Get Mystery Box with random crypto!

ሙሌ SPORT

የሰርጥ አድራሻ: @mulesport
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 328.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሙሌ ስፖርት ስፖርታዊ መረጃዎችን ከእሁድ እስከ እሁድ ያገኙበታል
የሃገር ቤት መረጃ
የአውሮፓ ሊግ መረጃ
ቀጥታ ስርጭት
የዝውውር ዜና
ለማስታወቂያ ስራ @Mulesporta
@Teme_Ayu

ስልክ ቁጥር 251911857852

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-04-08 22:20:06 "አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጡ ቡድን ነው"

የባየር ሙኒኩ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ነገ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ መርሀ ግብር ከአርሰናል ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት በጋዜጣዊ መግለጫ ንግግር አድርጓል።

"አርሰናል በአሁኑ ጊዜ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጡ ቡድን ነው። ሁሉም ስታቲስቲክስ ይህን ያሳያሉ። ፍፁም ከፍተኛ አቋም ላይ ናቸው።"

"ይሄ የውድድር ዘመን ለኛ አሁንም በፍፁም አላበቃም ፤ በርግጥ ያሳየነው ወጥነት የሌለው አቋም ከራሳችን የምንጠብቀው አልነበረም ፤ ነገ ግን በተለየ ውድድር ላይ ነው ምንጫወተው ፤ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፍ እንፈልጋለን።"

ቱሄል ስለ አርቴታ: "አስቸጋሪ አጀማመር ነበረው ፤ ነገር ግን ቡድኑ ከጎኑ ቆሞ በአስቸጋሪው ጊዜ ውስጥ አልፏል ፤ እነሱ በጣም ከፍተኛ በሆነ የታክቲክ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ፤ ከኳስ ጋር በጣም የተረጋጉ ናቸው ፤ በዚህም ለእሱ ትክክለኛውን ክሬዲት መስጠት አለባቹ ፤ ግን እኛም ጠንካራ ለመሆን እንሞክራለን የሻምፒዮንስ ሊግ ስታይል ከፕሪሚየር ሊጉ የተለየ ነው ግን ለአርቴታ እና ለክለቡ ትልቅ ክብር አለኝ።"

"በቡንደስሊጋው ላይ ሚፈለገውን ጉልበት አጥተናል። በሊጉ በበቂ ሁኔታ ወጥነት የለንም። ነገ ግን ሊጉን አይደለም ምንጫወተው"

ቱሄል ስለወደፊቱ ቆይታው፦"ለማሰለጥነው ቡድን ሁል ጊዜ ያለኝን ሁሉንም ነገር እሰጣለሁ በዚህ ደረጃ ማሰልጠን በመቻሌ ደስተኛ ነኝ። ስለሌሎች ክለቦች አርዕስተ ዜናዎችን ማንበብ አልፈልግም። ለባየርን እስከ መጨረሻው ጨዋታ ድረስ ሁሉንም ነገር እሰጣለሁ። "

ቱሄል ስለ ኦዴጋርድ፡ "አርሰናል እራሳቸውን እንደ ቡድን ይገልጻሉ እንጂ በአንድ ግለሰብ ላይ ጥገኛ አይደሉም. ኦዴጋርድ በእርግጠኝነት ከዋና ተጫዋቾቻቸው አንዱ ነው ፤እኛም ግን ሁኔታዎችን አስቸጋሪ ለማድረግ ትክክለኛ መፍትሄዎችን ማግኘት እንፈልጋለን። "

ቱሄል ስለ ካይ ሃቨርትዝ፡ "ካይ በአሰልጣኝነት ህይወቴ ለኔ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ጎሎች ውስጥ አንዱን አስቆጥሯል ፣ እሱ በጣም ጥሩ ሰው ነው፣ የሚገባውን አድናቆት እዚህ በማግኘቱ ደስተኛ ነኝ።"

SHARE  @MULESPORT
18.1K views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 22:19:35
16.2K views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 22:03:41
አሮጊቷ ተጫዋች ለማስፈረም ተቃርባለች !

ጁቬንቱሶች ፌሊፔ አንደርሰንን በነፃ ወኪል ለማስፈረም አንድ እርምጃ ቀርቷቸዋል።

መደበኛ ፕሮፖዛል ለብራዚላዊው የክንፍ መስመር ተጫዋች ተልኳል። ሁሉም ነገር በቅርቡ ሊያልቅ ነው።

አሁን በመጨረሻ ደረጃ ላይ የቃል ስምምነት ለመፈፀም እየተደረደሩ ነው። 

SHARE  @MULESPORT
17.1K views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 21:46:28
ኤቨርተኖች እንግሊዛዊውን አጥቂያቸው ዶሚኒክ ካልቨርት ሌዊንን ፈልጎ ለሚመጣ ክለብ እስከ 40 ሚሊዮን ፓውንድ ይጠይቃሉ።

-Football Insider

SHARE @MULESPORT
17.3K views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 21:33:45
"ቪኒሸስን ለመቆጣጠር  ዎከር አስፈላጊ ነው"

በነገው እለት የሚደረገውን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ወሳኝ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ተከትሎ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ ቪኒሸስ ጁንየር አስተያየቱን ሰጥቷል።

ፔፕ "ቪኒሸስ ለመቆጣጠር ካይል ወከር ወሳኝ ሰው ነው ነገር ግን በስልጠና ላይ ተጎድቷል ስለዚህ መፍትሄ መፈለግ አለብን"።

"ጆሽኮ ግቫርዲዮል አለን ግን ለነገ ጨዋታ ለመድረስ አሁን ቢሆን በጥርጣሬ ውስጥ ነው"ሲሉ ተናግረዋል።

SHARE  @MULESPORT
16.9K viewsedited  18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 21:59:50
ፊል ፎደን፣ ቡካዮ ሳካ እና ኮል ፓልመር በዚህ የውድድር ዘመን ስታቲስቲክስ ፦

ኮል ፓልመር ፦

39 ጨዋታዎች
21 ጎሎች
12 አሲስት

ቡካዮ ሳካ ፦

39 ጨዋታዎች
17 ጎል
13 አሲስት

ፊል ፎደን ፦

45 ጨዋታዎች
21 ጎል
10 አሲስት

SHARE  @MULESPORT
15.5K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 21:51:26
◉ አርሰናል በ 2024 38 የፕሪሚየር ሊግ ግቦችን አስቆጥሯል ይህም ከየትኛውም ቡድን ቢያንስ በሰባት ይበልጣል።

◉ አርሰናል በ2024 አራት የ ፕሪሚየር ግቦችን አስተናግዷል።ይህም ከየትኛውም ቡድን ቢያንስ በ6 ያነሰ ነው።

◉ አርሰናል በ2024 ሰባት የ ፕሪሚየር ሊግ Clean Sheet አለው። ይህም ከየትኛውም ቡድን ቢያንስ በ2 ይበልጣል።

መደፈኞቹ እጅግ አስደናቂ አቋም ላይ ናቸው

SHARE  @MULESPORT
14.8K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 21:46:30
አርሰናል ከ1997 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሜዳው ውጪ በፕሪሚየር ሊጉ 5 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ጎል አላስተናገደም።

SHARE  @MULESPORT
14.9K views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 21:40:43
ዲቪድ ራያ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው 5 ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ጎል ያላስተናገደ የመጀመሪያው ስፔናዊ ግብ ጠባቂ ሆኗል።

አስደናቂ ግብ ጠባቂ

SHARE  @MULESPORT
14.3K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 07:50:03
ሮድሪጎ ሪያል ማድሪድን መልቀቅ አይፈልግም !

ብራዚላዊዉ የሪያል ማድሪድ አጥቂ ሮድሪጎ በመጪው ክረምት ሪያል ማድሪድን የመልቀቅ ሀሳብ የለውም ኪሊያን ምባፔ ቢመጣም መልቀቅ አይፈልግም።

ሮድሪጎ በሪያል ማድሪድ ያለው ፕሮጀክት በእግር ኳስ ውስጥ ምርጥ ፕሮጀክት እንደሚሆን ያምናል።

ሊቨርፑል፣ አርሰናል፣ ፒኤስጂ፣ ማን ሲቲ እና ማን ዩናይትድ ሮድሪጎ ላይ ፍላጎት አሳይተዋል ግን ተጫዋቹ መልቀቅ አይፈልግም።

SHARE  @MULESPORT
13.4K views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ