Get Mystery Box with random crypto!

'አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጡ ቡድን ነው' የባየር ሙኒኩ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ነገ | ሙሌ SPORT

"አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጡ ቡድን ነው"

የባየር ሙኒኩ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ነገ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ መርሀ ግብር ከአርሰናል ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት በጋዜጣዊ መግለጫ ንግግር አድርጓል።

"አርሰናል በአሁኑ ጊዜ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጡ ቡድን ነው። ሁሉም ስታቲስቲክስ ይህን ያሳያሉ። ፍፁም ከፍተኛ አቋም ላይ ናቸው።"

"ይሄ የውድድር ዘመን ለኛ አሁንም በፍፁም አላበቃም ፤ በርግጥ ያሳየነው ወጥነት የሌለው አቋም ከራሳችን የምንጠብቀው አልነበረም ፤ ነገ ግን በተለየ ውድድር ላይ ነው ምንጫወተው ፤ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፍ እንፈልጋለን።"

ቱሄል ስለ አርቴታ: "አስቸጋሪ አጀማመር ነበረው ፤ ነገር ግን ቡድኑ ከጎኑ ቆሞ በአስቸጋሪው ጊዜ ውስጥ አልፏል ፤ እነሱ በጣም ከፍተኛ በሆነ የታክቲክ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ፤ ከኳስ ጋር በጣም የተረጋጉ ናቸው ፤ በዚህም ለእሱ ትክክለኛውን ክሬዲት መስጠት አለባቹ ፤ ግን እኛም ጠንካራ ለመሆን እንሞክራለን የሻምፒዮንስ ሊግ ስታይል ከፕሪሚየር ሊጉ የተለየ ነው ግን ለአርቴታ እና ለክለቡ ትልቅ ክብር አለኝ።"

"በቡንደስሊጋው ላይ ሚፈለገውን ጉልበት አጥተናል። በሊጉ በበቂ ሁኔታ ወጥነት የለንም። ነገ ግን ሊጉን አይደለም ምንጫወተው"

ቱሄል ስለወደፊቱ ቆይታው፦"ለማሰለጥነው ቡድን ሁል ጊዜ ያለኝን ሁሉንም ነገር እሰጣለሁ በዚህ ደረጃ ማሰልጠን በመቻሌ ደስተኛ ነኝ። ስለሌሎች ክለቦች አርዕስተ ዜናዎችን ማንበብ አልፈልግም። ለባየርን እስከ መጨረሻው ጨዋታ ድረስ ሁሉንም ነገር እሰጣለሁ። "

ቱሄል ስለ ኦዴጋርድ፡ "አርሰናል እራሳቸውን እንደ ቡድን ይገልጻሉ እንጂ በአንድ ግለሰብ ላይ ጥገኛ አይደሉም. ኦዴጋርድ በእርግጠኝነት ከዋና ተጫዋቾቻቸው አንዱ ነው ፤እኛም ግን ሁኔታዎችን አስቸጋሪ ለማድረግ ትክክለኛ መፍትሄዎችን ማግኘት እንፈልጋለን። "

ቱሄል ስለ ካይ ሃቨርትዝ፡ "ካይ በአሰልጣኝነት ህይወቴ ለኔ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ጎሎች ውስጥ አንዱን አስቆጥሯል ፣ እሱ በጣም ጥሩ ሰው ነው፣ የሚገባውን አድናቆት እዚህ በማግኘቱ ደስተኛ ነኝ።"

SHARE  @MULESPORT