት መስራትን እንዲሁም መሀይምነትን (የመሐይማንን ተግባር) ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን ከመተዉ አላህ ጉዳይ የለውም፡፡”

ቲርሚዚ ዘግበውታል: 707
@Muslimstudentsgroup
293 views 𝙯𝚞𝚣𝚞 ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , edited  12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 15:35:06
#የሰላምታ_ትሩፋትና #ሰላምታን_ማብዛት_ስለመታዘዙ  
#ክፍል_1

አላህ እንዲህ ብሏል፦
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቿ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ ከቤታችሁ ሌላ የኾኑትን ቤቶች አትግቡ።” (አን ኑር፡ 27)

#ሐዲሥ 131 / 845

ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ አል ዓስ እንዳስተላለፉት አንድ ሰው የአላህን መልዕክተኛ፦ “ከኢስላም (በጎ ሥራዎች) ሁሉ መልካሙ የትኛው ነው?” ሲል ጠየቀ። “ምግብ ማብላትህና ለምታውቀውም ለማታውቀውም ሰላምታ ማቅረብህ ነው” በማለት መለሱለት፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ ምግብን ማብላት ይወደዳል። ፍቅር ይጨምራል፣ ግንኙነትን ያጠነክራል። የሰየውንም ቸርነት አመላካች ነው።
2/ ሰላምታን ማብዛት ሱንና ነው። ሰላም ማለት ሱንና ሲሆን፥ መመለስ ደግሞ ግዴታ ነው። ከተሰበሰቡ ሰዎች መሐል አንዱ ከመለሰ በሌሎች ላይ ግዴታውን ያነሳላቸዋል።
3/ ሰላምታ ማቅረብ ሰላምታ ከመመለስ የበለጠ ነው።
4/ ምግብ ከማብላት ጋር መወሳቱ ፍቅርን እንደሚያክልና ግንኙነቶችን እንደሚያጠናክር ለማሳየት ነው።
5/ “ደህና አደርክ”፣ “ደህና ነህ” የሚሉና መሰል የሰላምታ ቃላት “አስሰላሙ ዐለይኩም”  የሚለውን ቃል አይተኩም።
294 views 𝙯𝚞𝚣𝚞 ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 21:19:03 ልብ በሉ ለወንዶች ብቻ ነው ውድድሩ
ለመወዳደር በዚህ ያናግሩን
@mahiro_fkr
@Alhamdulilah25
128 viewsМαнι ×͜×, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 21:19:03
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ የረበና ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን ለአላህ ብለን እንወዳቹሀለን ውድ የተከበራቹ አንድነት ለዲናችን ተከታታዮቻችን አዲስ የምስራች ይዘን ወደ እናንተ መጥተና በአይነቱ ለየት ያለ ውድድር ታላቅ ኦላይን የቁርአን ውድድር የረመዳን መድረስ አስመልክተን የተዘጋጀ የኦላይን የቁርአን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌግራም ሊጀመር ዛሬ ማታ በእኛው የቴሌግራም ቻናል ማለትም እሁድ 10/7/2015 ጀምሮ አጓጊ የቁርአን ውድድሩ ህግና ደንቦች ይኖሩታል እሱም አንድ ተወዳዳሪ ማሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ ይኖሩታል። ቁርአኑን ለመወዳደር  የእድሜ ክልል አይገድበውም ።


@Quran_Challange ህጎች
➱ አንደኛ እናንተ የመረጣችሁትን የቁርአን አያ ይሆናል የምትቀሩት
➱ ሁለተኛ ውድድሩ ውጤት የሚያዘው 75 % ሀርፉን ጠብቆ ሳይሰባበር በጥራት ስህተት የሌለበት አቀራር መሆን አለበት ! የአቀራር ሂደታቹ በኡስታዞች ነው የሚዳኘው 25 % ደሞ የቀራችሁ ቁርአን ከተለቀቀ ቡሀላ Like መሰብሰብ አለባችሁ ልብ በሉ የራሳችሁ ነው መሆን ያለበት !
➱ ሶስተኛ ደሞ የቀራችሁትን ቁርአን ከስር በምናስቀምጠው username ብቻ ነው የምልኩልንን

ይህ ወድድር የሚጀምረው ከዛሬ ቀን ጀምሮ ነው፡፡ እህቶቻንም ወንድሞቻቹን በመጋባዝ እንዲሸለሙ ያድርጉ። እኛስ ላላቹ እህቶች፦

ለሴት እህቶቻችንም ለየት ያለ ውድድር አዘጋጅተናል እሱንም ከረመዳን በኋላ የምናሰውቅ ይሆናል።
▬▬▬▬▬▬▬◆◆▬▬▬▬▬▬▬
አዘጋጅ፦ አንድታችን ለዲናችን የቴሌግራም ቻናል
አጋራችን፦ ፉርቃን Online የቁርአን መድረሳ
ኢቅራዕ Online የቁርአን መድረሳ
▬▬▬▬▬▬▬◆◆▬▬▬▬▬▬▬
       ᴊᴏɪɴ & Sʜᴀʀᴇ
@andnetachn_ledinachn
@andnetachn_ledinachn
127 viewsМαнι ×͜×, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 17:58:38 የቁርዓን ውድድሩን ለመመዝገብ እንዲሁም ስፖንሰር መሆን ምትፈልጉ አካላቶች ከስር ባለው አካውንት አናግሩን


@mahiro_fkr
@Alhamdulilah25
374 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 17:05:41 ለአሏህ ብለን ሼር እናረገው ለምን አትሰግድም ወንድሜ?
ለምን አትሰግጂም እህቴ? በዱንያ_ላይ፦
1• እስካልሰግድክ ድረስ ከእድሜህ ላይ በረካ ይነሳል ...
2• እስካልሰገድክ ድረሰ ከፊትህ ላይ ኑር
ይገፈፋል...
3• እስካልሰገድክ ድረስ ምትሰራው ስራ ሁሉ ተቀባይነት የለውም.
4• እስካልሰገድክ ድረስ ዱዓህ ተሰሚነት አያገኝም.
5• እሰካልሰገድክ ድረስ ሌሎች ሚያደርጉልህ ዱዓም አይጠቅምህም. ስትሞት፦
1• እስካለሰገድክ ድረስ እማትረባና የተዋረድክ ሆነህ ትሞታለህ.
2• እስካልሰገድክ ድረስ እንደተራብክ ትሞታለህ.
3• እሰካለሰገድክ ድረስ እንደተጠማህ ትሞታለህ. የባህርን ውሃ እንዳለ ብትጠጣ ጥምህን
አይቆትጥልህም. ቀብር_ውስጥ፦
1• እስካለሰገድክ ድረስ ጎንና ጎንህ እስኪተላልፈ ድረስ ቀብርህን አሏህ ያጠብብሃል.
2• እስካለሰገድክ ድረስ ቀብርህ ውስጥ እሳት ተቀጣጥሎብህ ነጋ ጠባ ትሰቃያለህ.
3• እስካለሰገድክ ድረስ በቀን አምስት ጊዜ ከእባብ ጋር ቀጠሮ ይኖርሃል ! የፈጅርን ሰላት ባለመስገድህ ሲያሰቃይህ ዙሁር ይደረሳል፤የዙሁርን ሰላት ባለመሰገድህ ሲያሰቃይህ አስር ይደርሳል ፤እንደዚህ እያለ ስቃይህ ይቀጥላል (አንድ ጊዜ ምትመታው እሰከ 70 ክንደ ያህለ መሬት ውስጥ ያሰምጠሃል).. የቂያማለት፦
1• እስካለሰገድክ ድረስ ወደ ጀሃነም እሳት . በፊትህ እየተጎተትክ ትወሰዳለህ .
2• እሰካልሰገድክ ድረስ አሏህ ፊት ቆመህ ስትተሳሰብ አሏህ (ሱ,ወ)
በቁጣ አይን ይመለከትህና ፊትህ ላይ ያለ ስጋ ይነሳለ.
3• እስካልሰገድክ ድረስ ከአሏህ (ሱ.ወ) ጋር የምትተሳሰበው ሂሳብ የከፋ ይሆነንና ወደ ጀሃነም እሳት እንደትወረወር ይደረጋል . ወንድሜ አሁንም አትሰግድም ?? እህቴ አሁንም አትሰግጂም ?? ያአሏህ ይህንን ፁሁፍ ላዘጋጀውም
ላነበብነውም ወንጀላችንን ማረን… በሂወት ያሉና የሌሉትንም ወንድምና እህቶቻችንንም ወንጀል ማርልን!!!
ለአሏህ ብለን #ሼር እናረገው አናውቅም በዚህች ሰበብ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሂዳያ ያገኙና እኛም በጭንቁ የቂያማ ቀን ይጠቅመን ይሆናል፡፡
ቢያንስ #ለ15 ሰው ሼር
776 views 𝙯𝚞𝚣𝚞 ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 17:04:32 ዐብዱላህ ብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦

‏إنَّ من أَكْبَرِ الذنب أن يقول الرجل لأخيه : اتّق الله فيقول : عليك نفسك أنت تَأْمُرُني

"ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ አንድ ሰው ወንድሙን 'አላህን ፍራ!' ሲለው 'በራስህ ጉዳይ ተጠመድ። አንተ ልታዘኝ ነው?' ማለቱ ነው።"
[አልከቢር፣ ጦበራኒይ፡ 8587
@Muslimstudentsgroup
356 views 𝙯𝚞𝚣𝚞 ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 17:03:43
#ሕልምና_ከርሱ #ጋር #የተያያዙ_ነገሮች     
#ክፍል_6

#ሐዲሥ 130 / 844

አቡል አስቀዕ ዋሢለት ኢብኑ አል አስቀዕ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ “ከትልልቅ ቅጥፈቶች ውስጥ አንድ ሰው አባቱ ያልሆነውን አባቴ ነው ማለቱ፣ ወይም ዓይኖቹን ያላዩትን ሕልም ማሳየቱ ወይም በአላህ መልዕክተኛ ላይ ያላሉትን ማለቱ ነው።” (ቡኻሪ)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ አባቱ ያልሆነውን አባቴ ነው በማለት ወደርሱ መጠጋት ትልቅ ጥፋት ነው። የዘር መቀላቀልን ይፈጥራል።
2/ በሕልም መዋሸት፣ ያላዩትን አየሁ ማለት ትልቅ ጥፋት ነው። ምክንያቱም በአላህ ላይ መዋሸት ነውና። በእውን መዋሸት በፍጡራን ላይ መዋሸት ነው። እርሱም ቢሆን ትልቅ ወንጀል ቢሆንም በአላህ ላይ መዋሸት ግን ይበልጥ አስከፊ ነው።
3/ በነቢዩ ላይ መዋሸትና እርሳቸው ያላሉትን እንዳሉ አድርጎ ማቅረብም ትልቅ ጥፋት ነው። ምክንያቱም ሰዎችን ወደ ማሳሳት እና ወደ ማጠመም ይመራልና። ወደ ሸሪዓው የርሱ አካል ያልሆነን ነገር ማስጠጋት ነውና።
379 views 𝙯𝚞𝚣𝚞 ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 22:04:26
ወደ አላህ ከዞርክ
ካንተ ጋር እንደሆነ እወቅ
 ۚ أَلَيْسَ الصُّبْحُ بِقَرِيبٍ
ንጋቱ ቅርብ አይደለምን»


@Muslimstudentsgroup
313 views 𝙯𝚞𝚣𝚞 ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , edited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 22:04:25
የዱንያ ውበት ከአሏህ ጋር ባለው ግንኙነት ውበት ነው !! ውብ ሕይወት ከፈለግክ አንተ እንደፈለግከው ሳይሆን አሏህ እንደሚፈልገው አሳልፈው !!
በመታዘዝ ታገስ ፤
በተከለከሉ ነገሮች ታገስ ፤
በሚያሠቃዩ ዕጣ ፈንታ ታገስ ።

በጀነት ውስጥ ይህን ለመስማት ፡-
سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ

«ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡
【አር_ረዕድ ②④】
@Muslimstudentsgroup
320 views 𝙯𝚞𝚣𝚞 ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , edited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ