Get Mystery Box with random crypto!

'ሪያል ማድሪድን በተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ ቀላል አይደለም' ስፔናዊዉ የውሀ ሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ፔ | ሙሌ SPORT

"ሪያል ማድሪድን በተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ ቀላል አይደለም"

ስፔናዊዉ የውሀ ሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከሪያል ማድሪድ ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት በጋዜጣው መግለጫ ንግግር አድርጓል።

"ጨዋታውን ለመቆጣጠር ብቻ አይደለም ወደዚህ ምንመጣው ፣ ሪያል ማድሪድን ለመጉዳት ፣ እነሱን ለመቅጣት፣ ጎል ለማግባት መሞከር አለብን። "

"የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አንዴ ብቻ ማንሳት ለማን ሲቲ በቂ አይደለም"

"ሪያል ማድሪድን በተከታታይ ሁለት ጊዜ በተመሳሳይ መንገድ ማሸነፍ ግን ቀላል አይደለም..."

"ማድረግ ያለብን ነገር ላይ እናተኩራለን ፣ የተቀናቃኞቻችንን የጥንካሬ ነጥቦችን እንፈትሻለን እና ለእሱ እንዘጋጃለን። ግን በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ እናተኩራለን"ሲል ጋርዲዮላ ተናግሯል።

ፔፕ ጋርዲዮላ አክሎም ስለ ጁድ ቤሊንግሃም እንዲህ ብሏል፦ "ልዩነቱን የሚያደርገው በጭንቅላቱ ውስጥ ያለው ነገር ነው ፤ እሱ አስደናቂ የውድድር ዘመን እያሳለፈ ነው ፤ በጣም ወጣት ነው ፤ ወደፊትም አስደናቂ የእግርኳስ ህይወት ይጠብቀዋል"ሲል ተናግሯል።

SHARE  @MULESPORT