2023-05-17 20:58:12
የወረቀት ገንዘብ ከምን ይሰራል?
የብር ኖትን ለመጀመሪያ ጊዜ እ.አ.አ በ1914 ይፋ ያደረገችው እንግሊዝ እንደሆነች ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚያወሱት ቻይናውያን እ.አ.አ በ900 አካባቢ እንደጀመሩት ታሪክ ይነግረናል፡፡
ለመሆኑ ገንዘብ በኪስዎ ሲይዙ ከምን እንደሚሰራ አስብው ያውቃሉ? አዲስ የብር ኖት በእጅዎ ይዘዉ አሽትተውስ ያውቃሉ? እንግዲያዉስ ያ ሽታ የጥጥ ሽታ ነው፡፡
የብር ኖት ወረቀት በየዕለቱ ከምንጠቀማቸው ወረቀቶች የተለየ ነው፡፡ የብር ወረቀት የሚሰራው ከጥጥ ነው ይህም የሚሆንበት ምክንያት በጣም ረዥም ጊዜ እንዲቆይ እና በቀላሉ እንዳይቀደድ ያደርገዋል:: አንድ የአሜሪካ ዶላር 4000 ጊዜ ያክል ሳይቀደድ መተጣጠፍ ይችላል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ወረቀትን ከጥጥ የሰሩትም አሜሪካኖች ናቸው፡፡
የወረቀት ገንዘብ አሰራር ሂደቶች
1. ከፍተኛ መጠን ያለዉን ጥጥ ትልቅ እና ግዙፍ ድስት ዉስጥ በማስገባት በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ለሁለት ሰአት ተጨቁኖ ድስቱ ዉስጥ ይቆያል፡፡ በመቀጠልም ትልቅ የመዋኛ ገንዳ በሚያክል ገንዳ ዉስጥ በማስገባት በዉሃ በጣም ነጭ እና ጽዱ እስከሚሆን ይታጠባል፡፡
2. በመቀጠልም ግዙፍ ማዋሃጃ ዉስጥ ገብቶ ይቦካል ያም ለስላሳ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም እንዳይኮረጅና በፎርጂድ እንዳይሰራም ያደርገዋል፡፡
3. በመቀጠል የተቦካው እርጥብ እንዳለ በኖቱ ልክ ሆኖ ይዘጋጃል፤እንደየሃገሩ የኖት መጠኑ ይለያያል፡፡
4. ከዛም ነጩ ወረቀት ቀለም እንዲያገኝ ይደረጋል የኖቶቹም የቁጥር መጠን ይለያል፤ የሃገሩ ስም ይጻፋል፤ፎቶዎችም ይጨመሩበታል፡፡
5. የብር ኖትን ልዩና እንዳይኮረጅ ከሚያደርጉ ዋና ነገሮች የደህንነት ክሮች የሚባሉት ሲሆኑ አብረቅራቂም ናቸው፡፡
እያንዳንዱ ክሮች ላይ ጥቃቅን ቁጥሮች ያሉት ሲሆን የእያንዳንዱ የብር መጠን ላይ ያሉት ቁጥሮች የተለያዩ ናቸው፡፡ እነዚህም ቁጥሮች ትክክለኛን ብር በሚለይ መሳሪያ የሚታዩ ሲሆን ለመኮረጅ የሚሞክሩ ሰዎች ይህንን ቁጥር የሚያሳይ መሳሪያ የላቸዉም፡፡
6. በመቀጠልም ዉሃዊ ምልክቶች ይጨመራሉ ያም ማለት ኖቱ ላይ ያለዉን ስዕል ብርሃን ላይ ሲሆን እንዲታይ የሚያደርገው ምስል ማለት ነው፡፡
7. በመቀጠልም ወረቀቱ እንዲደርቅ ይደረጋል ይህም ለብር ብቻ በተዘጋጀ ምድጃ ዉስጥ ነው፡፡
8. በመቀጠልም ማተሚያው ከብር ላይ ያለዉን እርጥበት ሙሉ በሙሉ በመንቀሳቀስ ያስወግደዋል፡፡
9. በመቀጠልም ገንዘቡ ታትሞ ለሚመለከተው አካል ይደርሳል፡፡
ታዲያ ህጋዊ የመገባባያ ኖት ወይም ብር ማተምና ማሳተም ለመንግስታትና ስልጣኑ ላላቸው አካላት ብቻ የተፈቀደ ነው፡
ይህንን አልፎ ግን ግለሰቦችና የተደራጁ ቡድኖች ገንዘብን ለማተምና ህዝቡን ለማጭበርበር በከፉ ተግባራቸው ሙከራ ሲያደርጉ ይታያል፡፡
ይሁን እንጂ የተደረጉና ሊደረጉ የታሰቡ ሙከራዎች ሁሉ የአጭበርባሪዎችን እኩይ ተግባር ለመመከት ከዘመኑ ጋር እኩል እያደገ በመጣው የዘርፉ ምርመራዎችና ክትትሎች የሚከሽፉና የሚጋለጡ መሆናቸው ይታወቃል።
በመሆኑም የአጭበርባሪዎችን እኩይ ተግባርና የሀሰተኛ ኖቶችን ዝውውር በመግታት ረገድ ህብረተሰቡ ሀሰተኛ ኖቶች ዕድል እንዳያገኙ በግብይት ወቅት መጠርጠር ማረጋገጥ እንዲሁም የአጭበርባሪዎችን ሴራ ማጋለጥና የተጠናከረ ተሳትፎ ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡፡
ምንጭ ግንቦት 9/2015(ዋልታ) በአብዱልከሪም መሃመድ
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
6.4K viewsedited 17:58