Get Mystery Box with random crypto!

Muhammed Computer Technology (MCT)

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedcomputertechnology — Muhammed Computer Technology (MCT) M
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedcomputertechnology — Muhammed Computer Technology (MCT)
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedcomputertechnology
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.76K
የሰርጥ መግለጫ

#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው!
በዚህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
አስተያየት ካላችሁ @ma1000me ልታገኙኝ ትችላላችሁ
በተጨማሪም የ YouTube ቻናል 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ጥሩ ቪዲዮችን ማግኘት ይችላሉ!

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-02-24 12:26:33
#ማሰታወቂያ

#የህንፃ_ኤሌክትሪክ_መስመር_ዝርጋታ ስራ ወጣቶች ሙያውን ከያዙት በቀላሉ ወደ ስራ የሚገቡበት ዘርፍ ነው። በዚህ ዘርፍ ከሰለጠኑ ከፈለጉ በጥሩ ደሞዝ በቅጥር ካልፈለጉ ደግሞ በግል የሚሰሩበትና ከፍተኛ ገንዘብ የሚያገኙበት ዘርፍ ነው።
እኛ ደግሞ በዘርፉ አንቱ የተባሉ ባለሙያ እንደምናረግዎታለን ከዚህ በፊት ከተቋማችን የሰለጠኑትና አሁን ስራ ላይ ያሉት ምስክር ናቸው
በአይነቱ ልዩ የሆነውንና ስራ ላይ ያሉ ሰዎች ትርፍ ጊዚያቸውን ተጠቅመው ተጨማሪ ገቢ የሚያገኙበት
#ቅዳሜ ከሰዓት ከ8:30-11 ሰዓትና #እሁድ ጥዋት ከ 3-6 ሰዓት ለ 3 ወራት ያክል በወርክሾፕና በሳይት ላይ ልምምድ   የሚሰጠውን የህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስልጠና #እሁድ(24/06/16ዓ.ም) ከጥዋቱ 3:00  ቦሌ ሚካኤል በሚገኘው ማሰልጠኛችን በመገኘት ስልጠናውን መጀመር እንደምትችሉ ስናሳውቃችሁ በደስታ ነው
ክፍያችሁን ከዛሬ ጀምሮ ስልጠናው እስከሚጀምርበት ቀን ድረስ ከሰኞ-ቅዳሜ በስራ ሰዓት  በአካል ቢሮ በመምጣት ወይም በባንክ  በመክፈል መመዝገብ  ትችላላችሁ
ስራ ላይ ያላችሁ የሙያ ባለቤት ሆናችሁ በትፍ ጊዚያችሁ በመስራት ተጨማሪ ገቢ የምታገኙበት ምርጥ ዘርፍ ነው።

ይመዝገቡ ይሰልጥኑ የሙያ ባለቤት ይሁኑ ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ
በአጭር ጊዜ ስልጠና የረዥም ጊዜ ህልምዎን ያሳኩ
#አሜን_ኤሌክትሪካል_ስራና_ማሰልጠኛ_ማዕከል

#ለተጨማሪ_መረጃ
#ለፌስቡክ:-
https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL
#ለዩቱብ፦



#ስቁ
0911585854
0118644716
0991156969
12.9K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-18 19:05:49 ከዚህ በታች ያለው የቴሌግራም ቻናል ስለኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ጥያቄ አጥቸ ሰዎች የሚፈተኑበት ቻናል ነው። እስከዛሬ ድረስ 50 ጥያቄዎች ያሉ ሲሆኑ በመግባት እራሳችሁን ፈትኑ እወቁ! መልሱን ወዲያውኑ ታውቃላችሁ! ወደፊት ጥሩ ጥያቄወችን እያዘጋጀሁ እለቅላችኋለሁ

ይግቡ ሊንኩ ከታች ያለውን ይጫኑ
https://t.me/mame_tech_QA
13.4K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-02 15:59:27 የጥናትና ምርምር (Research) መሰረታዊ ዋና ዋና ክፍሎች ምንድን ናቸው?
ይመልከቱት በምርጥ አቀራረብ የተዘጋጀ!












እነዚህ 16 ነጥቦች ልብ ይበሉ!

የጥናት/ሪሰርች ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት ሊለያይ ይችላል፡፡
ተጨባጭ ችግርን ለመፍታት ይሁን የተደበቀ ምስጢርን ፈልፍለን ለማግኘት ወይንም ከዚሁ ለተለየ ዓላማ ጥናት ሊታቀድና ሊከናወን ይችላል፡፡
በዚሁ መሰረት አንድ ጥናት/ሪሰርች ሲዘጋጅ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ብዙዎች ዘንድ የተለመዱ ዋና ዋና ይዘቶችን ሊያካትት ይችላል፡፡
ይመልከቱት በምርጥ አቀራረብ የተዘጋጀ!











13.6K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-30 05:31:01 ከF1 እስከ F12 ያሉ #የኪቦርድ ቁልፎች አገልግሎት

በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው
የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function
Key እንላቸዋለን፡፡
በዋናነትም ከሌሎች #ቁልፎች ጋር
በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ
ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና
ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው
ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡

F1
ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው
ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን #የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ
Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡
F2
#የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር
F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt
+ Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡
F3
ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift +
F3 መጫን #የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን
አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን
ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡
F4
አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 #መጫን
ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ
አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን
ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ
#የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን
ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን
ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ
ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4
ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt +
F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት
ነው፡፡
F5
አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5
መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ
Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት
ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡
F6
በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን
አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው
ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ
ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን #ወደቀጣዩ
የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡
F7
ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ
#Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም
ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡
F8
ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ #Startup menu
ለመግባት የጠቅማል፡፡
F9
በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን
በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን
#Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { }
ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት
CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ
ለማጥፋት
F10
አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ
ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን #ራይት ክሊክ
እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
F11
በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን
የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን
ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡
F12
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ #የ Save as ማስኮትን
ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡
ስሞኑን የለቀቅኳቸው ጥሩና አስተማሪ ቪዲዮዎች አሉ እነሱን እንድታዪቸው ግብዣየ ነው። በተጨማሪም አዳዲስ ቪዲዮችን እየሰራሁ ስለሆነ #Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን ይከታተሉ!
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!
የ YouTube ቻናል ሊንክ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
12.7K views02:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-23 14:37:26 የቴክኒክና ሙያ አዲሲ ካሪኩለት ኮርሶች
15.6K views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-02 10:47:57 የኮምፒውተር 32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት እና ጥቅም
ምንድነው?
=======================================
ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት
ይዘን
ቀርበናል ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን
ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ
(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር
ለመወሰን
ያግዛል፡፡ የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት
በሚል
የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም
አይነት እክል
የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና
ሶፍትዌሮች
ይወስኑታል፡፡
1. 32 ቢት ፕሮሰሰር
32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ
የሚገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና
ኤኤምዲ እየሰሩ
ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ኦፕሬቲን ሲስተም እና
ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት
ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ
ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 95፣
98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው
የተሰሩ ናቸው፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ
ሲስተም
መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን
የሚችለው
32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡
2. 64 ቢት ፕሮሰሰር
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961 አካባቢ
አይቢኤም IBM
7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም
እስከ 2000
ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ
አልነበረም:: ማይክሮሶፍት 64
ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ
ሲስተም ለገበያ አቀረበ
በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64
ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ
ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡ 64 ቢት
ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር
64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል
ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን
ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡ ማስታወሻ 64 ቢት
ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ
ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ
ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን
ሲስተም ላይ
የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት
ፕሮግራሞች/
ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም)
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን
አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት
አንዱ
ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64
ቢት
ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad
core፣ በsix
core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ
ነው፡፡
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው
በኮምፒውተሩ
ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት
ፕሮሰሰር
ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም
የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር
ከ4GB
በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣
ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም
አስፈላጊ ነው፡፡
በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64
ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት ቢሆኑ ይመረጣል።
ሼር ማድረግዎን አይርሱ፤፤ መልካም ቀን ይሁንልዎ
Like እና Share ማድረግ አይርሱ!
====================
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ
12.6K views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-30 06:57:02 ልታውቋቸው የሚገቡ Commands እንዴት አድርገን የኮምፒውተራችንን Users ማስተዳደር እንችላለን?
በመጀመሪያ ደረጃ Command Prompt ወይም CMDን እንከፍታለን።
ለምክፈት በ3 አማርጮች እንጠቀማለን
1ኛ Start-> All Program -> Accessories -> Command Prompt
2ኛ Crtl+R በመጫን CMD ብለው በመጻፍ OKን ይጫኑ
3ኛ start -> Search Box ላይ CMD ወይም Command Prompt ብለው ይፈልጉ። ከዛም ከሶስቱ 1ን አማራጭ ተጠቅመው ሲከፍቱት Black Screen ይመጣላችኋል። ከዛም ከታች ከ1-8ኛ ድረስ ያለውን ተግባራቶችን ይሞክሩ።
አዘጋጅ Muhammed Computer Technology
1ኛ net user ይህ ኮማንድ የሚጠቅመን ከኮምፒውተራችን ያሉንት Users ይዘረዝርልናል። እንዲሁም ከማንኛውም ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚል አካውንት አለ እሱ ምን እንደሆነ ከታች መልሱን ያገኛሉ።
2ኛ net user muhammed /add ይህ ኮማንድ ከኮምፒውተራችን ላይ muhammed የሚባል User Create(እንዲፈጠር ያደርግልናል)
3ኛ net user muhammed * ይህ ኮማንድ ከላይ ለፈጠራችሁት muhammed ለሚባል User ወይም ከዚህ በፊት ላለ User ለምሳሌ amin የሚባል ቢኖር Muhammed በሚለው ፈንታ amin የሚለውን ስታስገቡ ለUseሩ Password እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል። ትኩረት ሁለት ጊዜ password እንድታስገቡ ይጠይቃችኋል ሁለቱም password ተመሳሳይ መሆን አለበት። እንዲሁም ፓስውርድ ስታስገቡ እይታያችሁም ወይም ፓስወርድ ስትጽፉ አይታያችሁም ግን በውስጥ ታዋቂነት እየጻፈ ስለሆነ ግራ እንዳትጋቡ።
ነገርግን ለUseሩ password ነስጠት ባትፈልጉ ዝም ብላችሁ 2 ጊዜ Enterን መጫን ብቻ ነው።
4ኛ net user muhammed /add * ይህ ኮማንድ የሚያገለግለን አንድን User ከነ password Create(መፍጠር) ብትፈልጉ ይህንን መጠቀም አለባችሁ። ኮማንዱ በመጀመሪያ ደረጃ User create ያደርግና በተመሳሳይ ፓስወርድ እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል። password ማስገብት ከፈለጋችሁ አስገቡ ግን password ማስገባት ካልፈለጋችሁ Enterን 2 ጊዜ ይጫኑ።
ይህ ማለት ከላይ ተ.ቁ 2ና 3ን በአንድ ጊዜ ለመስራት ያገለግለናል።
5ኛ net localgroup Administrators muhammed /add ይህ ኮማንድ ከላይ የፈጠርነው user ምን ጊዜም Standard User ነው የሚሆነው።
በኮምፒውተር ተጠቃሚዎች አይነት Users Type በ3 ይከፈላል 1ኛ Administrator 2ኛ Standard User 3ኛ Gusts ናቸው።
እነዚህ Users ለምሳሌ ከላይ የፈጠርነው User Muhammed የሚባለው ከላይ ባለው ኮማንድ ሲፈጠር Standard User ነው። Standard User ደግሞ በኮምፒውተሩ ላይ ሙሉ የሆነ የመቆጣጠር አቅም የለውም የግድ ምን መሆን አለበት Administrator መሆን አለበት።
ስለዚህ ከላይ ያለውን 5ኛ ተ.ቁን Command መጠቀም ይኖርብናል።
6ኛ net localgroup Administrators muhammed /del ይህ ኮማንድ በተ.ቁ 5 ላይ muhammed የሚባለውን User ወደ Administratorነት ቀይረነዋል ነገር ግን ወደ Standar User ለመቀየር ከተፈለገ 6ኛውን ኮማንድ መጠቀም አለብን ማለት ነው። ይህም Muhammed የሚባለውን User ከ Administrator Account Type ወደ Standard User Account Type ቀየርነው ማለት ነው።
7ኛ ከማንኛው ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚባል User አለ ይህ User ለአደጋ ጊዜ ተብሎ የተቀመጠ User አለ ይህ User ከኮምፒዩተሩ ተደብቆ ሁኖ ነው ያለው ይህንን User መሉ በሙሉ ከኮምፒውተሩ ማጥፋት አይቻልም ነገርግን ሌሎች የተፈጠሩ User Account ማጥፋት ትቻላል። ለእናንተ የምመክራችሁ User Accountችን ሊጠፋብን ይችላል የሚል ስጋት ካለባችሁ Administrator የሚባለውን User Account Active ማድረግ አለባችሁ አሁን እሱን እናያለን!
net user Administrator active:yes
ከኮምፒውተሩ የተፈጠረን User Account ሳናጠፋ Inactive ለማድረግ ወይም እንዳይሰራ ለማድረግ ለምሳሌ muhammed የሚለውን እንዳይሰራ ለማድረግ።
net user muhammed active:no ይህ ኮማንድ muhammed የሚባለው user inactive ሁኗል ማለት ነው። እንደገና ግን Active ለማድረግ ከፈለጋችሁ
bet user muhammed active:yes የሚለውን ኮማንድ ተጠቀሙ።
8ኛ ከኮምፒውተሩ ያለውን User Account ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ከፈለጋችሁ ለምሳሌ muhammed የሚባለውን ማጥፈት ብትፈልጉ
net user muhammed /del
ማስጠንቀቂያ ይህ ኮማንድ ለምሳሌ muhammed የሚባለውን user መረጃ ሙሉ በሙሉ ነው የሚያጠፋው ያ ማለት በውጡ ያስቀመጣቸው Desktop ላይ My Documents ላይ My Music ላይ My Picture ላይ ያስቀመጣቸውን ሙሉ መረጃ ያጠፋብናል ስለዚህ ትኩረት ማድረግ አለባችሁ።
ግን ለትምህርት ለምሳሌ እንደእስካሁኑ muhammed የሚባል User Account ላይ እንደ መለማመጃ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
በቪዲዮ ከገለጋችሁ
እንዴት የኮምፒተር Usersና (Password) በCMD መስበር አንችላለን How to Crack Computer Password?




#ይሞክሩት!
ከተመቻችሁ ለሌሎች እንዲደርሳቸው #ሼር ቢያደርጉ ጥሩነት ነው።
12.6K views03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-27 12:38:27 የኮምፒውተር ሀርድ ዲስክን እንዴት መክፈል እንችላለን?
ዛሬ የምናየው እንዴት አድርገን አንድ ሎካል ዲስክን ወደ ሁለት ከዚያ በላይ ክፍልፋዮች እንደምንቀይር ነው።
ለምሳሌ Local disk C: ካለን ከሁለት ለመክፈል ለምሳሌ
#1_right click on My computer
#2_ከዛ Manage የሚለውን እንነካለን
#3_ከዛ ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን
#4_ከዛ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:
በመምረጥ right click እናደርጋለን
#5_ከዛ shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል
#6-ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ
ማስጠንቀቂያ:- ቁጥሩ በሜጋ ባይት ነው የሚገባው ለምሳሌ 50GB መክፈክ ብትፈልጉ 1GB ማለት 1024 MB ነው ይህ ማለት 50*1024=51,200 ይሆናል ስለዚህ 51,200 ብለን ማስገባት ይጠበቅብናል።
#7_ከዛ በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ
#8_click on "new simple volume
ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::
ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም።
እስኪ ለምሳሌ 152 GB ለመክፈል ብንፈልግ ስንት ብለን መጻፍ ይጠበቅብናል? ኮሜንት ላይ ይጻፉልኝ!
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!

የ YouTube ቻናል ሊንክ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
12.6K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 20:19:22 ምርጥ 11 የኮምፒዉተር ሶፍትዌር ማዉረጃ ሳይቶች

1) getintopc
https://getintopc.com
የተለያዩ ክራክ የተደረጉና ምርጥ ነጻ ሶፍትዌሮችን በማቅረብ የሚታወቅ ምርጥ ዌብሳይት ነው። በመሆኑም በዚህ ዌብሳይት የፈለጉትን ሶፍትዌሮችን በመፈለግ ማግኘት የሚያስችል በመሆኑ በብዙ ሰዎች ዘንድ ተፈላጊ ነው።

2) Download
https://download.cnet.com

የኮምፒዉተር ሶፍትዌሮችን ከማዉረጃ ሳይቶች ቀደምት ሲሆን ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተመሰረተ ነዉ፡፡ የዚህ ሳይት ባለቤት በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ገናና ስም ያለዉ CNet ነዉ፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም የሞባይል አፕሊኬሽኖችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከ 100,000 በላይ ፕሮዳከቶችን አካቷል፡፡ ሶፍትዌሮቹ በ ኤዲተሮች ተገምግመዉ እና ደረጃ ተሰጥቷቸዉ ተቀምጠዋል፡፡ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ግምገማዎችን መፃፍ እና ለ ሶፍትዌሮቹ ደረጃ መስጠት ይችላሉ፡፡

3) FileHippo
https://filehippo.com

ይህ ሳይት በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ነዉ፡፡ FileHippo Update Checker የሚል ፕሮግራም ያካተተ ሲሆን ይህም በኮምፒዉተራችን ላይ የጫንናቸዉን ሶፍትዌሮች scan በማድረግ አዲስ የተሻሻለ ምርት ካላቸዉ ይጠቁመናል፡፡ ይህም ኮምፒዉተርን ከሚያጠቁ ቫይረሶች ለመከላከል እጅጉን ይጠቅመናል፡፡

4) ZDNet
https://downloads.zdnet.com

ይህ ሳይትም እንደሌሎቹ ብዙ የ ሶፍትዌር አማራጮችን የያዘ እና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሳይት ነዉ፡፡

5) Softpedia
https://www.softpedia.com

Softpedia የሮማኒያ ዌብሳይት ሲሆን ሶፍትዌሮችን ዳዉንሎድ ማድረግ እና ስለ ሶፍትዌሮቹ ማብራሪያ መረጃዎችን ማግኘት ያስችለናል፡፡ ከ ሶፍትዌሮቹም በተጨማሪ የ ቴክኖሎጂ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና መዝናኛ ዜናዎችን ያገኙበታል፡፡ ሶፍትዌሮችን በ ካታጎሪ ተቀምጠዉ ማግኘት ስለምንችል ስራችንን ያቀልልናል፡፡ ተጠቃሚዎችም በሚፈልጉት መስፈርት መፈለግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በተሻሻሉበት ቀን፣ በተጠቃሚ ብዛት፣ ሬቲንግ እና በመሳሰሉት፡፡

6) Tucows
https://www.tucows.com/downloads

ስሙ ምህጻረ ቃል ሲሆን ይህም The Ultimate Collection Of Winsock Software ማለት ነዉ፡፡ ለ Windows, Linux እንዲሁም ለድሮዎቹ የ Windows ቨርዢኖች የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡

7) FreewareFiles
https://www.freewarefiles.com

ነፃ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በብዛት የምናገኝበት ሳይት ሲሆን ከ 15,800 በላይ ነፃ ሶፍትዌሮችን አካቷል፡፡ እነዚህን ሶፍትዌሮችንም በ ካታጎሪ ስለተቀመጡ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡

8) MajorGeeks
http://m.majorgeeks.com

ይህ ሳይት በፊት TweakFiles በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፋይሎች አሪፍ ኢንተርፌስ ያላቸዉ እና ለተጠቃሚዎች በቀላሉ የተገለፁ ናቸዉ፡፡ ፋይሎቹ ዌብሳይቱ ላይ ከመለጠፉ በፊት ጥራታቸዉ ይረጋገጣል ይህም ብዙዎችን ከሚያሰለቸዉ የዉሸት ሶፍትዎሮች እንዲሁም ቫይረሶች ይጠብቅዎታል፡፡ በተጨማሪም አሪፍ ዩሰር ኮሚዩኒቲ ያለዉ ሲሆን ስለ ኮምፒዉተር ያሉንን ጥያቄዎች ይመልሱልናል፡፡

9) FileCluster
https://www.bytesin.com

FileCluster አሁን ላይ ከተመሰረቱ አዳዲስ ዌብሳይቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ተጠቃሚዎቹም አዲስ እና የተሻሻሉ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የ WordPress Themes፣ ዜናዎችን እና ሶፍትዌር ካምፓኒዎችንም ማግኘት ይችላሉ፡፡

10) Soft32
https://www.soft32.com

በ 2003 የተመሰረተ ሲሆን የ ሶፍትዌር ዳይሬክተሪዉን ቶሎ ቶሎ update በማድረግ ይታወቃል፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux እንዲሁም ለ ሞባይል የሚሆኑ ሶፍትዌሮች ሲኖሩት ለ iPhone ተጠቃሚዎች ብቻ ራሱን የቻለ ክፍል አዘጋጅቷል፡፡ ከ 85,000 በላይ ሶፍትዌሮች ሲይዝ ጥያቄዎቻችንን መጠየቅ የምንችልበት ፎረምም አለዉ፡፡

11) File Horse
https://www.filehorse.com

እንደ ሌሎቹ ሳይቶች በቁጥር ብዙ ሶፍትዌሮችን ያካተተ ባይሆንም በጣም ታወቂ እና ጥራት ያላቸዉን ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የምናወርዳቸዉ ፋይሎችም ቫይረስ እንደሌለዉ የሚያረጋግጥ ሲስተም አካቷል፡፡ ነጻ ሶፍትዌሮችን ስለያዘ በክፍያ የሚገኙ ሶፍትዌሮችንም አማራጭ ነጻ ሶፍትዌር ልናገኝበት እንችላለን፡፡
telegram channel
Join
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
16.8K views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 17:11:58 የስልኮቻችንን ባትሪ ዕድሜ ለማራዘም እና የኢንተርኔት አጠቃቀም ፍጆታን ለመቀነስ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ባለሙያዎች አስቀምጠዋል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን ተግባራት ቢያከናውኑ የስክዎን ባትር እድሜ ያራዝማሉ፤ የኢንተርኔት አጠቃቀም ወጪን ይቀንሳሉ።
1. የማይጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች ባክግራውንድ(ዳታ) እንዳይሰሩ ማድረግ
2. ሞባይል ስልክዎን ቻርጅ ላይ ሰክተው አለመጠቀም
3. የማይጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች ወደ ስልክዎ ማሳወቂያ እንዳይልኩ ማድረግ
4. አቅጣጫ መፈለጊያ፣ ብሉቱዝ፣ 3ጂ/4ጂ እንዲሁም ዋይፋይ በማንጠቀምበት ጊዜ ማጥፋት
5. ትላልቅ ፋይሎችን ለማውረድ ገመድ አልባ ኢንተርኔት(ዋይፋይ) ብቻ መጠቀም
6. የሞባይል መተግበሪያዎችን ለማሻሻል ዋይ ፋይን ይጠቀሙ
7. ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ጊዜ የሞባይልዎን ኢንተርኔት(ዳታ) ይዝጉ
8. አገልግሎት የማይሰጡ ወይም ጊዜ ያለፈባቸውን መተግበሪያዎችን ከስልክዎ ያስወግዱ
9. ሁልጊዜ የስልክዎ ስክሪን የሚጠፋበትን ደቂቃ ያሳጥሩ፤ ከተቻለም ወደ ሰኮንዶች ይቀንሱ
10. ለስልኩ የተሻለ ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር ይጫኑለት።
13.8K views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ