Get Mystery Box with random crypto!

ሙሌ SPORT

የሰርጥ አድራሻ: @mulesport
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 328.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሙሌ ስፖርት ስፖርታዊ መረጃዎችን ከእሁድ እስከ እሁድ ያገኙበታል
የሃገር ቤት መረጃ
የአውሮፓ ሊግ መረጃ
ቀጥታ ስርጭት
የዝውውር ዜና
ለማስታወቂያ ስራ @Mulesporta
@Teme_Ayu

ስልክ ቁጥር 251911857852

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-29 13:58:58
"ቼልሲ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው"

በውድድር አመቱ መጨረሻ ቼልሲን እንደሚለቅ ያሳወቀው ቲያጎ ሲልቫ የስንብት ንግግር አድርጓል።

"ቼልሲ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው እኔ እዚህ የመጣሁት ለአንድ አመት ብቻ ለመቆየት በማሰብ ነበር ግን እዚህ አራት አመት ሆኖኛል ፤ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቤም ጭምር።"

"ልጆቼ ለቼልሲ ይጫወታሉ ስለዚህ የቼልሲ ቤተሰብ አባል መሆን ትልቅ ኩራት ነው ፤ በተለይ ልጆቼ እዚህ ስላሉ። ብዙ ተጫዋቾች ሊሳተፉበት በሚፈልጉበት በዚህ አሸናፊ ክለብ ውስጥ ህይወታቸውን እንደሚቀጥሉ ተስፋ አደርጋለሁ። "

"ይመስለኛል በአራት አመታት ውስጥ ሁል ጊዜ ያለኝን ሁሉንም ነገር እሰጥ ነበር ፤ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ነገር መጀመሪያ ፣ መሀከል እና መጨረሻ አለው።"

"ይህ ማለት ግን ይህ በአጠቃላይ መጨረሻ ነው ማለት አይደለም ፤ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በሌላ ሚና መመለስ እንድችል በሩ ክፍት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።"

"ግን ይሄ ሊገለጽ የማይችል ፍቅር ነው። እና አመሰግናለሁ ብቻ ነው የምለው"ሲል ቲያጎ ሲልቫ ተናግሯል።

SHARE @MULESPORT
17.0K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 13:46:02
አዲሱ የሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሪቻርድ ሂዩዝ የመሀመድ ሳላህ ፣ ቨርጂል ቫንዳይክ እና ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ የኮንትራት ሁኔታን ያስተናግዳል። የሶስቱም ተጫዋቾች ውል በ2025 ያበቃል።

ዴቪድ ኦሬንስታይን

SHARE @MULESPORT
15.4K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 13:35:14
ቲያጎ ሲልቫ ቼልሲን ይለቃል !

ቲያጎ ሲልቫ በዚህ ሲዝን መጨረሻ እና ከ4 አመታት በኋላ ቼልሲን እንደሚለቅ አስታውቋል።

የ39 አመቱ ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫ በ2020 ቼልሲን የተቀላቀለ ሲሆን ከዚህ ቡድን ጋር እንደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ያሉ ጠቃሚ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።

ቲያጎ ሲልቫ UEFA ሱፐር ካፕ እና የአለም ክለብ ዋንጫንም ማሳካት ችሏል።

ሲልቫ ለቼልሲ 151 ጨዋታዎችን የተጫወተ ሲሆን 9 ጎሎችን እና 3 አሲስቶችን ማድረግ ችሏል።

ፍሉሚንሴ የዚህ ልምድ ያለው ተከላካይ ቀጣይ መድረሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

SHARE @MULESPORT
15.6K views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 13:28:35
ሊቨርፑል ሞሃመድ ሳላህ እንደሚቆይ ይጠብቃሉ እና ከእሱ ጋር ቢያንስ አንድ ተጨማሪ የውድድር አመት እቅድ አውጥተዋል። በተጫዋቹ በኩል መልቀቅ የመፈለግ ምልክት የለም። ሳላህ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በሊቨርፑል ለመቆየት አቅዷል።

ዴቪድ ኦሬንስታይን

SHARE @MULESPORT
15.3K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 11:50:57
ሊቨርፑሎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት የመሀል ተከላካዮችን መመልከት ጀምረዋል ቡድኑን ለማጠናከር ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ቦታዎች አንዱ ነው።

በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ከአርኔ ስሎት ጋር ለመወያየት አማራጮችን እና ዝርዝርን በተመለከተ የውስጥ ድርድር በመካሄድ ላይ ነው።

- Fabrizio Romano

SHARE @MULESPORT
16.8K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 10:49:43
የሳዑዲ ፕሮፌሽናል ሊግ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሚካኤል ኢማናሎ ኬቨን ደብሩይንን ከማንቸስተር ሲቲ ለማስወጣት እየሰሩት ሲሆን በሰኔ ወር 33 አመቱ የሚሞላው ቤልጄማዊው ተጫዋች የሳውዲዎችን ሀሳብ እስካሁን እንዳልተቃወመ ተገልጿል።

ዘ አትሌቲክስ

SHARE @MULESPORT
17.3K views07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 10:03:07
ክርስቲያን ሮሜሮ በዚህ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን 5 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ይህ ቁጥር የሚከተሉት አጥቂዎች ካስቆጠሩት የጎል ብዛት ይበልጣል፦

ጋብሬል ጄሱስ ፡ 4 ጎሎች
ሚሃይሎ ሙድሪክ ፡ 4 ጎሎች
ፓብሎ ሳራቢያ ፡ 4 ጎሎች
ማዱኬ ፡ 4 ጎሎች
አንቶኒ : 1 ጎል

SHARE @MULESPORT
17.5K views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 07:15:22
በዚህ ሲዝን ለማንችስተር ሲቲ ኬቨን ደብሩይን እና ኤርሊንግ ሃላንድ ፦

ደ ብሩይን ፦

21 ጨዋታዎች
6 ጎሎች
16 አሲስት

ኤስሊንግ ሃላንድ፡

40 ጨዋታዎች
32 ጎሎች
6 አሲስቶች

ልዩ

SHARE @MULESPORT
19.0K views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 07:06:13
"በድሉ ደስተኛ ነኝ"

ሆላንዳዊው የቀያይ ሰይጣኖቹ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ከምሽቱ የሺፊልድ ድል በኃላ ንግግር አድርጓል።

"በዚህ ጨዋታ ብዙ አዎንታዊ ነጥቦች ነበሩን። ሁለት ጊዜ ከተመራን በኋላ ጠንካራ ምላሽ አሳይተናል። ግን አሉታዊ ነጥቦችም ነበሩ. በጣም በቀላሉ ተቆጥሮብናል ይህም ተቀባይነት የለውም። ከዚህ መማር አለብን። በድሉ ግን ደስተኛ ነኝ።"

"አሁን እያስቆጠርን ያለነው የጎል ብዛት ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። የተከላካይ መስመራችንን ማጠናከር ከቻልን በቡድኑ ብቃት ላይ የበለጠ መረጋጋት እናያለን።"

"ጨዋታው ለተመልካቾች በጣም አስደሳች ነበር፡ 4 ጎል እና ብዙ የጎል እድሎች ነበሩ። እኔ እንደማስበው ቡድናችን ጥሩ እንቅስቃሴ አድርጓል። ተለዋዋጭ እና አጥቂ እግር ኳስ መጫወት እንፈልጋለን"ሲል ቴን ሃግ ተናግሯል።

SHARE @MULESPORT
15.6K views04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 07:01:52
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፉክክሩ እንደጦፉ ይገኛል።

ማንችስተር ሲቲ በዛሬው እለት ከብራይተን ጋር ጨዋታ ያደርጋል።

SHARE @MULESPORT
14.3K views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ